Hakim

Hakim

Share

Ethiopian blend of medicine, history & humor.

Photos from Hakim's post 09/06/2026

ያለመውለድ ችግር (መካንነት) 10 ዋና ዋና ምክንያቶች

ጥንዶች ጋብቻ ከፈፀሙ በኋላ በቀጣዩ የህይወት ምዕራፍቸው የሚጠብቁት ነገር ልጅ መውለድ ነው። አንድ ሴት ምንም የመውለድ ችግር ሳይኖርባት እና የወሊድ መከላከያ ሳትጠቀም በአንድ ወር ውስጥ የማርገዝ እድሏ 20% ሲሆን 6 ወር ውስጥ 60% እንዲሁም በ1 ዓመት 85% ነው። ለሁለት አመት ቢሞክሩ ደግሞ 95% የማርገዝ እድል አላቸው።

15% የሚሆኑ ጥንዶት በአንድ አመት ውስጥ ምንም አይነት የወሊድ መከላከያ ሳይጠቀሙ ቋሚ የግብረስጋ ግንኙነት እያደረጉ የማርገዝ ችግር ያጋጥማቸዋል። ይህም መካንነት ወይም ያለመውለድ ችግር አጋጥሟቸዋል ተብሎ ህክምና ይጀመርላቸዋል።

የሴቷ እድሜ ከ35 አመት በላይ ከሆነ ለ6ወር ሙከራ አድርጋ እርግዝና ካልተፈጠረ የመካንነት ህክምና መጀመር አለባት።

መውለድ ያለመቻል እጅግ በርካታ ምክንያቶች ሲኖሩት አንዳንዶቹ ወደ 20% የሚሆኑት ይህ ነው የሚባል ምክንያት የላቸውም።

ያለመውለድ ችግር (መካንነት) ዋናዋናዎቹ ምክንያቶች እነሆ

1. ከወንድ በኩል የሚኖር መካንነት (male factor infertility)

እንደ ዓለም ጤና ድርጅት መረጃ መሰረት 20% የሚሆነው ያለመውለድ ችግር (መካንነት) ከወንድ በኩል የሚኖር ነው።ይህም በጭንቅላት ውስጥ የሚመረት ሆርምሞን ማነስ, በዘር ፍሬ ላይ የሚያጋጥም ሰፐርም የማምረት ችግር (primary testicular defect in spermatogenesis), የወንድ የዘር ትቦ መዘጋት, እንዲሁም ምክንያቱ የማይታወቅ የወንድ መካንነት (idiopathic male infertility) ዋና ዋናዎቹ ናቸው።

ከ70-80% የሚሆነው በወንዶች በኩል የሚያጋጥም መካንነት በዘር ፍሬ (te**es) በተለያዩ ምክንያቶች ዘር ያለማምረት ችግር የሚመጣ ነው። ይህም በዘር (genetics) ፣ በኢንፌክሽን ፣ በአደጋ፣ ጨረር መጋለጥ፣ ለሙቀት መጋለጥ እንዲሁም የሆርሞን ማነስ ምክንያት ሊሆን ይችላል።

2. በሴቶች ላይ እንቁላል የመለቀቅ ችግር (ovulatory dysfunction)

25% የሚሆነው ያለመውለድ ችግር (መካንነት) ምክንያት የእንቁላል ያለመለቀቅ ችግር ነው። አንዲት ሴት ስትወለድ ከ1-2 ሚሊየን የሚጠጉ እንቁላሎች በኦቫሪ ውስጥ ይኖራሉ። አነዚህ እንቁላሎች እድሜዋ አየጨመረ ሲሄድ እየቀነሱ ይመጣሉ። እርግዝና እንዲፈጠር እንቁላል ከኦቫሪ ወደ ማህፀን ግድግዳ መለቀቅ አለበት ይህ የመለቀቅ ሂደት በተለያየ ሆርሞኖች ቁጥጥር ስር የወደቁ ናቸው። የእነዚህ ሆርሞኖች መዛባት እንቁላል እንዳይለቀቅ ሊያደርጉ ይችላሉ።
PCOS ፣ ከአንጎል የሚመነጭ ሆርሞን ማነስ፣የፕሮላክቲን መብዛት ፣ የታይሮይድ ሆርሞን ማነስ/መብዛት እንደምክንያትነት ይጠቀሳሉ።

