Ethio time

Ethio time

Share

መልካም ይሆናል❤

19/05/2026

The Arsenal. Your Premier League champions.

16/05/2026

አማርኛ የBRICS መገልገያ ቋንቋ ሆኖ ተወስኗል!👇👇
በሕንድ፣ ኒውዴልሂ የተካሄደው የ BRICS+ አባል አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ አማረኛ ቋንቋን ጨምሮ በተለያዩ ቋንቋዎች ሲሰራጭ ነበር። የአማረኛ ቋንቋ የተቋሙ መገልገያ እንዲሆን የኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ ዲፕሎማሲያዊ ትግል አድርጓል።

በተመሳሳይ የአማረኛ ቋንቋ የአፍሪካ ሕብረት የሥራ ቋንቋ
እንዲሆን ከፍተኛ ጥረት እየተካሄደ ሲሆን በሙከራ ላይ የሚገኘው Amharic Machine Learning (AML) ወደትግበራ ከገባ ለዲፕሎማሲያዊ ጥረቶቻችን ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚኖረው ይሆናል።

14/05/2026

ልጁ አንድ ነገር ይሁንና የገፋፋችሁት ሰዎች ሲያሳዝን በጌታ😂

10/05/2026

መንግስት በድርጊቱ ተሸማቋል።

በረከት ከገበሬዋ የሰራችው ፋውል እንዳለ ሆኖ ነገር ግን የታችኛው የስልጣን እርከን ውስጥ ያሉ ባለስልጣናት የሰሩትን ሿሿ በእሷ ለማላከክ የሄዱበት አካሄድ ሙሉ መንግስርን አሸማቆታል።

በጣም የሚገርመው በዚህ የወንጀል ሰንሰለት ማን ከማን ተጣምሮ፣ ወንጀለኞች ከክልል እስከ ፌደራል ፖሊስ ሰው እንዳላቸው ቁልጭ አድርጎ ያሳየ ክስተት ነው።

አብይ እራሱ ይሄን ሲሰማ አንገቱን ነው የወዘወዘው፣ በጭራሽ ፌደራል ፖሊስ ውስጥ በዚህ ወንጀል የሚሳተፍ አልው ብሎ አይጠረጥርም ነበር።

አሁን መንግስት በነዚህ ሰዎች ላይ ምርመራ የጀመረ ሲሆን ፌደራል ፖሊስ ዋና መስሪያ ቤት ያሉ ሹማምንት ማምለጫ መንገድ እያፈላለጉ ነው።

በነገራችን ላይ ወንጀላቸውን ለመደበቅ በዋናነት አወንታ በርሲሳን ተጠቅመዋል። አወንታ ባላወቀው ነገር ጫፍ ይዞ እየተሟገተ ነው። Ethio time

10/05/2026

🔥 Marziyeh Amirizadeh ትባላለች 47አመቷ ሲሆን ኢራናዊ አሜሪካዊት ነች ብዙዎች በድፍረቷ ለሀይማኖቷ ባላት ድንቅ መስዋዕትነት ያቋታል ያደንቋታል።

20,000 በላይ መጽሐፍ ቅዱሶችን ቤት ለቤት በማከፋፈልና የቤት አምልኮ ስብሰባዎችን በመመራት ምክንያት ኦሷ እና ጓደኛዋ የሞት ፍርድ ተፈርዶባቸው ነበር። ነገር ግን ሰውነታቸውን ሊያስሩ ቢችሉም… መንፈሳቸውን ግን ማሰር አልቻሉም።

በኢራን አስፈሪው Evin እስር ቤት ውስጥ 259 ቀናት ታስራ እያለ፣ Marziyeh Amirizadeh እና ጓደኛዋ Maryam Rostampour ግን ፍርሃትን አልመረጡም። በእስር ቤቱ ውስጥ እስረኞችን ብቻ ሳይሆን ጠባቂዎችንም ሲሰብኩ ስለክርስትና ሲያስተምሩ ነበር።

በመጨረሻም በዓለም አቀፍ ግፊትና ድጋፍ ከታሰሩበት እስር ቤት በነፃ ተለቀዋል ። ዛሬ Marziyeh Amirizadeh በአሜሪካ ትኖራለች፣ ስለ እምነት፣ ስለ ነፃነት፣ ስለ ኢራን ህዝብ በድፍረት አሁንም ትናገራለች።

🔥 እውነተኛ ጀግና ማለት ይህ ነው፤ ላመንክበት ነገር እስከመጨረሻው መቆም።

08/05/2026

በሁለቱ ወገኖች በኩል ያለው ያልተነገረው እውነት!

