My Tena

My Tena

Share

መልካምነት መልካም ማድረግ መልሶ ለራስ ነው

17/11/2025
19/10/2025

🥀🥀🥀🥀

22/09/2025

ህይወት በእርምጃ ብትመተር:
ለእግሩም ችግር ነው የት ሊሰነዘር?
ከተለካች ግን በጣቶች ስንዝር !
ኢምንት'ኮ ናት ደቃቅ ነገር!

Photos from My Tena's post 09/08/2025

https://joinluvlive.com/54BeNH Download the app to meet more interesting friends from all over the world! My ID:51157583

26/04/2025

💡ቀስ እያለ ነጋ!

🔷አንዳንድ ቀን በጣም ከባድ ነው ሁሉም ነገር ይሰለቻል ከአልጋ ላይ ራሱ መነሳት ያስጠላል በጣም ደክሞኛል ስትል እንኳን ምን ለማለት ፈልገህ እንደሆነ ማንም አይረዳህም

በቃ............... ሁሉም ነገር ጭልምልም ይልብሀል ምን መስራት እንዳለብህ የት መሄድ እንዳለብህ ራሱ ግራ ይገባሀል ያስደስትህ የነበረዉ ሁሉ ያስጠላሀል በቃ መሀል ላይ ራስህን ታጣዋለህ፣ ሕይወት እንደ ደራሽ ማዕበል ይሆንብሃል፡፡ በሰላም ይሄዱ የነበሩ ነገሮች ልክ የተመካከሩ ይመስል በአንድ ላይ ይናጋሉ፡፡ የሁኔታዎች አልሳካ ማለት፣ ድንገተኛ ወጪዎች፣ የጉዳዮች መጥመም፣ የሰዎች ክህደት፣ስጋትን የሚፈጥሩ ሁኔታዎች መከሰት፣ ልክ እንደ ማዕበል በአንድ ላይ ይመጣሉ፡፡

💎ህይወት ሁሌ ሙሉ አይደለችም ፣ ማጣት ማግኘት መደሰት ማዘን መጫወት መከፋት ማዉራት ዝም ማለት መሳቅ ማልቀስ ብዙ ብዙ ነገር ይገጥመናል ሰው ይፈተንበት ዘንድ የተሰጠው ፈተና ሺ ነው፡፡ እስትንፋሱ እስካለች ድረስ ፈተናው አያልቅም፡፡ ተረጋጋሁ ሲል የሚረበሽ፤አረፍኩ ሲል እንከን የማያጣው ጥቂት አይደለም፡፡

📍ጥያቄው ግን እኛ ሰዎች በጎ በጎዉን ትተን መጥፎው ላይ ብቻ ለምን እንከርማለን ነው??

አንድ እውነታ የሚመሰረተው እውነታ ካልሆነው ነገር ጋር ተነፃፅሮ ነው። ካልሆነ ግን እውነት ሚባል ስያሜም አይኖረውም። ጥሩ መጥፎ ከሌለ ሊኖር አይችልም። ጥንካሬ ድክመት ካሌለ ሊታወቅ አይችልም።ስለዚህም መከራን አትጥላው። የመከራ ዘር በውስጡ የማንነት እድገትን ይዟልና። ያሰብከው እና ያገኘህው ነገር ሊለያይ ይችላል። ነገር ግን የቱም ሁኔታ ትምህርትን ይዞ ይመጣል፣ የምንኖረው በአንፃራዊ አለም ውስጥ ነውና።

💡ለማንም ሰው ህይወት ስህተት ወይም ትክክል መሆኑን የሚያውቀው ሲፈተን ነው። ጫጩት ለማግኘት የእንቁላሉ ቅርፊት ማስወገድ ሽፋኑን መግለጥ ያስፈልጋል፣ ወርቅ የሚወጣው ከጭቃ ውስጥ ነው። ዝናብ ሊዘንብ ሲል ነጎድጓድና የመብረቅ ብልጭታ ቀድመው መታየት ይጀምራሉ። ሌቱ ሊነጋጋ ሲል በጣም ይጨልማል። ከከባድ ምጥ በኋላ ልጅ ይወለዳል። ይህ የተለመደ የሕይወት አካል የሆነ ክስተት በእኛም ላይ ሲደርስ መረጋጋት ወሳኝ ነው፡፡

