Joye
Let's spread good vibes and light up each other's world! ✨ #ChooseJoy #LiveBright have global aim
15/03/2026
With Sheraton Addis, a Luxury Collection Hotel – I'm on a streak! I've been a top fan for 9 months in a row. 🎉
ኢትዮጵያ የኦጋዴን የተፈጥሮ ጋዝ ኤክስፖርት ፕሮጀክት ሰረዘች
👉 በምትኩ የማዕድን ሚኒስትር የተፈጥሮ ጋዝን ለአገር ዉስጥ ፍጆታ ለመጠቀም የሚያስችል አዲስ ፕሮጀክት እያጠና ነዉ
ኢትዮጵያ በኦጋዴን ክልል የሚገኘውን የተፈጥሮ ጋዝ ወደ ውጭ የመላክ ፕሮጀክት የገንዘብ እጥረትና የትግበራ መዘግየትን ዋቢ በማድረግ እንደሰረዘች አስታውቃለች። በምትኩ፣ የማዕድን ሚኒስቴር የተፈጥሮ ጋዝን ለአገር ውስጥ ፍጆታ፣ በተለይም ማዳበሪያ ለማምረትና ኤሌክትሪክ ኃይል ለማመንጨት የሚያስችል አዲስ ፕሮጀክት እያጠና መሆኑን ገልጿል።
የማዕድን ሚኒስቴር እንደገለጸው፣ ኢትዮጵያ በተለይም በኦጋዴን ተፋሰስ፣ በካሉብና ሂላላ አካባቢዎች ከፍተኛ የተፈጥሮ ጋዝ ክምችት ያላት ሲሆን፣ ይህም ከ50 ዓመታት በላይ ለሚሆን ጊዜ ማዳበሪያ ለማምረት፣ ኃይል ለማመንጨትና ለተለያዩ የነዳጅ ምርቶች ለማገልገል የሚያስችል እንደሆነ ቢገመትም፣ እስካሁን በጥልቀት አልተጠናም።
የጅቡቲ የቧንቧ መስመር ፕሮጀክት መሰረዝ
በ2022፣ ከኦጋዴን የተፈጥሮ ጋዝ አውጥቶ በ767 ኪሎ ሜትር ርዝመት ባለው የቧንቧ መስመር ወደ ጅቡቲ በመላክ በፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ ወደ ውጭ ለመላክ ታቅዶ የነበረው ፕሮጀክት መሰረዙ ተገልጿል።
ካፒታል የመለከተዉ Ethiopia Energry Outlook 2025 ሪፖርት እንደሚጠቁመዉ ለፕሮጀክቱ መሰረዝ ዋነኛዉ ምክንያት የፋይናንስ ችግሮች ሲሆን ይህ ደግሞ ኢትዮጵያ ከተፈጥሮ ጋዝ ወደ ውጭ በመላክ ገቢ የማመንጨት አቅሟን ቀንሷል።
በ4 መንስታዊ ተቋማት አማካኝነት በተዘጋጀዉ በዚህ ሪፖርት ላይ እንደተገለፀዉ :- የማዕድን ሚኒስቴር በአሁኑ ወቅት ማዳበሪያ ማምረትን ጨምሮ በአገር ውስጥ የተፈጥሮ ጋዝን የመጠቀም አዲስ ፕሮጀክት እያጠና ነው።
ሚኒስቴሩ የተፈጥሮ ጋዝን ወደ ኤሌክትሪክ ኃይል ለማመንጨት ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ጋር ለመስራት ፍላጎት እንዳለው ገልጿል። ይህ በተለይ ዝናብ በሌሉባቸው ዓመታት የኃይል ስርዓቱን ለማመጣጠን ጠቃሚ አማራጭ ሊሆን ይችላል ተብሏል።
ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በዓመት ከ4 ቢሊዮን ዶላር በላይ በሚገመት ወጪ ከውጭ በሚገቡ የነዳጅ ምርቶች ላይ ጥገኛ መሆኗ ይታወቃል።
ይህንን ለመቀነስ፣ መንግስት የአገሪቱን የተፈጥሮ ሀብቶች ለማልማት የሚያስችል ስትራቴጂ በመተግበር ላይ ነው። አዲሱ ፖሊሲ በተፈጥሮ ጋዝ ፍለጋ ላይ በማተኮር ዘርፉን ለኩባንያዎች ክፍት በማድረግ እና ኢንቨስትመንቶችን በማበረታታት ላይ ቅድሚያ እንደሚሰጥ ተመላክቷል።
የሠራተኞች መነሻ የደመወዝ ወለል 8,384 ብር እንዲሆን ተጠየቀ