ረዳና ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በጠረጴዛ ዙሪያ ተቀምጠው መነጋገር ከቻሉ፣ "ለምን ነባሩ ህወሓትና ብልፅግና ይሄን ማድረግ ተሳናቸው?" አብሮ የመስራቱ መንገድ ለምን እንዲህ እሾህ በዛበት? ብለን እንጠይቅ ይሆናል።

ነገር ግን በሁለቱም ወገን ያለው "ቁርሾ" እና "ስጋት" ከምንገምተው በላይ ጥልቅ ነው። እስቲ ምን እደሆኑ እንመልከታቸው ፦

1️⃣ የህጋዊነት ማነቆ
የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ህወሓትን ከዝርዝር ሰርዞታል። በህግ ጥላ ስር ለመመለስ ደግሞ ፓርቲው እንደ አዲስ መመዝገብና የፌደራል መንግስቱን ህግጋት መቀበል አለበት። ለነባሮቹ አመራሮች ግን ይሄ "ውርደት" ነው። "የ50 ዓመት ታሪክና የህዝብ ደም ያለበትን ድርጅት ስጡኝ ብሎ መለመን ሰብዕናን ዝቅ ማድረግ ነው" ብለው ያምናሉ። ህጋዊነታችን ከሰነድ ሳይሆን ከከፈልነው መስዋዕትነት ነው የሚል የቆየ እምነት ስላላቸው፣ አዲስ አበባ ሄዶ መደራደር እንደ "ልመና" ይታያቸዋል።

2️⃣ የጦርነቱ ጠባሳ 💔
ጦርነቱ እጅግ አሰቃቂ ነበር። በደብረፅዮን የሚመራው የፓርቲው ክንፍ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይን የሚያየው ትግራይን ለማጥፋት እንደመጣ ጠላት ነው። "ከጠላታችን ጋር አብረን ብንሰራ፣ የረገፍውን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ወጣቶችና የተሰቃየውን ህዝብ መክዳት ነው" የሚል ስሜት አላቸው። ለእነሱ አብሮ መስራት "ሰላም" ሳይሆን "እጅ መስጠት" ይመስላቸዋል። ይህ የቆሰለ እምነት ደግሞ በቀላሉ ለመሻር ይከብዳል።

3️⃣ እምነት ማጣት
"የፌዴራል መንግስቱ ህወሓትን እንደ ድርጅት ማጥፋት ይፈልጋል" የሚል አስተሳሰብ በህወሓት በኩል ያለ ሲሆን

ፌደራል መንግስቱ በበኩሉ
ነባር የህወሓት አመራሮች "ሰላም ፈላጊ" ሳይሆን "አሁንም አድብተው እኛን ለመጣል እድል የሚጠብቁ" ናቸው ብሎ ያምናል።

4️⃣ የርዕዮተ-ዓለም ልዩነት
እዚህ ጋር የሃሳብ ጦርነት አለ።
👉 ህወሓት "አብዮታዊ ዲሞክራሲን" እና ትግራይ የራሷ የሆነ ጠንካራ ስልጣን ያላት፣ እንደ ሀገር የምትቆጠር ክልል እንድትሆን ይፈልጋል።
👉 የፌደራል መንግስቱ (ብልፅግና) ደግሞ አንድነቱ የጠነከረና ማዕከላዊ መንግስቱ ስልጣን ያለው ኢትዮጵያን ይሻል።