እናም ወዳጄ

✍️ህይወት ሁሌም ለማንም የትም ሙሉ አይደለችም፡፡ ቀን አለና ቀና በል፣ አስብ ባሰብከው ሀሳብ ተፅናና በተፅናናህበትም ቃል ሌሎችን አፅናና!! በሕይወት ሩጫዎችህ መሀል ያለውን ውስብስብ የሕይወት ገፅ ጠንቅቀው የሚያውቁት ጥቂቶች ናቸው። ስለሆነም ባልተረዱህ ብዙ ሰዎች እየተናደድክ ሳይሆን በተገነዘቡህ ጥቂት ሰዎች እየተደሰትክ ኑር። አልሞላ ያለው ነገር ሁሉ ፈጣሪ በራሱ ግዜ አስተካክሎ ጨምሮ ያመጣዋል ።

ዛሬን ባለህ ነገር አመስግነህ ደስ ብሎህ ኑር። ባለህ የማትረካ ከሆንክ ሩጫህ ሁሌ ሌላ ነገር ፍለጋ ብቻ የሆናል፡፡ የሌለህን ነገር ብቻ ካሰብክ በማማረርህ ውስጥ ያለህንም ታጣዋለህ፡፡ ያለህን ነገር ካሰብክ ግን በምስጋናህ ውስጥ የሌለህንም ታገኘዋለህ፡፡

መልካም ቀን

25/09/2024

ተፈጥሮ በአጠቃላይ እጅግ በጣም የተወሳሰበ ሂደት ነው ፣ እናም በውስጡ ጥሩም ይሁን መጥፎ ነገር እንደያዘ ለመናገር ከባድ ነው። ምክንያቱም የመጥፎ ነገር ውጤት ምን እንደሚሆን በጭራሽ አይታውቅም ፣ ወይም ደግሞ መልካም ዕድል ምን ይዞ እንደሚመጣ በጭራሽ አይታውቅም።

በአንድ ወቅት አንድ የቻይና ገበሬ ፈረሱ ሸሽቶ ተሰወረበት ፡፡ የዚያን ዕለት ምሽት ሁሉም ጎረቤቶቹ ተሰብስበው ሊያፅናኑት መጡ ፡፡ እነሱም “ፈረስህ በመጥፋቱ በጣም አዝነናል ፡፡ ይህ በጣም መጥፎ ነገር ነው አሉት ፡፡
”ገበሬውም“ ምናልባት ”አላቸው ፡፡

በሚቀጥለው ቀን ፈረሱ ሰባት የዱር ፈረሶችን ይዞ ወደ ቤቱ ተመለሰ
ምሽት ላይ ሁሉም ጎረቤቶቹ ወደ ቤቱ በመምጣት“ ዕድለኛ ነህ በጣም ፡፡ እንዴት ያለ ታላቅ ክስተት!! አሁን እኮ ስምንት ፈረሶች አሉህ! ” አሉት።
ገበሬው እንደገና“ ምናልባት ”አላቸው ፡፡

በሚቀጥለው ቀን ልጁ ከፈረሶቹ አንዱን ለመጋለብ ሲሞክር ወድቆ እግሩን ተሰበረ ፡፡ ጎረቤቶቹም “ ይሄ ደግሞ በጣም መጥፎ አጋጣሚ ነው” አሉት።
ገበሬውም በድጋሚ “ምናልባት” ብሎ መለሰላቸው ፡፡

በሚቀጥለው ቀን የግዳጅ መኮንኖች ሰዎችን ወደ ጦርርነት ለማሰማራት በመጡበት ጊዜ የገበሬው ልጅ የተሰበረ እግር ስለነበረውው ልጁን አይመጥንም ብለው ጥለውት ሄዱ ፡፡ እንደገና ጎረቤቶቹ ሁሉ መጡ እና “ይሄ እንዴት ደስ ይላል ልጅህ እኮ ጦርነት ከመግባት ተረፈ!” አሉት ፡፡
አሱ ግን እንደገና “ምናልባት” አላቸው፡፡

ገበሬው ስለ ትርፍ ወይም ኪሳራ ፣ ጥቅምና ጉዳት ከመሳሰሉ ነገሮች ከማሰብ በጥብቅ ተቆጥቧል፣ ምክንያቱም የህይወት ክስተቶች በጭራሽ ይዘው የሚመጡትን ነገር ማናችንም አናውቅም። ብዙዏቻችን በህይወት ባህር ውስጥ የምንሰምጠው፤ እንደገበሬው ከኑሮ ጋር በቀላሉ መንሳፈፍን ስላለመድን ነው። በህይወታችን ወስጥ በእኛ ቁጥጥር ስር የሆኑ ነገሮች አሉ፤ ሌሎች ከእኛ ቁጥጥር ውጪ የሆኑ ደግሞ እጅግ ብዙ ነገሮች ይኖራሉ።

