Green Community Development

Green  Community Development

Share

We all are a responsible citizens to contribute for our country development'', all the best of our k

It is a movement for the restoration of healthy living environment; and to contribute for sustainable Community/ City development.

14/08/2021

ጓዶች ስለ ጦርነት ብቻ ስናወራ ስለ ኢኮኖሚያችን እና ስለ ልማት ስራዎቻችን ማውራት አቆምን እኮ ። እስቲ
የከተማ ልማቶቻችን ላይ ካያችኋቸው ችግሮች ዋና ዋና የምትልቱን እያነሳን እንነጋገርባቸው?

07/07/2021

We don't accept a biased act of USA over Ethiopian politics !
*******************
We Ethiopians expect the USA to understand the very complicated political issues of Ethiopia before directly involving in Ethiopian politics through a continuous pressure on the government of Ethiopia, which is going through a difficult time with serious political instability.

It has been all too obvious that the USA has been and is continuing to be biased in its approach to current Ethiopian politics. As has often been the case in other contexts as well, USA stances and policies are based on a shallow and highly partisan understanding. A more balanced and fair approach would make the US policies much more effective in contributing to a solution to the current crisis and to bringing about sustainable peace, if at all that is the real interest of the USA.

Unfortunately, what has been observed is that you simply accept and endorse the arguments and narratives of TPLF remnants, their supporters and enablers who never worried about the interests of the the large majority of Ethiopians in the first place. This raises the question as to whether you care more about the loss of TPLF power than about the fate of the overwhelming majority of Ethiopians.

We Ethiopians don't give up to defend our rights and express fair demands !

Sisay Habtamu

11/08/2020

"በሽታውን ያላወቀ መሐድሂኒት አያገኝም"
🇧🇴 ከቅኝ ገዥዎች ግዜ ጀምሮ እንደ ዱላ ቅብብሎሽ አይነት ከ100ዓመታት በላይ የተፈፀመብን ለኢትዮጵያውያን የአንድነታችንና የስነልቦና ጥንካሬአችን መሰረት የሆነውን የክርስትና ሃይማኖታችንን አንድነት ለማዳከም የተሰራው ሚስጥራዊ ሴራ ሲገለጥ፧
===============
#ይነበብ እና #ሼር ይደረግ❓
================
♦️ በናዚው ሂትለር መልእክተኞች ጀርመን ኢትዮጵያን የመከፋፈልና ጠንካራው አቅማችንን የማዳከም ሴራ አፄ ሚኒሊክ በሰሩት ታሪካዊ ስህተት #በወለጋ መርዟን በመዝራት ዘረኝነትን አስጀመረችን ~> እንግሊዝ ዱላውን ተቀበለችና ቀጠለች~> ግብፅም ከእንግሊዝ ተቀብላ አስቀጠለች ~> ህወሃት እና ኦነግ እንደ እስትራቴጂ ተቀብለውት እርስ በእርስ ግጭት ታሪክ ትርክት በመጻፍ በሃሰት የታሪክ ትርክት ደም እያፋሰሱ የበደል ፅዋዎችን ጋቱን.. ~> የአባይ ውሃችን ቋሚ ጠላታችን ያደረጋት ግብፅ እርዳታዋ ተጨምሮበት ተላላኪዎቿን በመጠቀም የኢትዮጵያውያንን አንድነት የማተራመስ አለምአቀፋዊ ሴራ እስካሁንም ድረስ የኢትዮጵያውያን ህብረታችንና አንድነታችን መሠረቱን አናግቶብን እርስ በእርሳችን በመናጨት በሰላም እጦት እና በድህነት አረንቋ ውስጥ ተዘፍቀን፣ በስደትና በመከራ ስቃይ፣ ከቄያችን በመፈናቀል ፣ እርስ በእርሳችን በጥላቻ መርዞች እርጭት ደም በመፋሰስ የህዝባችን ያለአግባብ እልቂትና የንብረት ውድመትን እያስተናገድን ቤተ እምነቶቻችንን እያቃጠሉብን እና እየተራረድን የደረስንበት ደረጃ ላይ እንገኛለን።

