Alex Sheger

Alex Sheger

Share

Alex Sheger Ethiopian artist
singer & Writer

25/05/2026

🙏አምላኬ ሆይ እንደ ቶተንሃም በተአምር ከሞት አትርፈኸኛል ለዚህም🙏 ከልቤ አመሠግንሃለሁ ❤ አሁን ደግሞ እንደ አርሰናል ታሪኬን ቀይረውና ወዳጆቼ ደስ ይበላቸው የማይወዱኝ ሠዎችም እያዩኝ በስራህ ይደነቁ🙏

አሌክስ ሸገር
ከኢትዮጵያ ዋና ከተማ አዲስ አበባ
💚💛❤

Photos from Alex Sheger's post 19/05/2026

ብራቮ! ልጆቻችን በ3 ኛው ጨዋታ በሚገባ ክሳችሁናል!

💚💛❤️ ኢትዮጵያ 1-0 ቱኒዚያ 🇹🇳
# አሚር 90+3
ወደ አለም ዋንጫ ለማለፍ 90 ደቂቃ ብቻ ቀርቶናል!!!

አሌክስ ሸገር
ከኢትዮጵያ ዋና ከተማ አዲስ አበባ
💚💛❤️

08/05/2026

' ❤️ እ.ል.ኸ.ኛ. ነው!

ሠላም ………ወዳጅ ጓአደኞቼ ሙዚቃውና ክሊፑ ተሠርቶ እስኪያልቅ ድረስ ከመጀመሪያው ቀን የስቱዲዮ ቆይታዬ ከሳንፕሉ ለቅምሻ ያህል ልጋብዛችሁ ………,እ.ል.ኸ.ኛ …ነው!

እልኸኛ ……ነው!

አሌክስ ሸገር
ከኢትዮጵያ ዋና ከተማ አዲስ አበባ
💚💛❤️

06/05/2026

አይከብድም ወይ፡ የኔ ፍቅር
ለሠው ብሎ………ብቻ መኖር
አይከብድም ወይ፡ የኔ ቆንጆ
ለሠው ብሎ ፣ ሠውን ማጣት
አይከብድም ወይ …እናትዬ
ለእውነት ቆሞ ፣ መዋል ግራ
አይከብድም ፣ ወይ አዲስዬ
አራዳው ልጅ ፣ በሌቦች አፍ
በሆዳሞች… ስባል ፋራ?

አሌክስ ሸገር
ከኢትዮጵያ ዋና ከተማ አዲስ አበባ
💚💛❤️

04/05/2026

" እውቅና መስጠት አትወዱም እንጂ ነግሬያችሁ ነበር👌

አሌክስ ሸገር
💚💛❤
ከኢትዮጵያ ዋና ከተማ አዲስ አበባ

02/05/2026

ደቡብ አፍሪካ ለምትኖሩ የሀገሬ ልጆች በሙሉ ኦሮሞ ትግሬ ፣ አማራ፣ጉራጌ፣ወላይታ ሃዲያ…ወዘተ ሳትሉ በአንድነት ቁሙ! የመጣባችሁን አረመኔ መንጋ በአንድ ላይ መክቱ ራሳችሁን ተከላከሉ!

Photos from Alex Sheger's post 25/04/2026

እንዲህ አይነት ልብ ሠባሪ መርዶ ስሠማ መኖር ያስጠላኛል

ከድር ማለት የኔ ድራመር ነበር!

በfacebook ም ሆነ በስልክ ስንገኛኝ የምጠራውም እንደዛ እያልኩኝ ነበር።

የኔ ድራመር!

ሃና ማሪያም ገና ሙዚቃ የጀመርኩ ወቅት በጩጨነቱ ከወንድሙ ከማል ጋር ግቢያቸው ውስጥ እንዴት እንደሠሩት አላውቅም ብቻ በቀለም ቆርቆሮና በእንጨት በሠሩት እጅግ ጉደኛ ድራም እቤታቸው እየሄድኩ ተራ በተራ እየመቱልኝ እኔ እየዘፈንኩ እንደጉድ ትሬሊንግ እሠራ ነበር።