አብሮ መስራት ማለት "የሰሜን ንጉስ" የመሆን ህልሙን ትቶ፣ ለአዲስ አበባ ታዛዥ መሆን ማለት ነው።

ይሄ ደግሞ ለነባር መሪዎቹ ለመዋጥ የሚያስቸግር መራራ ፅዋ ነው።

በመጨረሻም...
ሁለቱም ወገኖች የራሳቸውን እውነት ይዘው ቆመዋል። ችግሩ ግን መሪዎቹ በፖለቲካዊ 'ኢጎ' ውስጥ ሆነው 'እኔ ልክ ነኝ' በሚሉበት እልህ ውስጥ፣ በመሃል የሚጎዳውና ሰላሙ የራቀው የትግራይ ህዝብ ነው።

ፌዴራሉ 'እንደ አዲስ ተመዝገቡ' ይላል፤ ህወሓት 'አልመዘገብም' ይላል። አንዱ 'ህግ' ሲል፣ አንዱ 'ታሪክ' ይላል ... ህዝቡ ግን ዳቦ፣ ሰላምና መረጋጋት ይላል!

ሰላም እንዲመጣ ማን ቀድሞ እጁን መዘርጋት አለበት? ፌደራል መንግስቱ ህወሓትን እንደ ድርጅት መቀበል? ወይስ ህወሓት የፌደራል መንግስቱን ህግጋት መቀበል?

ጊዜ የሚፈታው ነገር ነው።

ሰላም ለሀገራችን ... ሰላም ለህባችን 🇪🇹

30/04/2026



በስሙ ምክንያት ተባረረ

+-+++ ታዋቂው ቲክቶከር አዶናይ በስሙ ምክንያት ወደ እስራኤል እንዳይገባ ተከለከለ በመጣበት አውሮፕላን ወደ አገሩ መልሰውታል ... አዶናይ ከወላጅ እናቱ ጋ ቅድስት እየሩሳሌምን ለመጎብኘት ወደ እስራኤል የተጓዘ ቢሆንም ..በህጉ መሰረት የካናዳ ፓስፖርት ስላለው ቪዛ (visa on arrival) እስራኤል ሲደርስ ኤርፖርት ሊመታለት ይገባው ነበር ነገርግን እየሩሳሌም Ben Gurion airport ሲደርስ ያላሰበው ገጥሞታል ..አዶናይAdonai የሚለው ስም ለእስራኤላውያን የአምላካቸው የእግዚአብሔር ስም ሲሆን ትርጉሙ የስልጣን ሁሉ እና የሀይል ሁሉ ባለቤት(ምንጭ) ሁሉም የሚገዛ ጌታ ማለት ነው.. በአይሁድ ህግ የፈጣሪያቸው ስሞች በፍፁም ለሰው ልጅ ይሁን ለመላዕክት አይሰጡም ለዚህም ነው ቲክቶከሩ አዶናይእየሩሳሌም ኤርፖርት ሲደርስ ያላሰበው ያጋጠመው ቲክቶከር አዶናይ ወረፋው ደርሶ ፖስፖርቱን ለኦፊሰሩ ይሰጣል የኢሜግረሽን ኦፊሰሩ ፓስፖርት ተቀብሎ ስሙን ካየ በሃላ በንዴት ስምህ አዶናይ ነው ብሎ ይጠይቀዋል አዶናይ አዎ ይላል ያኔ እስራኤላዊ ኦፊሰርሴኩሪቲ ይጠራል ይዘው ወደ ማቆያ ወሰዱት የደህንነት አባላት ከበው ለምን መጣህ እንዴት አዶናይ ተባልክ ጥያቄ ያበዙበታል አዶናይ በድንጋጤ ይዋጣል ትውልደ ኢትዮጵያዊ መሆኑን ይናገራል የእስራኤል ደህንነት አባላትም አማርኛ የሚችል ቤተ እስራኤላዊ አባላቸውን ይጠሩታል እሱም አዶናይን ይጠይቀዋል ከዛም ስሙን ወላጆቹ እዳወጡለት አሱ በፈቃዱ ሰሙን ቀይሮ እዳልሆነ ይረዳል ከዛ በሱ ትብብርወደ ካናዳ ኤምባሲ ደውሎ አሳወቀለት በመጨረሻ እስራኤል በሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያ አይሁዶች ቤተ እስራኤላውያን ትብብር እና የካናዳ ኤምባሲ ትብብርበመጣበት አውሮፕላን ወደ መጣበት አገርመልሰውታል ... ወደ እስራኤል ተመልሶ እዳይመጣ ተነግሮታል አሻራ ሰቷል... እንኳን በሰላም ተመለስክ
አዶናይ፣ ኤልሻዳይ፣ ኢየሱስ፣ አማኑኤል ወዘተ እያልን ስም ማውጣቱ ቢቀርብንስ