በኑሮ ባህር ውስጥ መስመጥ የሚከሰተው ታዲያ፤ ከእኛ ቁጥጥር ወጪ የሆኑ ነገሮች ላይ ግትርነታችንን ለማሳየት ስንሞክር ነው። መለወጥ የማንችለውን ነገር በጉልበት ለመለወጥ ስንሞክር፤ የመዋኘት ጥበቡ ጠፍቶናል ማለት ነው። ህይወት ወደድንም ጠላንም ባልታሰቡ ፈተናዎች እና ስጦታዎች የተሞላች ነች። እንደ ገበሬው ረጋ ብለን ካልተንሳፈፍን በፍጹም ከለውጥ ጋር ተግባብተን ለመኖር አይቻለንም።

እናም ወዳጄ ዓለም እና የሰው ልጅ ተፈጥሮ በብዙ ስንክሳር የተሞሉ ናቸው። ባሳለፍከው ህይወት ብዙ ክስተቶች ታይተዋል። የሚያሳዝንም የሚያስደስቱም ሁኔታዎች የህይወት ገጾች ናቸው። ሁሉ ይመጣል፣ ሁሉም ይሄዳል። ያለፈውና የሚሄደውን በሰላም ሸኘው። አሁን ካለው ጋር በሰላም ተከባብረህና ተሳስበህ ኑር። ዘልዓለማዊ ክስተት የለም፣ ለውጥ እንጂ ። ከሁኔታዎች በላይ መሆንን እወቅበት። መረጋጋት መልካም ነው።

ውብ ምሽት

21/09/2024

አንተው ተናገር እኛ ዝም ብለናል!!

17/09/2024

💡የሆነ መንደር ውስጥ አንድ ጅል ይኖራል። የመጨረሻ ጅል ከመሆኑ የተነሳ አምሳ ሳንቲም እና አስር ሳንቲም መለየት አይችልም። እና የመንደሩ ነዋሪዎች ይመጡና "አንተ ጅል ና እስቲ ከዚህ ምረጥና ውስድ" ብለው አምሳ ሳንቲም እና አስር ሳንቲም ሲያስቀምጡለት አስሯን ያነሳል። "ይሄ (አምሳውን) ይሻልሃል" ሲሉት "እምቢ ብሎ ያለቅሳል።

🔆 "አይ ይሄ ጅል … ኑ ጉድ እዩ፤ ኑ ጉድ እዩ" ይሉና አስር ሳንቲም እና አምሳ ሳንቲም ድጋሚ ያስቀምጡለታል። አሁንም አስሯን ያነሳል። ኧረ ይሄ ይሻልሃል ሲሉት "እምቢ፣ እምቢ" ብሎ ያለቅሳል።

በኋላ በዚህ ጅል ዘመዶቹ እያፈሩ ሄዱ። አንዱ ዘመዱ መጣና "አንተ ጅል … ሁሌ ባንተ እንዳፈርን እንቅር? ኧረ ተው ግድ የለህም፣ ተው ግድ የለህም። አምሳ ሳንቲም እና አስር ሳንቲም መለየት አቅቶህ አምሳ ሳንቲም ሲሰጡህ በአስር ሳንቲም ታለቅሳለህ? ኧንደው ምናለ አምሳውን ብታነሳ?" ብሎ ሲመክረው። "ጅልስ አንተነህ ነህ! አምሳውን ያነሳው ቀን አያስመርጡኝም።

🔆ማነው ጅል? እነሱ ወይስ ጅል ብለው የሚያስቡት ብልጥ? አያችሁ እሱ ብልጥ ጅል ነው፤ እስከ ኖረ ድረስ አስር፣ አስር ሳንቲሟን እየመረጠ የተጃጃለ መስሎ ያጃጅላቸዋል፤ ምክንያቱም አምሳዋ አንዴ ነች፤ አስሯ እስካለ ትቀጥላለች።

💡እንደነሱ ከሆነ አምሳ ሳንቲሟን የብልጠቱ፣ አስር ሳንቲሟን ደግሞ የጅልነቱ መገለጫ አድርገዋታል። ለሱ ግን አስር ሳንቲሟ የብልጠቱ መሰወሪያ፣ መደበቂያ ነች። አምሳዋን የመረጠ ቀን ጅልነቱ ያበቃል፤ ማንም አያስመርጠውማ። ምክንያቱም አውቋል፤ ነቅቷል ይሉታላ።

✍ዓለማየሁ ገላጋይ

ከሞኝ ብልጦች ብልጥ ሞኞች የሚያዋጣውን ያውቃሉ!

❤❤❤

Want your public figure to be the top-listed Public Figure in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Website

Address

Addis Ababa