3. የማህፀን ቱቦ መዘጋት

በግራና በቀኝ በኩል የሚገኙ እንቁላል አስተላላፊ ትቦዎች በተለያየ ምክንያት ሊዘጉ ይችላሉ። በሰርጀሪ፣ በኢንፌክሽን፣ ከማህፀን ውጭ በሚያጋጥም እርግዝና እንዲሁም በሆድ እቃ ውስጥ በሚያጋጥም ጠባሳና መጣበቅ ሊዘጋ ይችላል።

4. በማህፀን ግድግዳ ላይ የሚያድግ እጢ

በማህፀን ግድግዳ ላይ የሚፈጠር እጢ እንቁላልና ስፐርም ሴል እንዳይገናኙ እንዲሁም እርግዝና ከተፈጠረ በኋላም ምቹ ሁኔታ እንዳይኖር ሊያደርጉ ይችላሉ።

5. የማህፀን አፈጣጠር ችግር

በተፈጥሮ ለሁለት የተከፈለ ማህፀን (septated uterus) ተደጋጋሚ ውርጃ እንዲኖር እንዲሁም ምንም ማህፀን ያለመፈጠር ችግር የመካንነት ችግር ሊያመጡ ይችላሉ።

6. ኢንዶሜትሪዮሲስ (endometriosis)

ጠባሳና መጣበቅን በመፍጠር የማህፀን ትቦ እንዲዘጋ እንዲሁም በኦቫሪ ውስጥ እጢ (endometrioma) በመፈጠር የእንቁላል ማምረት ሂደትን በማወክ መካንነትን ሊያመጣ ይችላል።

7. የዘረ መል (chromosome) ችግር

Turner syndrome, down syndrome, Kallman syndrome, የተባሉ የዘረመል ችግሮች ያለመውለድ ችግር ያመጣሉ።

8. ምክንያቱ የማይታወቅ (unexplained infertility)

ብዙ ምርመራዎች ተደርገውም ምንም ምክንያት ላይገኝ ይችላል።ይህም 20% የሚሆኑት ያለመውለድ ችግር ያለባቸው ጥንዶች ላይ ያጋጥማል።

9. የግብረ ስጋ ግንኙነት አደራረግ ችግር

እርግዝና እንዲፈጠር እርግዝና የሚፈጠርበትን የወር አበባ ኡደት ጊዜ ጠብቆ የማድረግ ችግር፣ ማለስለሻ ጄሎችን መጠቀም ያለማርገዝ እድልን ይጨምራሉ። እንቁላል የሚለቀቅበትን ወቅት ጠብቆ (Fertile period) ተደጋጋሚ ግንኙነት ማድረግ የማርገዝ እድልን ይጨምራል።

10. እድሜና የአኗኗር ሁኔታ

የሴቶች እድሜ ሲጨምር የእንቁላል መጠን እየቀነሰ ይሄዳል። በተጨማሪም ሲጋራ ማጨስ ፣ ለተለያዪ ኬሚካሎች መጋለጥ፣ ለጨረር መጋለጥ፣ የክብደት መጨመር፣ ጭንቀት፣ ከፍተኛ መጠን ያለው አልኮል መውሰድ ለመካንነት ያጋልጣል።

ዶ/ር በላይ አለሙ የማህፀንና ፅንስ ስፔሻሊስት

ቴሌግራም ይቀላቀሉ: t.me/HakimEthio

Photos from Hakim's post 09/06/2026

"ልጄ ቀኝ እና ግራ እግሩ እኩል አደሉም ወይም ሲራመድ ይስበዋል ምን ሊሆን ይችላል?"

