Tesfa
የሰው ልጆችን በእውነተኛ ተስፋቸው ላይ እንዲያተኩሩ ለመርዳት የተከፈተ ገፅ ነው
02/06/2026
እግዚአብሔር ለእኛ ለሕዝቡ የሰጠን ትእዛዝ የምንኖርባትን ምድር ሰላም እንድንፈልግ እና ስለ ምድራችንም እንድንጸልይ ነው። ለሀገራችን፣ ለሕዝባችን እና ለመሪዎቻችን መጸለይ አለብን።
መሪዎች በጥበብ እንዲመሩ፣ ፍትሕ እንዲሰፍን፣ ሕዝብም በአንድነት እንዲኖር መጸለይ። ለሀገራችን የሚያስፈልጋት የእግዚአብሔር ሰላም ነውና።
ኤርምያስ 29:7 በእርስዋ ሰላም ሰላም ይሆንላችኋልና ወደ እርስዋ ላስማርክኋችሁ ከተማ ሰላምን ፈልጉ፥ ስለ እርስዋም ወደ እግዚአብሔር ጸልዩ።
01/06/2026
ሀገር ሰላምን፣ ሕዝብም ፈውስን ይሻል።
ይህ የሚሆነው ደግሞ በጸሎት፣ በትሕትና እና ወደ እግዚአብሔር በመመለስ ነው።
በዚህ ዘመን ሀገራችን ሰላምን፣ ፈውስን እና የእግዚአብሔርን ምሕረት እጅግ ትሻለች። እንደ ሀገር ለምናቅደው ነገሮች ሁሉ፣ ተስፋችን እግዚአብሔር ብቻ ነው።
ወደ እግዚአብሔር በጸሎት ብንጮህ፣ እርሱ ይሰማናል። የተሰበረ ልባችንንም ይፈውሳል፣ ለሀገራችንም ሰላሙን ያመጣልናል።
2 ዜና 7:14 በስሜ የተጠሩት ሕዝቤ ሰውነታቸውን አዋርደው ቢጸልዩ፥ ፊቴንም ቢልፈጉ፥ ከክፉ መንገዳቸውም ቢመለሱ፥ በሰማይ ሆኜ እሰማለሁ፥ ኃጢአታቸውንም ይቅር እላለሁ፥ ምድራቸውንም እፈውሳለሁ።
Follow Tesfa on:
Instagram | Facebook | Telegram | TikTok | Youtube | Threads
31/05/2026
እግዚአብሔር የልጆቹን ጩኸት ይሰማል። አንዳንድ ጊዜ በችግር፣ በሀዘን ወይም በጭንቀት ውስጥ ልታልፍ ትችላለህ፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ጸሎትህን ይሰማል፣ የምታልፍበትንም ያውቃል፤ ደርሶም በጊዜው ይረዳሀል።
እግዚአብሔር ቅርብ ነው፣ የሚሰማ እና የሚያድንም አምላክ ነው።
ዛሬ በጭንቀት ውስጥ ከሆንክ ተስፋ አትቁረጥ። እግዚአብሔር ጩኸትህን ይሰማል፤ በጊዜውም ይደርስልሀል።
“ጻድቃን ጮኹ፥ እግዚአብሔርም ሰማቸው ከመከራቸውም ሁሉ አዳናቸው።”— መዝሙር 34፥17
28/05/2026
እውነተኛ እረፍትና እፎይታ የሚገኘው በእግዚአብሔር ልጅ በኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው።
በሀጢያት ወይም በመንፈሳዊ ሕይወትህ ደክመሀል? ኢየሱስ ወደ እኔ ና፤ እረፍት እሰጥሃለሁ ብሎ ይጠራሀል።
እርሱ የሚሰጠው እረፍት: ከሀጢዓተኝነት እና ከበድለኝነት ነፃ የሚያወጣ እረፍት፣ ከጭንቀትና ከፍርሃት ነፃ የሚያወጣ እረፍት፣ በልብ ውስጥ የተረጋጋ ሰላምና እፎይታ የሚሰጥ እረፍት፣ የዘላለም ሕይወት የሚገኝበት እውነተኛ እረፍት ነው።
ዛሬ ወደዚህ እረፍት ተጠርተሀል!
ማቴዎስ 11:28 እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ።
27/05/2026
እግዚአብሔር በማንኛውም የሕይወት ሁኔታ ውስጥ ለልጆቹ ቅርብ ነው። ከአደጋ ምትሸበት እና የምትጠለልበት መጠጊያ ቦታ ነው። እግዚአብሔር በድካምህ ጊዜ የሚያበረታህ ኃይልህ ነው። አንዳንድ ጊዜ በሕይወትህ የምታልፍበት ነገር ከአቅምህ በላይ ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን እግዚአብሔር በዚያ ጊዜ ውስጥ እንኳ የሚያጸናህ እና እንድትቀጥል የሚያደርግ ኃይል ይሰጥሀል። እግዚአብሔር አምላክ በችግርህ ጊዜ ከአንተ ጋር ያለ፣ የሚረዳ፣ የሚያጽናና እና ተስፋ የሚሰጥ አባት ነው።
ዛሬ በሕይወትህ ውስጥ ድካም፣ ፍርሃት ወይም ጭንቀት ካለ፣ ብቻህን አይደለህም። እግዚአብሔር መጠጊያህ፣ ኃይልህ እና ረዳትህ ነው። ወደ እርሱ በጸሎት ብትቀርብ ሰላሙን ይሰጥሃል፣ ልብህንም ያበረታል።
መዝሙር 46:1 አምላካችን መጠጊያችንና ኃይላችን፥ ባገኘን በታላቅ መከራም ረዳታችን ነው።
26/05/2026
በዚህ ቃል መሰረት ፈተና ወይም ፍርሃት ቢኖር እግዚአብሔር ከአንተ ጋር መሆኑን ይነግርሀል። ብቻህን አይደለህም፤ እርሱ ይመራህል፣ ያጽናናሀል፣ ኃይልም ይሰጥሀል።
በምታልፍበት ሁኔታ ሳይሆን በእግዚአብሔር ህልውና ታመን። እርሱ በምትሄድበት ሁሉ ከአንተ ይሆናል። ፍርሃትህን አስወግደህ፤ በእግዚአብሔር ብቻ ታምነህ ምትኖርበትን ህይወት ዛሬ ወስን!
