Sinework Taye
Public Figure
06/09/2025
በዋናው ነገር ላይ ማተኮር!
አንድን እጅግ በጥበብ የላቀን ሰው አገኘሁትና ባለችኝ የጋዜጠኝነት ሙያ ተጠቅሜ መጠየቅ የምችለውን ያህል ለመጠየቅ ሞከርኩ፡፡
ጠቢቡ - “ና ጠጋ በል … ጥያቄ ልትጠይቀኝ እንደፈለግህ ታስታውቃለህ” አለኝ፣ የልቤን ፍላጎት ገምቶ፡፡
እኔ - “ጊዜ ካለህ” አልኩት፡፡
ጠቢቡ (ልብን በሚሰርቅ ፈገግታ) - “ለማወቅ ለሚፈልጉ ሰዎች ሁሉ ጊዜ አለኝ” ብሎ መለሰልኝ፡፡
ይህ ጥበበኛ እንዴት ለሰው ሁሉ ጊዜ ሊኖረው ቻለ? እያልኩ ሳወጣና ሳወርድ በፈገግታና በትእግስት ይጠብቀኝ ነበር፡፡
እኔ፡- “ስለ ሰው ፍጥረት ከሚያስገርሙህ ነገሮች መካከል ጥቂቱን ንገረኝ” አልኩት፡፡
ጠቢቡ -
• “ልጆች ሳሉ መሰልቸታቸውና ትልቅ ለመሆን መሮጣቸው … ካደጉ በኋላ ደግሞ ልጅ መስሎ ለመታየት መሯሯጣቸው ያስገርመኛል …
• ገንዘብ ለማካበት ጤንነታቸውን ማጣታቸው … ጤናቸውን ለመመለስ ደግሞ እንደገና ያንኑ ገንዘብ ማፍሰሳቸው ያስደንቀኛል …
• ስለ ነገ በመጨነቅ ዛሬን ለመኖር አለመቻላቸውና ከዛሬም ሆነ ከነገ ሳይሆኑ መንከራተታቸው ያስገርመኛል …
• ልክ እንደማይሞት ሰው መኖራቸውና ልክ እንዳልኖረ ሰው ተጽእኖ ቢስ ሆነው መሞታቸው ያስገርመኛል፡፡
ይህን ጠቢብ ዝም ብለው ሌሎች ሃሳቦች እንደሚጨምር እየተሰማኝ በማቋረጥ፣ “ሌላ ጥያቄ ልጠይቅህ?” አልኩት፡፡
ጠቢቡ፡- ደስ በሚያሰኝ ፈገግታ ፈቃደኝነቱን ገለጠልኝ፡፡
እኔ፡- “የሰው ልጅ ሁሉ አባት ብትሆን ለሰው ልጆች እንዲያደርጉ ከምትመክራቸው ነገሮች መካከል ጥቂቶቹን ንገረኝ” አልኩት፡፡
ጠቢቡ (ረዥም ጺሙን ዳበስ ዳበስ በማድረግ ካሰበ በኋላ)፡-
• ማንም ሰው እንዲወዳቸው ማስገደድ እንደማይችሉ፣ ነገር ግን ማድረግ የሚችሉት የሚወደድ ማንነትን ማሳደግ ብቻ እንደሆነ እንዲያወቁ እመክራቸው ነበር፡፡
• መልካም ማንነትንና የተመሰከረለት ማህበራዊ ሕይወት ለመገንባት አመታት እንደሚፈጅ፣ ለማፍረስ ግን አንድ ደቂቃ እንደሚፈጅ እንዲያውቁ አስተምራቸው ነበር፡፡
• የሕይወታችቸውን አቅጣጫ የሚወስነው ያላቸው ንብረትና ሃብት ሳይሆን በሕይወታቸው ያስጠጓቸው የወዳጆች አይነት እንደሆነ እንዲገነዘቡ አሳስባቸው ነበር፡፡
• ታላላቅ ሕልሞችን ለማለምና ከግባቸው ለማድረስ የሚያስፈልገው ታላቅ ሰው መሆን ሳይሆን ከግብ ለመድረስ የቆረጠ ማንነት እንደሆነ እንዲያውቁ የተቻለኝን አደርግ ነበር፡፡
• ሃብታም ሰው ብዙ ገንዘብና ቁሳቁስ ያለው ሰው ሳይሆን የሚያስፈልገውን ነገር ያወቀ ሰው እንደሆነ እንዲያውቁልኝ እጥር ነበር፡፡