* መንግሥት መነሻ ወለል ከ1,200 እስከ 2,000 ብር በሚል ረቂቅ አዋጅ አቅርቧል
* ከፍተኛ ግብር የሚጣልባቸው ሠራተኞች ደመወዝ ከ150,000 ብር ጀምሮ እንዲሆን አሳስቧል
ወርኃዊ ደመወዛቸው እስከ 8,384 ብር የሆነ ሠራተኞች ከግብር ነፃ እንዲሆኑ የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) ለመንግሥት ጥያቄ ማቅረቡን ገለጸ፡፡ የኢሠማኮ ፕሬዚዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ ለሪፖርተር እንዳሉት፣ ወርኃዊ ደመወዛቸው እስከ 8,384 ብር የሆነ ተቀጣሪ ሠራተኞች ከግብር ነፃ እንዲደረጉ ለመንግሥት ጥያቄ አቅርበዋል፡፡
የገንዘብ ሚኒስቴር ላለፉት ዘጠኝ ዓመታት በሥራ ላይ ቆይቷል የተባለውን የገቢ ግብር አዋጅ 979/2008ን ለማሻሻል ጉዳዩ ይመለከታቸዋል ከተባሉ ባለድርሻዎች ጋር ውይይት በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ በዚህ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ እስከ ሁለት ሺሕ ብር የሚከፈላቸው ሠራተኞች ከግብር ነፃ እንዲሆኑ ተደንግጓል፡፡
ኢሠማኮ እስከ 8,384 ብር ድረስ የሚከፈላቸው ተቀጣሪዎች ከግብር ነፃ እንዲሆኑ ለገንዘብ ሚኒስቴር በደብዳቤ እንደጠየቀ አስታውቋል፡፡ አቶ ካሳሁን በዓለም ባንክ መረጃ መሠረት ዕለታዊ ገቢው ከሦስት ዶላር በታች የሆነ ሰው ደሃ በመሆኑ፣ የመንግሥት የገቢ ግብር በዚህ ወለል ሥር ያሉ ተቀጣሪዎችን ታሳቢ ሊያደርግ ይገባል ብለዋል፡፡
በማናቸውም ቀጣሪ ተቋማት የሚሠሩ ሠራተኞች በወር ከ8,384 ብር እስከ 22,974 ብር ደመወዝ የሚያገኙ ሠራተኞች፣ አሥር በመቶ ግብር እንዲጣልባቸው መንግሥትን መጠየቁን ኢሠማኮ ገልጿል፡፡
ከ22,975 እስከ 44,530 ብር ወርኃዊ ደመወዝ ተከፋዮች የ15 በመቶ፣ ከ44,531 እስከ 72,336 ብር የሚከፈላቸው ደግሞ 20 በመቶ፣ እንዲሁም ከ72,337 እስከ 107,449 ብር የ25 በመቶ ግብር እንዲጣልባቸው ኢሠማኮ በደብዳቤው አሳስቧል፡፡
ከ107,450 እስከ 150,107 ብር ድረስ የሚከፈላቸው ሠራተኞች 30 በመቶ ግብር፣ እንዲሁም 150,108 ብር እና ከዚያ በላይ የሚከፈላቸው ተቀጣሪ ሠራተኞች ደግሞ 35 በመቶ ግብር እንዲከፍሉ ለመንግሥት ባቀረበው ደብዳቤ ኢሠማኮ መጠየቁን ገልጿል፡፡
አሁን በሥራ ላይ ባለው የሠራተኞች የገቢ ግብር አዋጅ መሠረት እስከ 600 ብር ድረስ የሚከፈላቸው ሠራተኞች ከግብር ነፃ ሲሆኑ፣ ከ10,900 ብር ጀምሮ ደግሞ 35 በመቶ ግብር እንዲከፍሉ ይገደዳሉ፡፡
የገንዘብ ሚኒስቴር ከአንድ ሳምንት በፊት ለውይይት ይፋ ባደረገው የገቢ ግብር ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ 1,200 ብር፣ 1,600 ብር እና 2,000 ብር ወርኃዊ ደመወዝተኞች ከግብር ነፃ እንዲደረጉ ድንጋጌ መኖሩ ይታወሳል፡፡
የመንግሥት የገቢ ግብር ማሻሻያው ሠራተኞች ያለባቸውን ወቅታዊ የኢኮኖሚ ሁኔታ ታሳቢ ያላደረገ እንደሆነ የተለያዩ የውይይት ተሳታፊዎች አስተያየት መስጠታቸው አይዘነጋም።
(Ethiopian reporter )
14/06/2025
ይህ እየተዘዋወረ ያለው መረጃ ትክክለኛ ነው ?