ይህ ከአንድ ወላጅ የተጠየቅኩት ጥያቄ ነው:: መራመድ በጀመሩ ህፃናት የእግር ቁመት እኩል አለመሆን ወይም አንዱ መሰለል ብዙ ምክንያቶች ቢኖሩትም አንደኛው ከነርቭ መወጠር ጋ የተገናኘ ነው::

በእግር ላይ ያለው ምልክት ቆይቶ ከወራት ወይም ዓመታት በሁአላ ቢሆንም የሚታየው ችግሩ ግን የሚከሰተው ቀድሞ ነው:: በአብዛኛው በተፈጥሮ ነው የሚከሰተው:: ቀድሞ ማወቅም ይቻላል::

በተፈጥሮ የሚከሰት የህብለሰረሰር መወጠር (Tethered cord) ወደ እግር የሚሄድ የነርቭ መልክት መዛባት ስለሚያመጣ አንደኛው እግር ከሌላኛው እኩል አያድግም:: ልጁም እግሩን በነፃነት ማዘዝ እየከበደው ይመጣል:: ይሄንንም ለማካካስ ሲል በተርከዝ መርገጥ ትቶ በ ግር ጣቶች ብቻ ለመርገጥ ይሞክራል:: እግሩም እየተወጠረ መሄድ ስለሚከብደዉ እየሳበው ይሄዳል::

ከዚህ ባለፈ የነርቭ መልክት መተላለፍ መዛባት ወደ ሽንት ፊኛ ሲደርስ ሽንት መቆጣጠር አለመቻል ይሄም በልጆች ቀኑን ሙሉ ዳይፐር አንደረጠበ መቆየት ይኖራል:: ሽንት በፊኛ እየተጠራቀመ ሲመጣ ወደ ኩላሊት እየተመለሰ ኩላሊት ዉስጥ መጠራቀም እና ተደጋጋሚ የኩላሊት እንፈክሽን ያመጣል አለፍ ሲልም ኩላሊት ስራ ሊያቆም ይችላል::

ወደ ታችኛው የአንጀት ክፍል የሚሄድ የነርቭ መልክት መዛባት ደግሞ ድርቀት ያመጣባቸዋል:: ይህ መወጠር ከአርከካሪ ጎን ያሉ ጡንቻዎችን በማዛባት የአከርካሪ መጣመም ሁሉ ያመጣል::

እንዴት ማወቅ ይቻላል?

ችግሩ ከዉስጥ ቢሆንም ከቆዳ ላይ የሚያሳየው ምልክት አለ:: ለምሳሌ ከጀርባ ላይ ያለ አንድ ቦታ ችምችም ያለ ፀጉር: መሃል ወገብ ላይ ያበጠ ወይም የተከማች ስብ: መሃል ወገብ ላይ ያለ Dimple (መሰርጎድ) : የአከርካሪ መጣመም እና የመሳሰሉት::

ሕክምና አለው?

አዎ መታከም ይችላል:: ነገር ግን ሕክምናው ህመሙ እንደታወቀበት ጊዜ ይወሰናል:: ተጨማሪ የMRI ምርመራ ያስፈልጋል:: በዋነኘት የተወጠርዉን ህብለሰረሰር በማላቀቅ ያንን ተከትሎ የሚመጣዉን መዘዝ መቀነስ ነው:: አንዴ የደርሰዉን ጉዳት መመለስ ግን እጅግ አዳጋች ነው::

ለእያናዳንዱ ታካሚ የራሱ የህክምና እና የክትትል plan ያስፈልጋል:: ሁሉም አንድ አይነት ስላልሆነ::

References

1. Guggisberg, D., et al. (2004). Skin markers of occult spinal dysraphism in children: a review of 54 cases. Child's Nervous System

2. International Survey on the Management of Skin Stigmata and Suspected Tethered Cord. Child's Nervous System, Vol. 26

3. Kulkarni, A. V., et al. (2017). Evaluation and management of tethered cord syndrome in occult spinal dysraphism. Child's Nervous System.

ቸር ያሰማን!
ዶ/ር ሱራፌል መኮንን: ረዳት ፕሮፌሰር
የህፃናት አንጎል ህብለሰረሰር ነርቭ ቀዶ ጥገና ሰብ ስፔሺያሊስት

Telegram: t.me/HakimEthio

09/06/2026

በዘመናዊው Mindray Resona i9 አልትራሳውንድ ማሽን የጉበት ስብ ክምችት እና የጉበት ጠባሳ ደረጃ ለማወቅ የኢላስቶግራፊ ምርመራ እናደርጋለን፡፡

ተክለሃይማኖት ጠቅላላ ሆስፒታል
ከልብ በመነጨ እንክብካቤ ወደ ላቀ ምዕራፍ!