✝️ በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ የሆንን ክርስቲያን ወገኖቼ ሆይ ከእንቅልፋችሁ ንቁ❓
👇 ልታውቁት የሚገባ እውነታው ይህ ነው።

በፌስቡክ በብዙ የብእር ስሞች የፌስቡክ ገፆችን ከፍተው ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ለመከፋፈል በጣም እየተሰራበት ነው። በተለይም አሁን ደግሞ ህዝቡን በእምነት ሳይቀር ለማከፋፈልና ህብረታችንን ለማዳከም በተለይም ክርስቲያኑን ማህበረሰብ ላይ ትኩረት ተደርጎ ክርስቲያኖች ሁሉ በክርስቶስ ኢየሱስ ምክንያት የተመሰረተ በክርስቶስ ኢየሱስ የከበረውና እኛን ለማዳን በፈሰሰው በኢየሱስ ደም ተመሠረተውን ክርስትናችን እና ክርስቲያናዊ አንድነታችንን ለማከፋፈል በተለያየ መልኩ የመለያየት መርዝ እየረጩ የኢትዮጵያን ህዝብ ህብረትና አንድነት በማከፋፈል ኢትዮጵያን ተበታትና አቅም እንዳይኖራት በማቀድ በማተራመሱ እየተሰራበት ነው።

💎 የኢትዮጵያን ህዝብ በእምነት አንድነት ሳይቀር ለማከፋፈል በሚደረገው ጥረት የምናውቀው ፣ የቤተክርስቲያን ምእመናንን በጎሳ ሃረግ ተለክቶ የቅዱስ ሲኖዶስ አንድነት የመለያየት ጥያቄ ጭምር የቤተክርስቲያን መምህራን ውስጥ ድረስ ዘልቆ በሴራ በመግባት ምእመናንን ለማከፋፈል በመጣር፣ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ቤተክርስቲያን ብቻ ሳይሆን በፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያን ጭምር በጎሳ የተከፋፈሉ የእምነት መሪዎችን በማሰልጠንና በየመንደሩ በስም የተለያዩ እና አንዱ ከሌላው ህብረት የሌላቸው የቤተ እምነቶችን ያለገደብ በማስፋፋት በሰፊው የተኬደበትና ክርስቲያኖች በአንድነት ሆነው ህብረት እንዳይኖራቸው በስፋት ተሰርቶበታል፣ አይተንማል ።

በክርስቶስ ኢየሱስ ምክንያት ክርስቲያን የሆኑ የክርስቲያኖችን ህብረት በሴራዊ ተልእኮ በሆነ የጥቅማ ጥቅም መንገዶችን በመዘርጋትና በማሳየት የጀርመን ናዚዎች መልእክተኞች የተጀመረው የቅኝ ገዥዎች ሰርገው በመግባት የጀመሩት መንገድ ክርስቲያኖችን ለያይተው በእምነት ተቋማት ልዩነት መንገድ በመበታተን ኢትዮጵያውያን ጥንካሬአቸው የነበረውን በክርስቲያናዊ ህብረት የነበረውን ቀደምትና ገራሚ የሆነ አንድነት በቀጣይነት እንዳይኖራቸው ታስቦበት የውጪ ተቀናቃኞች የነበሩት የዘመኑ የቅኝ ገዥዎች በጥልቀትና በስፋት በመስራት የእምነት ተቋማትን ሲያባዙልን አንዳንዶች ክርስቲያን ተብዬዎች በአፍቅሮተ ንዋይና በጥቅም በመጠለፍ የእምነት ተቋማትን እንደ ትናንሽ ቢዝነሶች አይነት ቢዝነስ ሆነው እንዲመሰረቱና እንዲለያዩ ጭምር በማድረግ በጉዳዪ ላይ ለረጅም አመታት ሲሰራበት ቆይቷል። የገዛ ወገኖቻችን የሆኑት ወንድሞቻችንም ለዚህ ተልእኮ አንደኛ ተባባሪዎች ናቸው።