ከታላቅ ወንድሙ ከሚሎ ጋር ጥሩ ቀረቤታ ቢኖረንም በተለይ ከከድር ጋር ግን በጣም ነበር የምንግባባው።(የምንዋደደው)
ረዥም ሠአትም ስለ ሙዚቃ እያወራን እየተነጋገርን እንሠራ ነበር።

በኋላ በፋሚሊ ኬዝ ሃና ማሪያምን ለቅቄ ወደ በፊት ሠፈሬ ቄራ ከተመለስኩኝ በኋላ ለረዥም ግዜ ተለያይተን እኔም እሱ ፈፅሞ ባላሠበኝ ሂወት ውስጥ ሆኜ ትንሹ ከድር አድጎ በfacebook ፈልጎኝ አገኘኝናን ስልክ ተለዋወጥን።

ከዛ በኋላ አልፎ አልፎም እየደወለ ሙዚቃው ላይ ተመልሼ እንድሠራና ስኬቴን ማየት እንደሚፈልግ ሁሌም ይወተውተኝ ነበር።

ምን ዋጋ አለው ይሄ አንድ ፍሬ ምስኪን ልጅ ገና ሳይኖር ዛሬ ሞቱን እዚሁ facebook ላይ ድንገት አየሁና ማመን ቢያቅተኝ ወደ ሠፈር ደውዬ ከሠፈር ልጆች እውነታውን አረጋገጥኩ።

እንዴት እንደሞተም በከፍተኛ ቁጭት አወጉኝ

ከድር ረመዳን ወቅት ሙሉ ቀን ፆሞ ሊያፈጥር ሲል ድንገተኛ ህመም ቢጤ ይሠማዋል።
ቤተሠቦቹም ባቅራቢያ ወዳለ መለስተኛ ሀኪም ቤት ይወስዱትና ሃኪሞቹ አንድ መርፌ ይወጉታል ከድሬም ላይመለስ በዛው ያሸልባል።

ከሞቱ አማሙአቱ እንዲሉ የሞቱን ምክንያት ስሠማ ጭራሽ ልቤ ተሠበረ ።

ደግ አይበረክትም ማለት ይሄው ነው!

ከድርዬ የኔ ድራመር የልጅ አዋቂው ፈጣሪ ነብስህን ይማር!

ለ ከማል ይመር እንዲሁም ለመላው ቤተሠባችሁ ፈጣሪ
ብርታትና ፅናቱን ይስጣችሁ።
እንዲሁም ለጓደኞቹና ለመላው የሃንዬ ልጆች ፈጣሪ ፅናቱን ይስጣችሁ!

ከድሬ……እ…ወ…ድ…ሃ…ለ…ው!

24/04/2026

እመቤቴ የነገርኩሽን አደራሽን 2×
የነገርኩሽን አደራሽን………

ኪዳነ ምህረት ማርያም ኪዳነ ምህረት
ኪዳነ ምህረት ማርያም ኪዳነ ምህረት………

16 የኪዳነምህረት ረድኤት በረከት አማላጅነት አይለየን 🙏

💚💛❤️
አሌክስ ሸገር
ከኢትዮጵያ ዋና ከተማ አዲስ አበባ

19/04/2026

ገና ለገና የአርሰናል ደጋፊ ያበሽቀኛል ብዬማ ስንት በለፋ አሠልጣኝ (በአርቴታ) ላይ አልመቀኝም መልካም እድል የአርሴ ደጋፊዎች
ትንሽ ፀባያችሁ ነው እንጂ ዋንጫማ ይገባችኋል!

19/04/2026

ልክ እንደ ቦብ ማርሊ
ሬጌን በራስታ
ነበር እኔ እማውቀው
ፀጉሩን አሳጥሮ
ቴዲ አፍሮ እሚባል
የአቶ ካሳሁን ልጅ
ጥበብ የገባው ሠው
ችክችካና ሬጌን
በአማርኛ ቋንቋ
እያቀነቀነ
ከምስራቅ አፍሪካ
ከኢትዮጵያ ተነስቶ
አለምን በሙሉ
በቺጌ ቀወጠው
----/ /---------

👌 ይመቸው!

አሌክስ ሸገር
ከኢትዮጵያ ዋና ከተማ አዲስ አበባ

Want your public figure to be the top-listed Public Figure in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Address

Addis Ababa