09/06/2025
At just 15 years old, an Ethiopian innovator gained global recognition by developing a special soap aimed at helping treat skin cancer. His groundbreaking work, driven by a passion for science and healthcare, earned him the title of TIME's 2024 Kid of the Year, celebrating his impact on both medicine and youth innovation.
የ 67 ሚሊየን ብር ሽልማት የሚጠብቃት ቆንጆዋ ሀሴት
በ1951 በኤሪክ ሞንሪ የተጀመረውና ዘንድሮ ለ72 ኛ ጊዜ በህንድ አይደራባድ በተካሄደው የሚስ ወርልድ የቁንጅና ውድድር ኢትዮጵያዊቷ ሀሴት ደረጀ ፡ ከታይላንዳዊቷ ተፎካካሪዋ በመቀጠል የሁለተኛ ደረጃን ይዛ ማጠናቀቋ ይታወሳል ።...
በዚህ ውድድር ፡ ታይላንዳዊቷ Opal Suchata Chuangsri አንደኛ ... ኢትዮጵያዊቷ ሀሴት ደረጀ ሁለተኛና .. የፖላንዷ ተወዳዳሪ Maja Klajda ሶስተኛ ሆነዋል ።....
እና በዚህ ውድድር ከ1-3 የወጡት ለሁሉም ሽልማት የሚሰጣቸው ሲሆን አንደኛ የወጣችው Opal Suchata በአልማዝ ፈርጦች ያጌጠ ዘውድ ትሸለማለች ፡ በአንደኛነቷ ከሚሰጣት የአንድ ሚሊዮን ዶላር ሽልማት በተጨማሪም ፡ ለአንድ አመት ያህል በእንግሊዝ ሀገር ፡ ሙሉ ወጭዋ ተችሎ ተቀምጣ ፡ Beauty with a Purpose በሚባለው ፕሮጀክት ስር አለም አቀፍ የበጎ አድራጎት ጉዞ ይዘጋጅላታል ። ከተለያዩ አለም አቀፍ የፋሽን ካምፓኒዎች ጋር የማስታወቂያና የብራንድ ውል በሚሊዮን በሚቆጠር ገንዘብ ትፈራረማለች ።....
ከሷ በመቀጠል ያለችው የኛዋ ሀሴት ደረጀ ናት ። ሀሴት በዚህ ውድድር የሁለተኛ ደረጃን ይዛ በማሸነፏ የአምስት መቶ ሺህ ዶላር ፡ ወይም በኛ ከ67 ሚሊየን ብር በላይ የምትሸለም ሲሆን ፡ በአለም ታዋቂ በሆኑ ዲዛይነሮችና የፋሽን ካምፓኒዎች የነጻ አቅርቦት ይሰጧታል ።
በአለም ታዋቂ የሆኑ የሜካፕና የፋሽን ካምፓኒዎች የተለያዩ ማስታወቂያዎችን ያሰሯታል ፡ ብራንድ አምባሳደር በመሆን በሚሊዮን የሚቆጠር ገቢ ታገኛለች ።
ከመኪና እስከ የቅንጦት እቃ መሸጫ መደብሮች ምርቶቻቸውን እንድታስተዋውቅላቸው የነጻ ስጦታ ያቀርባሉ ። .....