በዚህም የኢትዮጵያ ክርስቲያኖችን ህብረትና አቅማቸውን በታትኖ በህብረት እንዳይቆሙ የማዳከም ሴራ እናንተ ከምትገምቱት በላይ በፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች መካከል ሳይቀር በጥልቀትና በስፋት ተኪዶ ተሰርቶበታል ።

♦️ዛሬ ላይ በተለይ በፕሮቴስታንት እምነት ቤተክርስቲያን አንድነትና ህብረት የሚባል ነገር የለም ። ከኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች በላይ የሆኑ የፕሮቴስታንት እምነት ተቋማቶች በእየመንደሩ እንደ ቢዝነስ ተቋማት በተለያየ ስም ተመስርተው እንደአሸን ፈልተው ህዝባችንን አንድነቱን በመበታተን ህሊናውን እያደናገሩትና እየነገዱበት በልዩነት መድረክ ትውልዱን የሚያደናግሩት ብዙ ሰባኪያን ትውልድ አደንዛዦች አሉ።

♦️በዳግማዊ ንጉስ ሚንሊክ ዘመነ መንግስት በጀርመን ሚሽነሪዎች አማካኝነት በወለጋ የተጀመረው የኢትዮጵያ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን የክርስቲያኖች አንድነት (ጥንካሬአችንን) ከማዳከም የተጀመረው ሴራዊ ተልእኮ አልፎ ተርፎ ከኢ/ኦ/ቤ/ክ የተለየ የክርስትና አስተምሮሆት የፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያንን ከመፍጠሩ ባሻገር ዛሬ ላይ ፕሮቴስታንት እምነት እራሱ ሳይቀር በብዙ ቁጥሮች የተከፋፈሉና የተባዙ ህብረት የሌላቸው ሆን ተብሎ በሰው ልጆች ሴራና ጥቅመኝነት የተፈጠሩ የክርስትና እምነት ተቋማት ሴክተር ናቸው።

ዛሬ ላይ ያለው የኢትዮጵያን ክርስቲያኖች የማጥቃትና የማዳከም ተልእኮ የክርስቲያኖችን አንገት እስከ ማቅላት የደረሰ፣ የክርስቲያኖችን ንብረትና ሃብታቸውን የማዳከም፣ እንዲሁም ቤተክርስቲያንን በማቃጠል የካህናቱን አንገት ማቅላት ደረጃ ላይ ደርሷል። ይህንንም የእርኩስ መንፈስና የመናፍስት ሴራዊ ተልእኮ በእኛው ዘመን ሲከወንናፐየሰው ልጆችን ደም ሲያስገብር፣ የሰውን ደም እንደ ፅዋ ሲጎነጩት በቪዲዮ ሳይቀር ተቀርጾ እንድናይ እየተደረገ፣ አንገት ሲቀላ ቪዲዮ እየተቀረጸ፣ ፎቶ እያነሱ በመልቀቅና በማሸበር ጠላቶቻችን እና ተላላኪዎች ሲያደርጉት አሳይተውናል፣
በጆሮአችን ሰምተናል፣ በአይናችንም ጭምር በመንደራችን ሲደረግ አይተናል ።

ለዚህ ሁሉ እኩይ ተልእኮዎች ምክንያቶቻቸው የኢትዮጵያ ህዝብን ሰላምና መረጋጋት እንዳይኖራቸውና ወደ እድገትና ብልፅግና ጎዳና ውስጥ ለመግባት ሰላምና መረጋጋት ኖሯቸው በትጋትና በእውቀት እንዲሁም በልህቀት ሆነን ሐገራችንን ከድህነት አረንቋ እንዳናወጣት፣ እኩልነት፣ ፍትህ እና ዲሞክራሲያዊ ስርዓት የሰፈነባት ሃገር እንዳትኖረን ታስቦበት ሌትተቀን በትጋት የሚሰሩበት ያለ ሁኔታ መሆኑን ያላገናዘባችሁ ቢሆንም ጥቂቶች ሳንሆን ብዙዎች ጉዳዩን ካሰብንበት ለብዙ አመታት የተሰራባቸውን ኢትዮጵያን የማዳከም ያላሰለሱት ሴራዎችን ጠንቅቀን እንረዳዋለን ብዬ እገምታለሁ ።