With advanced Mindray Resona i9 ultrasound machine, we perform liver fat accumulation and liver fibrosis stages examination.

Teklehaimanot General Hospital
Healing with Heart to Tertiary Excellence!

Photos from Hakim's post 09/06/2026

አንዲት ነፍሰጡር እናት የቅድመ-ወሊድ ቫይታሚኖችን (Prenatal Vitamins) እንዴት መውሰድ አለባት?

ዶ/ር ዳዊት መስፍን (የማህፀን እና ፅንስ ስፔሻሊስት)
www.tiktok.com/

1. የቅድመ-ወሊድ ቫይታሚን መቼ መጀመር አለበት?

👍ከእርግዝና በፊት፦ የተሻለው ጊዜ እርግዝና ከመከሰቱ ከ2 እስከ 3 ወራት በፊት መጀመር ነው። ይህም በፅንሱ ላይ የሚከሰቱ የነርቭ እና የአከርካሪ አጥንት ችግሮችን (Neural tube defects) ለመከላከል ይረዳል።

👍 እርግዝና እንደታወቀ፦ አስቀድመው ካልጀመሩ፣ እርግዝና መኖሩን ካወቁበት የመጀመሪያ ቀን ጀምሮ መውሰድ መጀመር አለብዎት።

👍 በእርግዝና ወቅት ሁሉ፦ ቫይታሚኖቹን በእርግዝና ዘመን ሁሉ እስከ መውለጃ ቀን ድረስ መቀጠል ያስፈልጋል።

2. ምን ዓይነት ቅድመ-ወሊድ ቫይታሚን(prenatal) መውሰድ አለባት? ( የምትወስጂውን prenatal ጀርባውን ተመልከቺ)

💊Folic Acid ፦ በቀን 400 mcg
💊 Iron ፦ 27 mg :- ለደም ማነስ መከላከያ እና ለፅንሱ እድገት
💊 Calcium 1000-1300mg , Vitamin D 600IU(15mcg) ፦ ለፅንሱ አጥንት እና ጥርስ ጥንካሬ።
💊 Iodine ፦ 150mcg - ለፅንሱ የአንጎል እድገት
💊 Omega 3 DHA - 200-300mcg - ለፅንሱ የአንጎል እድገት

3. Prenatal እንዴት መውሰድ ይገባል?

👉 በየቀኑ፦ እስከ ወሊድ ድረስ
👉 ከምግብ ጋር፦ ሆድ ላይ መጠነኛ መረበሽ እንዳያመጣ
👉 ከበቂ ውሃ ጋር

4. ቀላል የጎንዮሽ ጉዳቶች ሲያጋጥሙ ምን ማድረግ አለብን?

🫴 የማቅለሽለሽ ስሜት
ቫይታሚኑን ማታ ከመተኛት በፊት መውሰድ ወይም ከቀላል ምግብ ጋር መውሰድ ማቅለሽለሽን ይቀንሳል

🫴 የሆድ ድርቀት
ብዙ ውሃ መጠጣት፣ ፋይበር ያላቸውን ምግቦች (አትክልትና ፍራፍሬ) ማዘውተር እና መጠነኛ እንቅስቃሴ ማድረግ።

🫴 የቫይታሚኑን አይነት መቀየር

🫴 የሚወሰድበትን ሰዓት መቀየር

Photos from Hakim's post 09/06/2026

የጨቅላ ህፃናት ቢጫ መሆን + የካካ መንጣት ‼️

የጨቅላ ህፃናት አይን እና ገላ ቢጫ መሆን በተለያየ ከቀላል እስከ ከባድ የጤና እክል ምክንያቶች ሊከሰት ይችላል።

ነገር ግን በዋነኝነት አሳሳቢ የሚሆነው
👉 በተወለዱ 24ሰአት ውስጥ ከተከሰተ
👉 ቢጫነቱ ከ 2 ሳምንት በላይ ከቆየ
👉 ቢጫነቱ ከጭንቅላት ጀምሮ ወደታች ከእንብርት አልፎ ከሄደ
👉 የካካ ነጭ መሆን ወይም የሽንት መጥቆር ካለ
👉 ተያይዞ ማስመለስ ፣ የክብደት አለመጨመር ፣ የእንቅልፍ መዛባት እና የመሳሰሉት የህመም ምልክቶች ካሉ ነው።