ሀሴት ባላት VIP Travel Packages ከአለም አቀፍ የፕሮሞሽን ካምፓኒዎች ጋር አብራ በመስራት ወደተለያዩ ሀገራት ስትጓዝ አየር መንገዶች ፡ በቢዝነስ ክላስ ደረጃ በነጻ እንድትጓዝ ሁኔታዎች ይመቻቹላታል ። እንዲሁም በአለም አቀፍ ደረጃ ያሉ በባለ አምስት ኮከብ ሆቴሎች ውስጥ በነጻ ማረፍ ትችላለች ።....
ሶስተኛ የወጣችው ፖላንዳዊቷ Maja Klajda ም በገንዘብ ደረጃ 250 ሺህ ዶላር የምትሸለም ሲሆን የተለያዩ እድሎችንም ታገኛለች ።
ሀሴት ደረጀ እንኳን ደስ ያለሽ 👑
02/06/2025
ቻይና ከኢትዮጵያም በላይ በኢትዮጵያውያን ዘንድ ተወዳጅነት አገኘች
በአዲስ አበባ ታሪካዊ የአፍሪካ አዳራሽ ይፋ በተደረገው አዲስ የአፍሪካ ምርጥ ብራንዶች ሪፖርት መሰረት፣ ቻይና በኢትዮጵያ ውስጥ እጅግ ተወዳጅ ሀገር በመሆን ኢትዮጵያን እራሷን ጭምር በልጣለች። ይህ ጥናት የውጭ ሀገራት ተፅዕኖን እና የሀገር ውስጥ ብራንዶች የሚያጋጥሟቸውን ተግዳሮቶች የሚያመላክት ነዉ ተብሏል።
በ31 ሀገራት በተካሄደው የብራንድ አፍሪካ ጥናት፣ ኢትዮጵያውያን ከሚያደንቋቸው ሀገራት ዝርዝር ውስጥ ቻይና ቀዳሚ ስትሆን፣ ኢትዮጵያ፣ ሩሲያ፣ ዩናይትድ ስቴትስ እና የተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ ይከተሏታል።
ምንም እንኳን 68% የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ለአፍሪካ የወደፊት ዕጣ ፈንታ ብሩህ ተስፋ ቢኖራቸውም፣ የሀገር ውስጥ ብራንዶች ግን እውቅና ለማግኘት እየተቸገሩ ነው።
በኢትዮጵያ ከሚደነቁ 100 ምርጥ ብራንዶች ውስጥ 6% ብቻ ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ፣ በአጠቃላይ ከሚደነቁ ብራንዶች ውስጥ 13% ብቻ የሀገር ውስጥ ናቸው። ይህ የውጭ ብራንዶች የበላይነትን እና የሀገር ውስጥ ኩባንያዎች ተጨማሪ ትኩረት እንደሚያስፈልጋቸው ያሳያል።
በአፍሪካ Nike፣ Adidas፣ Samsung፣ Coca-Cola እና Apple ከፍተኛ አምስት ተወዳጅ ብራንዶች ሲሆኑ፣ በኢትዮጵያ ደግሞ መቄዶኒያ፣ ኢትዮ ቴሌኮም እና ኮካ ኮላ "ለህብረተሰብ መልካም በመስራት" ተወዳጅነትን አግኝተዋል።
ዝርዝሩን ያንብቡ
https://capitalethiopia.com/2025/06/01/china-tops-ethiopias-admiration-rankings-surpassing-ethiopia-itself/
የኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂ ጫፍን ማሳያ ተደርጎ የሚወሰደው የሳዑዲ አረቢያ ሰማይ ታካኪ ሕንፃ አለምን እያስደመመ ነው።
አንድ ኪሎ ሜትር የሚረዝመውና በሳዑዲ አረቢያ ግንባታው በይፋ የተጀመረው ጅዳ ታወር ሰማይ ታካኪ ሕንፃ ግንባታው ከሦስት አመት በኃላ በ2028 ዓ.ም ሊጠናቀቅ ይችላል።
በግንባታው ዘመን አመጣሽ አዲስ ቴክኖሎጂ ለመጀመሪያ በተግባር ላይ ውሏል። የሕንፃው ግንባታ የመጀመርያ ምዕራፍ እየተካሄደ ያለው በ4D ሞዴል ቴክኖሎጂ ሲሆን፣ ይህም ሞዴል በFreeform 3D የተፈጠረ ከመሆኑም በላይ፣ ቴክኖሎጂው ሰማይ ጠቀሱ ህንፃ እንዴት እንደሚጠናቀቅ ከማሳወቁም በላይ አመላካች የማጠናቀቂያ ቀናትንም በውስጡ አካቶ ይዟል።
ግንባታው ሙሉ በሙሉ ከተጠናቀቀ የዱባይ 828 ሜትር ቡርጅ ካሊፋን የሚበልጥ አዲሱ የዓለማችን ረጅሙ ህንፃ ይሆናል።
📷 Freeform 3D / SBG
14 ባንኮች በተሳተፉበት ስድስተኛው የውጭ ምንዛሪ ጨረታ የአንድ የአሜሪካ ዶላር አማካይ ዋጋ 133 ብር ሆኖ ተመዘገበ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ 50 ሚሊዮን ዶላር ያቀረበበት በዚህ ስድስተኛው ዙር የውጭ ምንዛሪ ጨረታ፣ 14 ባንኮች ተሳትፈውበታል። የአንድ ዶላር አማካይ ዋጋ 133.17 ብር ሆኖ ሲመዘገብ፣ ከ16 ቀናት በፊት በተካሄደው አምስተኛው ዙር ጨረታ የአንድ ዶላር ዋጋ 132.9 ብር እንደነበር ይታወቃል። ይህም መጠነኛ የዋጋ ጭማሪ አሳይቷል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ ገበያን ለማረጋጋትና የውጭ ምንዛሪ መረጋጋትን ለመቆጣጠር ያለመ ይህን ጨረታ በየሁለት ሳምንቱ እንደሚያካሂድ ማሳወቁ ይታወሳል።