ይህም ሁሉ ይሁን እንጂ ጉዳዩ የገባንና የተረዳንው ጥቂትም ብንሆን የሴረኞቹን ሴራዎችና ተልእኮዎች በአግባቡ ባለመረዳታችን ምክንያት ለደረሰብን ማህበረሰባዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳቶች ከዛሬ ጀምረን እንኳ ቢሆን ሴራዎችን እና ሴረኞችን ተልእኮአቸውን ጠንቅቀን በመረዳት እኛ የኢትዮጵያን ሰላም እና ትንሳኤ ፈላጊዎች በቁጥር በእጅጉ የላቅን ብንሆንም የጥቂት ሴረኞችን የፖለቲካ አሻጥርን ጠንቅቀን ባለመረዳታችን ምክንያት የብዙዎቻችንን አላማ የሆነውን የኢትዮጵያንና የህዝቦቿን ትንሳኤ ምኞትና ያላሰለሰ ጥረቶቻችንና ትግላችንን ጥቂቶች በሆኑት የፖለቲካ ሴረኞችን በመዳከም የኢትዮጵያ ህዝብን መከራቸውን እየገፉ እንዲኖሩ ፣ የደከመች ኢትዮጵያ እንድትፈጠር ሳናውቅ ተባብረናቸዋል።

የኢትዮጵያ ምድር ያፈራቻቸው የእናት ጡት ነካሾች በሆኑት የኢትዮጵያውያንን በአንድ ሃገራቸው እጣ ፈንታ መልካሙን በጋራ ከማሰብ ይልቅ በተጻራሪ መልኩ የመለያየትና ኢትዮጵያን የማዳከም ሴራዊ ተልእኮ ያነገቡና ለአፍራሽ ተልእኮዋቸው ሌትተቀን የሚተጉ የሴራ ፖለቲካ ተዋናይ የሆኑት ሃገር አፍራሽ ተልእኮ ያነገቡ እራስ ወዳዶችና በህዝብ ስም የሚነግዱ የጠላት ተላላኪ የሆኑት የእናት ጡት ነካሽ ፖለቲከኞቿ በሚፈጥሩት የማያቋርጡ የሴራ አይነቶች የኢትዮጵያ ህዝብን ከድጡ ወደ ማጡ እየገባን ያለንበት የፖለቲካ ሂደት ሁኔታ ተፈጥሯል።

የኢትዮጵያ የሴራ ፖለቲከኞች ከዲሞክራሲያዊ ስርዓት እና ከፍትህ ናፋቂ ፖለቲከኞች ጋር ሊቀራረብ የማይችልና በተቃራኒው የሆነውን የሴራዊ ፖለቲካ ሽኩቻ ውስጥ በመግባታቸው ምክንያት ኢትዮጵያ በዙሪያዋ ላሉ የውጪ ጠላቶቿን መመከት እንዳትችል እና ደካማ ሃገር እንድትሆን ሆድ አደር ባንዳዎች ጥቂቶች ቢሆኑም እንደ ብዙሃን ህዝብ ጥያቄ ያነገቡ በመምሰልና በውክልና መልክ ሆነው በሶሻል ሜዲያ አንዱ እንደብዙ በተለያዪ ስሞች በመባዛት እና በመተወን ጭምር ከፍተኛ የሆነ ሴራዊ የሆነ ህዝብን የማለያየት ስራዎችን በቅብብሎሽ እየሰሩበት መሆኑን ልታውቁት ይገባል።