ስለዚህ እነዚህን ምልክቶች ካስተዋሉ በጊዜ የልጅዎን ሀኪም ማማከር እና የደም ምርመራ እንዲሁም እንዳስፈላጊነቱ የሆድ አልትራሳውንድ ምርመራ በማስመርመር መንስኤው ምን እንደሆነ መለየት እና ተገቢውን ህክምና ህፃኑ እንዲያገኝ ማድረግ ያስፈልጋል።

ይህን ርዕስ ያነሳውበት ምክንያት አንዳንድ ጊዜ ከአፈጣጠር ጋር በተያያዘ ከጉበት ወደ ትንሹ አንጀት ክፍል የሀሞት ፈሳሽን የሚያስተልፈው ቱቦ መዘጋት ወይም አለመኖር ሊከሰት ይችላል። በዋነኝነት የሚታየው ምልክት የአይን እና ገላ ቢጫ መሆን እና ከዚሁ ጋር በተያያዘ በምስሉ ዳይፐሩ ላይ እንደሚታየው የካካ ቀለሙ ነጣ ማለት ነው።

ይህ የጤና እክል ደግሞ በመጀመሪያ 3 ወር እድሜያቸው በጊዜ ታውቆ በቀዶ ህክምና ተፈጥሮአዊ ችግሩ ካልታከመ ጉበትን በጊዜ ሂደት በመጉዳት ከጥቅም ውጪ ያደርጋል። ይህ ሁኔታ ከተከሰተ ደግሞ በጉበት ንቅለ ተከላ ቀዶ ህክምና ካልታከመ የህፃኑን ህይወት በአሳዛኝ ሁኔታ ይቀጥፋል።

ስለዚህ ወላጆት በተለምዶ አባባል የጨቅላ ህፃናት ቢጫ መሆን በፀሀይ መሞቅ ብቻ በጊዜ ሂደት በራሱ ይጠፋል ብላችሁ እንዳትዘናጉ እና ጥንቃቄ እንዳታደርጉ እንዲሁም ተያይዞ የጠቀስኳቸውን ምልክቶች ካስተዋላቹ በጊዜ ወደ ጤና ተቋም በመሄድ ልጃችሁን ማስመርመር ያስፈልጋቹሀል።

ማጣቀሻ
1. Coran Pediatric Surgery 7th Edition
2. American pediatric surgical Association Guideline

ዶ/ር ዮናታን ከተማ: በቅዱስ ጳውሎስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የህፃናት ቀዶ ህክምና ሬዚደንት ሀኪም

ሰላምና ጤና በያላችሁበት ይሁን!

ለበለጠ ማብራሪያ 👇👇👇 መጎብኘት ይችላሉ።
YouTube - https://youtube.com/?si=4k6s0RROG_lVCA3u

Photos from Hakim's post 09/06/2026

Pharmacy graduates of Adama Science and Technology University, 2026.

Medical Laboratory graduates of Wolaita S**o University, 2026.

Medical Laboratory graduates of Jimma University, 2026.

Public Health Officer graduates of Bonga University, 2026.

Nursing graduates of Bule Hora University, 2026.

Photos from Hakim's post 08/06/2026

የትልቁ አንጀት ካንሰር በወጣቶች ላይ እየጨመረ በመምጣቱ መከላከል ስለምንችላቸው ነገሮች ግንዛቤ ለማስጨበጥ የቀረበ ፅሁፍ

1- የመጀመሪያ ደረጃ መከላከል (ህመም ከመከሰቱ በፊት)

• ፋይበር የሚያበዛ ምግብ ይመገቡ፡ አትክልት፣ ፍራፍሬ፣ ያልተፈተጉ ጥራጥሬ እህሎችን ይመገቡ።

• ቀይ ሥጋ እና የተቀነባበረ ሥጋ ይቀንሱ፡ በሳምንት ሁለት ጊዜ በሚበልጥ አይመገቡ።

• አልኮል ይቀንሱ

• ጥሩ የክብደት ማስተካከያ ያድርጉ፡፡ ከመጠን በላይ ክብደት እና የቦርጭ መጨመር ተጋላጭነት ይጨምራል።

• አካላዊ እንቅስቃሴ ያድርጉ፡ ቢያንስ በሳምንት 150 ደቂቃ መንቀሳቀስ (ለምሳሌ በፈጣን መራመድ)።

• ሲጋራ አትጠቀሙ፡ ማጭስ ለሁሉም ካንሰር አይነት ያጋልጣል።

2. ሁለተኛ ደረጃ መከላከል (ቀደም ሲል ማወቅ እና ማከም)