ባለፈዉ በተደረገዉ አምስተኛ ዙር ጨረታ ባንኩ 60 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ያቀረበ ሲሆን፣ በጠቅላላው 16 የንግድ ባንኮች የውጭ ምንዛሪ ድልድል ማግኘት ችለው ነበር። የዘንድሮው ጨረታ ግን የቀረበውን የዶላር መጠን ወደ 50 ሚሊዮን ዝቅ አድርጎታል።
Parent-teacher-associations can play an important role to make sure children are enrolled in school, learning and well-supported - this is especially meaningful for girls and children with disabilities.
Together, GPE and UNICEF South Sudan helped to train members of parent-teacher-associations in 🇸🇸 , improving their capacities to focus on school development, resource mobilization, goal setting and financial management.
Members of the association are happy with the results of the training:
👉 Now, they are able to better engage with community members and bring out-of-school children back to the classroom while using their resource mobilization skills to fund school activities, support volunteer teachers and carry out minor repairs in classrooms.
Canada’s new 2035 Nationally Determined Contribution (NDC) sets a bold climate target: a 45–50% emissions reduction below 2005 levels by 2035, building on its 2030 goal of 40–45%.
The updated NDC also emphasizes climate resilience, Indigenous leadership, and just transition measures—highlighting cities, housing and land-use planning as critical to reaching net zero by 2050. 📉🌎
As Canada raises its climate ambition, leadership on the ground is evolving too. Former Vancouver mayor Gregor Robertson wraps up his term as Special Envoy for Cities in the CHAMP initiative, where he championed stronger local-national climate collaboration.
“If all 75 CHAMP countries fully support local action, we can cut 2.6 billion tons of emissions—equal to Japan, Germany, and the UK combined,” he noted.
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the public figure
Telephone
Website
Address
Addis Ababa
Opening Hours
| 12:00 - 06:00 |