ከዚህም እውነታ ባሻገር ሃገር ወዳድ የሆናችሁ የኢትዮጵያ ዜጎችና የፖለቲካው ተሳታፊዎች የሆናችሁ ሁሉ ጥቃቅን የልዩነቶቻችንን ማካበድና የስልጣን መቆጣጠር ጥማችንን እና እርስ በእርስ መቀናናታችንን ፣ መጣጣላችንን እና የታጋዮችን እግር ጠልፈን መጣል፣ ከኋላ ቆመን እንዳይሮጡ ጨርቃቸውን ወደኋላ መጎተትና መጓተት ትተን በህዝብ እና በሃገር ፍቅር ፍፁም የሆናችሁ ታጋዮች ሁሉ የሰፊውን ህዝብ ጥቅም በማስቀደም ብቻ ለትግል ቆማችሁ ሃገራችን ኢትዮጵያን በእርስ በእርስ ጦርነት እንደ ሶርያ እና አንደ የመን እንዳትሆንብን ህዝብን በፍቅር ለማገልገል በሰላማዊና ከሴራ ተልእኮ በፀዳ እና በቀናው መንገድ ብቻ የፖለቲካውን ስልጣን የመቆጣጠር የሰላማዊ ትግል ሂደት ውድድር የሰላማዊ ትግል ጎዳና ገብታችሁ በአግባቡ ለመጓዝና ተወዳዳሪ በመሆን ለቀጣዪ ሃገር አቀፋዊ ምርጫ ለገዥው መንግስት ብቁ ተወዳዳሪ ፓርቲ በመሆን ለመቅረብ ብትዘጋጁ እንደሚሻል ልመክር እወዳለሁ።

እመቤት ሲሳይ ሀብታሙ
ከ አዲስ አበባ
ነሃሴ 5 ቀን 2012

02/06/2020

* * ❗️
======================
። ምክንያቱም የአባይ ወንዝ ምንጩ ከመሐል ሐገር ኢትዮጵያ ነው ፣ የአባይ ግድብ ከ2003 ዓም ጀምሮ እስከዛሬም ድረስ እየተገነባ ያለው ከእያንዳንዳችን ኢትዮጵያውያን ኪስ በወጣ የገንዘብ መዋጮ ብቻ ነው። በመሆኑም የአባይ ግድብ ላይ የአብዛኛው ኢትዬጵያዊ ገንዘብ በግድም ይሁን በውድ ኢንቨስት ተደርጎበታል።

♦️ከአባይ ግድብ የግንባታው ለወደፊት በሚሰጠን ጥቅሞች በኢትዮጵያ ህዝብ ህልውና ላይ በድፍረት እንደሚደራደሩበት አድርጌ እቆጥረዋለሁ ።

♦️አንዳንድ ፖለቲከኞች/የፖለተካ አክቲቪስቶች/ድርጅቶች/ግለሰቦች በአባይ ወንዝ ግድብ አላማና ሂደት ዙሪያ እና ግድቡ ወደፊት ለኢትዬጵያ በሚሰጠው አገልግሎት ላይ በተመለከተ ገንዘብ እንደበሉበት ሰምተናል።
የፖለቲካ ፓርቲ፣ የፖለቲካ አክቲቪስት ወይም ፖለቲከኛ እንዲሁም ግለሰብ ቢኖሩ እነርሱ እንዲሁም ከኢትዮጵያ ህዝብ ፍላጎቶች በተፃራሪ መልኩ በተቃርኖ እንደቆሙ እቆጥረዋለሁ ።

ስለዚህ የአባይ ጉዳይ የእያንዳንዱ የኢትይጵያ ህዝብ አሻራው ያረፈበት የህልውና እና የሐገር ሉአላዊነት ጉዳይ መሆኑን: ከግብፅና ከሱዳን ጋር ተደራዳሪ ቡድኖች/ግለሰቦች ጠንቅቃችሁ ልታውቁት ይገባል እላችኋለሁ ።

እ/ት ሲሳይ ሐብታሙ
ከአዲስ አበባ ም/ወ 28

Want your school to be the top-listed School/college in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Telephone

Website

Address

Yeka Sub City
Addis Ababa