© ይህ በጣም ወሳኝ ነው። አንጄት ካንሰር ብዙውን ጊዜ ከፖሊፕ /polyp የሚጀምር ሲሆን ይህን ፖሊፕ ወደ ካንሰር ከመቀየሩ በፊት በማግኘት ማስወገድ ይቻላል።

© በጊዜው ቅድመ-ምርመራ (screening)፡ ለአማካይ ተጋላጭነት ያለው ሰው መመርመር በ 45 ዓመት ይጀምራል። ነገር ግን፥ ወጣት ከሆኑ እና የሚከተሉት ምልክቶች ካሉዎት መጠንቀቅ አለብዎት።

መጠንቀቅ ያለብዎትን ምልክቶች ማወቅ በሽታውን በእንጭጩ ለማግኘ ይቻላል።

• እነዚህን ምልክቶች ካጋጠሙዎት ወዲያውኑ ወደ ዶክተር ይሂዱ። "ወጣት ነኝ" ብሎ መዘናጋት አያስፈልግም።

1. በመፀዳጃ አካል ደም መምጣት (በሰገራ ውስጥ ደም መታየት፣ ጥቁር ሰገራ መሆን)።

2. በመፀዳዳት ልማድ ላይ የማይመለስ ለውጥ፡
· የረጅም ጊዜ ሆድ ድርቀት ወይም ተቅማጥ
· ሰገራ ቀስ በቀስ ከፊንጢጣ ሲወጣ ቀጭን መሆን።

3. የማያቋርጥ ሆድ ማቃጠል ወይም መንፋት።

4. ሰገራዎን ሙሉ በሙሉ እንደማታወጡ ስሜት።

5. ምክንያት የሌለው የሰውነት ክብደት መቀነስ።

6. ድካም እና የደም ማነስ (anemia)።

ለወጣቶች የአንጄት ካንሰር ተጋላጭነት የሚጨምሩ ምክንያቶች፡

© የቤተሰብ ታሪክ፡ በቤተሰብ (በወላጆች፣ ወንድማማቾች፣ ልጆች) ውስጥ የአንጀት ካንሰር ወይም ፖሊፕ ታሪክ ካለ።

© የአንጄት ቁስለት/ብግነት (IBD)፡ እንደ ulcerative colitis ወይም crohns በሽታ ካለዎት።

© የዘረመል ሁኔታዎች፡ እንደ ሊንች ሲንድሮም (HNPCC) ወይም ፋሚሊያል አዲኖማቶስ ፖሊፖሲስ (FAP)።

© የተሳሳተ ኑሮ ልማድ፡ ከላይ የተጠቀሱትን (ምግብ፣ እንቅስቃሴ፣ ክብደት)

መወሰድ ያለባቸው እርምጃዎች፡

1. ተጋላጭነትዎን ይገምግሙ፡ ከቤተሰብዎ ጋር ሆነው ስለ ካንሰር ታሪክ ይወያዩ።

2. የኑሮ ልማድዎን ይለውጡ፡ ፋይበር ይጨምሩ፣ እንቅስቃሴ ያድርጉ፣ የተቀነባበረ ሥጋ ይቀንሱ።

3. ምልክቶችን አትተዉ፡ ከላይ የተጠቀሱትን ምልክቶች ካጋጠሙዎት ወዲያውኑ ወደ ዶክተር ይሂዱ።

4. ስለ ቅድመ-ምርመራ (screening) ያስቡ፡ በጣም ከፍተኛ ተጋላጭ ከሆኑ (ለምሳሌ ከተወሰነ የዘረመል በሽታ ወይም ቤተሰብ ታሪክ) የሚጀምረውን የመመርመር ጊዜ ለምሳሌ በ30 ወይም 40 ዓመት ከዶክተርዎ ጋር ያወያዩ።

