Elijah Xo Promotion company
Elijah Xo iz a promotion and travel agency Company at Esteren Ethiopia (Nazareth)
‘’ .... በጥጋባቸው አድዋ ላይ ተዋግተው ድል ሆኑ :: እኔ ግን በድንቁርናቸው ብዛት የእነዚያን ሁሉ ... ደም በከንቱ መፍሰሱን እያየው ድል አደረኳቸው ብዬ ደስ አይለኝም....''
አፄ ምኒልክ ለሙሴ ሽፍኔ መጋቢት 23 ቀን 1888 ዓ.ም ከፃፉት ደብዳቤ :
እንኳን ለ 129ኛው የዓድዋ ድል በዓል አደረሰን!
“...in their arrogance they were defeated at Adwa. Seeing however that so much ... blood was shed due to their great ignorance, I do not say happily that I was victorious over them.”
Emperor Menelik II to Monsieur Léon Chefneux
March , 1896
Happy ADWA, Happy victory day!
17/09/2021
ራስ
Irreechaa Fashion Show Come joins us as we celebrate the beginning of Birra (spring) with a spectacular fashion show showcasing the talent and diversity of Oromo and African culture during the annual Irreechaa festival here in Finfinnee|Addis Ababa.
07/09/2021
AXUM OBELIX N AXUM ZION
07/09/2021
HARER
08/07/2021
31/08/2020
በ1540 ዓ.ም የተሳለ ታሪካዊ የግድግዳላይ ስዕል::
22/06/2018
ታሪካዊውና ታላቁ የሸንኮራ ዮሐንስ መጥምቀ መለለኮት ቅዱስ ዮሐንስ እንዴት አሁን ወዳለበት ቦታ እንደመጣ በጥቂቱ እናስዳሳችሁ፡፡ የመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ፅላት አሁን ያለበት መምህር ሀገር ሸንኮራ ዮሐንስ ከመምጣቱ በፊት በ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ዮሐንስ ደብረ ኤጎራ መንዝ እንደነበረ ይነገራል፡፡
አባ ገድሉ ብርሃኑ የሚባሉ መነኩሴ በስደት ዘመን ታቦተ-ህጉን ይዘው ከደብረ ኤጎራ ከእጩ ዮሐንስ በመነሳት ወደ ጠራ ሳፋጅ ዮሐንስ ይሰደዳሉ፡፡ ከዚያም በፈቃደ እግዚአበብሄር መምህር ሠርፀ-ወልድ ከቡልጋ ጠራ ከአባ ገድሉ ብርሀኑ ፅላቱን በመቀበል አሁን ታቦተ-ህጉ ካለበት በስተቀኝ በኩል ባለው ትልቅ ዋሻ ያስቀምጡታል፡፡ ለ30 አመታት በዚያ ዋሻ ካስቀመጡት በኋላ በ1620 ዓ.ም መምህር ሰርፀ-ወልድ ከዚህ ዓለም በሞት የሚለዩበት ጊዜ ሲደርስ እግዚአብሔር በራዕይ እንዲህ ይላቸዋል አንተ መሄጃህ ደርሷል ስለዚህ ታቦተ-ህጉን አውጥተህ ቤተ-ክርስቲያኒቱን መስርት በዚያም ብዙ ታምራት ይደረግበታል ለምፅ ይነፃል፣ድውያንን ይፈዉሳል ብሎ በራዕይ ይገልጥላቸዋል፡፡ መምህር ሰርፀ-ወልድ ትውልድ አፅሜን እንዳይወቅስ በማለት ታቦተ-ህጉን 30 አመት ከኖረበት ዋሻ አውጥተው አሁን ካለበት ቦታ በ1620 ዓ.ም ይመሰርቱታል፡፡ በዚያም ለብዙ ዘመናት ከቆየ በኋላ ለመምህር ሰርፀ ወልድ እንደተነገራቸው ለምፃምን የሚያነፃ፣ ድውያንን የሚፈውስ፣የታሰሩትን የሚፈታ ታላቅ የምስራች በ1954 ዓ.ም ይገለፃል፡፡ ይኸውም የመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ጠበል መፍለቅ ነው፡፡የጠበሉ አገኛኘትም በቦታው የነበሩ አቃቢ አባ ካሳ ራዕይ ያያሉ፡፡ አባ ካሳ በተኙበት በስማቸው ጠርቶ በቤተልሄሙ ፊት ለፊት ጫካ ውስጥ ጠበል ፈልቋልና ይህንን ለካህናቱና ለህዝቡ አሳውቅ ይላቸዋል፡፡አባ ካሳ ሌሊት የተገለፀላቸውን ራዕይ ለማረጋገጥ ጠዋት በተነገራቸው ገደል ውስጥ ቀኑን ሙሉ ጠበሉን ሲፈልጉ ቆይተው ሳያገኙት ይመለሳሉ፡፡ በድጋሚ በቀጣዩ ሌሊት በራዕይ በስማቸው ደጋግሞ በመጥራት ጠበሉን ፈልገህ አጣኸው ድጋሚ ተመልሰህ ከገደሉ ውረድ እንደዛሬው ደክመህ አትመለስም፡፡ ምልክት አደርግልሃለሁ አላቸው፡፡ አቃቢውም በዚህ መለኮታዊ ትዕዛዝ በማግስቱ ወደ ጠበሉ ሲወርዱ ከፊትለፊታቸው እርግብ ትመራቸው ጀመር፡፡ ደክሟቸው ሲያርፉ ከቅጠል ላይ እያረፈች በመጨረሻ ጠበሉ አጠገብ ካለ ዛፍ ላይ በማረፍ ክንፎቿን አርገበገበች፡፡ አባ ካሳም ወደቋጥኙ ቢመለከቱ ጠበሉን አዩት፡፡ እግዚአብሄርን አመስግነው ከጠበሉ ቀመሱ፡፡ ለካህናቱና ለህዝቡም ነግረው ሚያዝያ 30 ቀን ታቦተ-ህጉ ካህናቱና ሕዝቡ ወደ ገደሉ ወርደው ጠበሉ ተባረከ እስከዛሬም በርካታ ድንቅ ታምራትን እያደረገ ይገኛል፡፡
Click here to claim your Sponsored Listing.