30/04/2026

በደቡብ አፍሪካ ኢትዮጵያዊያን፣ ሶማሌዎችና የማላዊ ዜጎች እየተመረጡ ሲገ-ደሉ በጉዳዩ መንግሥት ዝምታን መምረጣቸው አስገርሞኛል። ምንም የሀዘን መግለጫ እንኳን ያላወጣው መንግስት ከእነዚህ ዜጎቻችን የዶላር ምንዛሬን ብቻ ነው የሚፈልገው ማለት ነው..? 🤔 የሌሎች ሀገራት መሪዎች [ ለምሳሌ የማላዊ መንግስት ከዚህ ቀደም በነበሩ የ Xenophobia ጥቃቶች ወቅት ዜጎቹን ለማውጣት አውሮፕላን እስከመላክና የዲፕሎማሲ ግንኙነቱን እስከመገምገም ደርሶ ነበር 💔

Photos from Ethio time's post 29/04/2026

ደቡብ አፍሪካ ሁሌም የኢትዮጳያውያን መቃብር ስፍራ ናት ! ላለፉት አመታት ለመቀበል የሚከብዱ ብዙ አይነት የሀገራችን ህዝቦች ነፍስ እንደ ቅጠል በደቡብ አፍሪካ ሲረግፍ ኖሯል የሚያስዝነው 90% እሚሆኑት በጣም ወጣት ናቸው እጅግ አሰቃቂ በሆነ መንገድ ሲያልፉ አካላቸውን ሲያጡ ማየት ኖርማል ነገር ሆኗል ሁሌም እንቆቅልሽ ሆኖብኝ የቀረ ጥያቄ እዛች ምድር የረገጠ የኛ ዜጋ ራሱ በራሳችን ዜጋ ላይ ለጉድ ነው ግ$ድያ ሚፈፅመው እዛ ሀገር ላይ ምን አይነት የሞት መንፈስ ነው የተናወጠው ?

በጣም የሚያመው ግን ይሄም ሲሆን ወደዛ ያለው የህዝባችን ፍሰት እንኳን ሊቀንስ በእጥፍ እየጨመረ ይሄዳል ትላንት የተሰማ አሳዛኝ የሶስት ሰዎች ሞት አለ በጣም የሚያስፈራ ምድር ደቡብ አፍሪካ !

በሰላም አይተኙም ያለ ሽጉጥ አትሰራም አቤት ሰቀቀን

21/04/2026

አሳዛኙ ተግባር በነጮቹ ያልተገዛችሁ ሀገር ኢትዮጵያ የዘረኝነት ጥቃት አደረሰች ቢባል አንገት ያስደፋል ።
የኢትዮጵያ ቡናው ጋናዊዉ ግብ ጠባቂ የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች የዘረኝነት ጥቃት ፈፅመዉብኛል ዝንጀሮ ብሮ ሰድበዉኛል በማለት በፌስቡክ ገፁ ላይ በማስፈሩ በሀገሩ ጋና ዉስጥ አሁን ላይ ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆኗል።

የጥቁሮች ኩራት ሆኔን ጥቁሮችን መሳደብ ተገቢ አይደለም በዚህ ጉዳይ ሀሳባችሁን አስቀሚጡልን

Want your public figure to be the top-listed Public Figure in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Website

Address

Addis Ababa