ዶ/ር ካሳሁን ምትኩ: ጠቅላላ ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት - ዓለም ሆስፒታል ቡታጅራ

‎telegram - https://t.me/Behaset

‎tik tok- https://www.tiktok.com/.kassahun?_t=ZM-8xXq1Uxnq2H&_r=1

‎face book
https://www.facebook.com/share/1Mpmhj7Uem/

‎linkedin -https://www.linkedin.com/in/kassahun-mitiku-b92373270

Photos from Hakim's post 08/06/2026

𝗣𝗲𝗹𝘃𝗶𝗰 𝗢𝗿𝗴𝗮𝗻 𝗣𝗿𝗼𝗹𝗮𝗽𝘀𝗲: 𝗜𝘀 𝗛𝘆𝘀𝘁𝗲𝗿𝗲𝗰𝘁𝗼𝗺𝘆 𝗔𝗹𝗼𝗻𝗲 𝗮 𝗧𝗿𝗲𝗮𝘁𝗺𝗲𝗻𝘁?

One of the most common misconceptions in pelvic organ prolapse surgery is the belief that removal of the uterus automatically cures prolapse.

The evidence tells a different story.

Pelvic organ prolapse is primarily a defect of pelvic support structures -the ligaments, fascia, and muscles that suspend the uterus and va**na. The uterus is often the victim of support failure, not the cause of the disease.

Therefore, removing the uterus alone does not correct the underlying support defect.

The American College of Obstetricians and Gynecologists (ACOG) states:

"Hysterectomy alone is not an acceptable treatment for uterova**nal prolapse because removal of the uterus does not correct inadequate apical support."

Similarly, the International Continence Society (ICS) emphasizes that restoration of apical va**nal support is a critical component of prolapse repair. Failure to address apical support is associated with recurrent prolapse and post-hysterectomy va**nal vault prolapse.

Scientific studies consistently demonstrate that women undergoing hysterectomy with concomitant apical suspension have significantly lower rates of recurrent prolapse and repeat surgery compared with hysterectomy alone.

Current evidence-based prolapse surgery focuses on restoring support through procedures such as:

✔ Uterosacral Ligament Suspension (USLS)

✔ Sacrospinous Ligament Fixation (SSLF)

✔ Sacrocolpopexy

✔ Uterine-preserving procedures (Hysteropexy)

The modern question is no longer:

"Should the uterus be removed?"

The real question is:

"How will apical support be restored?"

𝗞𝗲𝘆 𝗠𝗲𝘀𝘀𝗮𝗴𝗲 For Gynecologists

Pelvic organ prolapse is a support defect, not simply a uterine problem. Hysterectomy without apical suspension is not definitive prolapse surgery. Every prolapse procedure should include careful assessment and restoration of apical support to achieve durable long-term outcomes.

“Removing the uterus without restoring support is like replacing the roof of a house while ignoring its collapsing foundation. Successful prolapse surgery depends on restoring support, not simply removing an organ."

References

1. Pelvic Organ Prolapse. ACOG Practice Bulletin No. 214. Obstetrics & Gynecology. 2019;134(5):e126-e142

2. DeLancey JOL. Anatomic aspects of va**nal eversion after hysterectomy. Am J Obstet Gynecol. 1992;166(6 Pt 1):1717-1728

3. Cruikshank SH, Kovac SR. Randomized comparison of three surgical methods used at the time of va**nal hysterectomy. J Pelvic Surg. 1999;5:197-203.

4. Maher C, Feiner B, Baessler K, Schmid C, et al. Summary: 2021 International Consultation on Incontinence Evidence-Based Surgical Pathway for Pelvic Organ Prolapse. Journal of Clinical Medicine. 2022;11(20):6106. doi:10.3390/jcm11206106.