"በምትሄድበት ሁሉ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነውና ጽና፥ አይዞህ አትፍራ፥ አትደንግጥ ብዬ አላዘዝሁህምን?” ኢያሱ 1፥9
15/05/2026
እግዚአብሔር በሰው ህይወት ውስጥ የሚፈቅደውን ሁሉ ነገር ለበጎ ይለውጠዋል። ዛሬ የምታልፍበትን ነገር ሁሉ እግዚአብሔር ይቀይረዋል።
አንዳንድ ጊዜ የምታልፍበት ነገር ለምን እንደሚሆን ላይገባህ ይችላል፤ ህመም፣ መዘግየት፣ ችግር ወይም ውድቀት ቢኖርም በዚህ ሁሉ ውስጥ ግን እግዚአብሔር እየሠራ ነው።
እርሱ ከባድ ነገሮችን እንኳ ለመልካም ያደርጋቸዋል።
ዛሬ ያልገባህ ሁኔታ ቢኖርም ተስፋ አትቁረጥ። እግዚአብሔር ከህይወትህ አንድም ክፍል አይለይም። እርሱ እያንዳንዱን ነገር ለመልካም ፍጻሜ እያዘጋጀህ ነው።
ሮሜ 8:28 እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን።
14/05/2026
በጣም ከባድ ጊዜያቶችን በምታሳልፍበት ጊዜ እንኳን እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነው። ዳዊት ብዙ ጦርነት፣ ፍርሃት እና አደጋ አጋጥሞት ነበር፤ ነገር ግን በእግዚአብሔር አብሮነት ላይ ሙሉ በሙሉ ይተማመን ነበር። ምክንያቱም እግዚአብሔር እንዲህ ባለ ጊዜ እንኳ እንደማይተወው ስለሚያውቅ ነው።
ዛሬ ምንም አይነት ጭንቀት ቢገጥምህ፣ ብቻህን አይደለህም! እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነው፣ እርሱም ሰላምን ይሰጥሃል።
መዝሙር 23:4 በሞት ጥላ መካከል እንኳ ብሄድ፡ አንተ ከእኔ ጋር ነህና ክፉን አልፈራም፤ በትርህና ምርኵዝህ እነርሱ ያጸናኑኛል።
13/05/2026
የእስራኤል ሕዝብ በመከራና በስደት ውስጥ ባሉበት ጊዜ እግዚአብሔር ግን ለእነርሱ ያለውን ፍቅር እና መልካም ዕቅድ ነግሯቸዋል።
እነርሱ ተስፋ ቢቆርጡም እግዚአብሔር ግን እኔ ስለእናንተ መልካም አሳብ አለኝ ብሎ ተስፋን እንደሰጣቸው፤ ይህ ቃል ዛሬም ለአንተ ህይወት ይሰራል፡፡ ለህይወትህም ትልቅ መጽናናት ነው።
አንዳንድ ጊዜ ሕይወት ግራ ሊያጋባህ ይችላል፤ ፈተና፣ መዘግየት ወይም ያልተጠበቀ ነገር ሲመጣ እግዚአብሔር እንደረሳህ እና እንደተወህ ሊሰማን ይችላል።
ነገር ግን እግዚአብሔር ስለ አንተ ያለው አሳብ የሰላም፣ የተስፋ እና የመልካም ፍጻሜ ነው።
እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነው የመጨረሻው ታሪክህም በእርሱ በእጁ ነው።
ዛሬ በምንም ዓይነት ግራ መጋባት እና በጭንቀት ብታልፍ፣ እግዚአብሔር ስለ አንተ ያለው ዕቅድ መልካም መሆኑን አስታውስ። እርሱ ተስፋ የሚሰጥ አምላክ ነው፤ ወደፊትህም በእጁ ውስጥ ነው።
ኤርምያስ 29:11 ለእናንተ የማስባትን አሳብ እኔ አውቃለሁ፤ ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም።
12/05/2026
ሕይወት ብዙውን ጊዜ የፍርሃት፣ የጥርጣሬ እና የድክመት ጊዜያትን እንድታልፍ ታስገድድሀለች። ነገር ግን ብቻህን አይደለህም! እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነው።
የእግዚአብሔር መገኘት ከሚገጥምህ ከማንኛውም ችግር ይበልጣል።
እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፤ እኔ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ፤ አበረታሃለሁ፥ እረዳህማለሁ፥ በጽድቄም ቀኝ ደግፌ እይዝሃለሁ። ትንቢተ ኢሳይያስ 41:10
Click here to claim your Sponsored Listing.