5. Haylen BT, Maher CF, Barber MD, Camargo SFM, Dandolu V, Digesu A, et al. An International Urogynecological Association (IUGA)/International Continence Society (ICS) Joint Report on the Terminology for Female Pelvic Organ Prolapse. International Urogynecology Journal. 2016;27(2):165-194

Dr. Finot Gashu: Obstetrician and Gynecologist, Urogynecology and RPS sub specialist

Telegram: t.me/HakimEthio

Photos from Hakim's post 08/06/2026

ማህፀን መንሸራተት ወይም መውጣት (Pelvic Organ Prolapse) እና የተሳሳቱ አመለካከቶች

የማህፀን መንሸራተት ወይም መውጣት ችግር ሲያጋጥም፣ ብቸኛው መፍትሔ ማህፀንን በቀዶ ጥገና ማስወገድ ብቻ ይመስላችኋል? ይህ ግን ፍጹም የተሳሳተ ግንዛቤ ነው!

የማህፀን መንሸራተት ወይም መውጣት የሚከሰተው ማህፀንን ደግፈው የያዙት የዳሌ ጡንቻዎችና ጅማቶች ሲላሉ ነው። ችግሩ ያለው ጡንቻዎቹ ላይ እንጂ ማህፀኑ ላይ አይደለም። ስለዚህ ማህፀንን ብቻውን ቆርጦ ማውጣት ችግሩን አይፈታውም!

ጥናቶች እንደሚያሳዩት ማህፀንን ብቻውን ማውጣት፦በመጀመሪያው አንድ ዓመት ውስጥ ችግሩ የመመለስ እድሉን Vault prolapse በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምራል።

ዶ/ር ፍኖት ጋሹ: የማህፀንና ፅንስ ስፔሻሊስት : ዩሮጋይነኮሎጅ ሰብስፔሻሊስት

Telegram: t.me/HakimEthio

08/06/2026

𝐎𝐩𝐭𝐢𝐜𝐚𝐥 𝐂𝐨𝐡𝐞𝐫𝐞𝐧𝐜𝐞 𝐓𝐨𝐦𝐨𝐠𝐫𝐚𝐩𝐡𝐲 (𝐎𝐂𝐓)

At 𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨 𝐓𝐄𝐁𝐈𝐁 𝐇𝐨𝐬𝐩𝐢𝐭𝐚𝐥, we provide 𝐎𝐩𝐭𝐢𝐜𝐚𝐥 𝐂𝐨𝐡𝐞𝐫𝐞𝐧𝐜𝐞 𝐓𝐨𝐦𝐨𝐠𝐫𝐚𝐩𝐡𝐲 (𝐎𝐂𝐓), an advanced, non-invasive imaging technology that uses light waves to generate highly detailed cross sectional images of the retina, optic nerve and anterior segment structures.

This enables our ophthalmologists to diagnose, monitor, and manage a wide range of eye conditions with precision without injections, surgery, or discomfort.

𝐎𝐩𝐭𝐢𝐜𝐚𝐥 𝐂𝐨𝐡𝐞𝐫𝐞𝐧𝐜𝐞 𝐓𝐨𝐦𝐨𝐠𝐫𝐚𝐩𝐡𝐲 (𝐎𝐂𝐓)
✅Glaucoma
✅Diabetic Retinopathy
✅Age-Related Macular Degeneration (AMD)
✅Macular Edema
✅Retinal Vein Occlusion
✅Macular Holes and Epiretinal Membranes
✅Optic Nerve Disorders
✅Ocular Surface Pathology
✅Unexplained Vision Loss

𝐖𝐡𝐲 𝐂𝐡𝐨𝐨𝐬𝐞 𝐎𝐂𝐓 𝐚𝐭 𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨 𝐓𝐄𝐁𝐈𝐁 𝐇𝐨𝐬𝐩𝐢𝐭𝐚𝐥?
🔹 High-resolution eye imaging
🔹 Fast, painless & non-invasive
🔹 Early detection of vision-threatening diseases
🔹 Precise disease monitoring
🔹 Experienced ophthalmologists
🔹 Comprehensive eye care under one roof

With experienced specialists and advanced diagnostic services, Ethio TEBIB Hospital is committed to delivering excellence in eye care.

📞 For more information or to schedule an appointment:
Call 0935402078 or 9000

📍 Visit us: Road to Kolfe, Masalemiya Sefereselam

Telegram Tiktok Facebook Instagram Youtube

🩺 𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨-𝐓𝐞𝐛𝐢𝐛 𝐇𝐨𝐬𝐩𝐢𝐭𝐚𝐥
We always strive for your health!

Want your practice to be the top-listed Clinic in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Website

Address

Addis Ababa