• ራሳቸውን ከሌላው ጋር ማነጻጸርና ማወዳደር እንደማይገባቸውና ከእነርሱ የሚያንስ ሰው እንዳለ ሁሉ የሚበልጥም ሰው የመኖሩን እውነታ እንዲቀበሉት አስረዳቸው ነበር፡፡
• አመለካከታቸውን መቆጣጠር እንዳለባቸው አለዚያ አመለካከታቸው እነሱን እንደሚቆጣጠራቸው እንዲማሩ እሞክር ነበር፡፡
,• እጅግ በጣም የሚወዷቸውና የሚያከብሯቸው ነገር ግን ያንን በቅጡ ለመግለጽ የማይሆንላቸው ብዙ ወዳጆች እንዳሏቸው አስረዳቸው ነበር፡፡
• እውነተኛ ጓደኛ ማግኘት እጅግ ከባድ እንደሆነ፣ ያንን ያገኘ ግን የሕይወቱን አብዛኛውን ችግሩን እንዳቃለለ እንዲያውቁ እመክራቸው ነበር፡፡
• የቅርብ ወዳጆቻቸውን ለማቁሰል ሰከንድ እንደሚበቃ ለመፈወስ ግን አመታት እንደሚፈጅ እንዲገባቸው እጣጣር ነበር፡፡
• ሰዎችን ለመቆጣጠር በመሞከር እንደሚያጧቸው፣ ምርጫቸውን በማክበር ነጻነታቸውን በመስጠት ግን ለዘለቄታው ወዳጆች እንደሚያደርጓቸው እንዲገነዘቡ ለማድረግ እሞክር ነበር፡፡
• የውስጥ ሰላም ለማግኘት ከሰዎች ይቅርታን ማግኘት ብቻ ሳይሆን ራሳቸውንም ይቅር ማለት እንደሚገባቸው እንዲያስታውሱ አሳስባቸው ነበር፡፡
• ከመናገር በሚቆጠቡበት ነገር ላይ ጌታ፣ በልቅነት ለሚናገሩት ንግግር ደግሞ ባሪያ ሆነው እንደሚኖሩ አሳውቃቸው ነበር፡፡
• እውነተኛ ደስታ የውሳኔ ጉዳይ እንደሆነ፣ በማንነታቸውና ባላቸው ነገር ደስተኛ መሆን፣ አለዚያ በቅንአትና በፉክክር ወጥመድ ውስጥ እንደሚገቡ አስገነዝባቸው ነበር፡፡
• በአጭሩ በዋናው የሕይወት ነገር ላይ ያተኮረ ዝንባሌ ቢኖራቸው እመክራቸዋለሁ፡፡
የተባረከ ምሽት ተመኘን 🙏
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊
06/09/2025
ሕይወት እንደ አይሮፕላን በረራ ነች!
አንዳንድ ጊዜ ሕይወት እንደ አይሮፕላን በረራ ያደርጋታል፡፡ የአይሮፕላን በረራ አደገኛው፣ ለመከስከስ ተጋላጭ የሆነውና እጅግ ትልቅ ጥንቃቄ የሚስፈልገው ጊዜ ሁለት ነው፡፡
1) የመነሻው (የመጀመሪያ) ጊዜ፣
2) የማረፊያው (የመጨረሻው) ጊዜ፡፡
ማንኛውንም ግንኙነት፣ ንግድ፣ ስራ፣ ራእይ . . . ስትጀምሩ በጥንቃቄ አስባችሁበት ጀምሩ፡፡ በችኮላ፣ በመላ-ምትና በግድ የለሽነት የተጀመረ ነገር ለመከስከስ አደጋ የተጋለጠ ነው፡፡ ትክክለኛ ነገር እየጀመርን እንኳን በጥንቃቄ ካላደረግነው ከአደጋው አናመልጥም፡፡
ማንኛውም ግንኙነት፣ ንግድ፣ ስራ፣ ራእይ . . . ወደማብቂያው እንደደረሰ ሲገባንና “ማሳረፍ” ስንፈልግም ታላቅ ጥንቃቄ ይጠይቃል፡፡ በስሜታዊነትና በችኮላ ነገሮችን ከማቋረጥ መጠንቀቅንና ስናቋርጠው ደግሞ በጥበብ ማድረግን ይጠይቃል፡፡ አሳርፉት እንጂ አትከስክሱት!
የተባረከ ምሽት ተመኘን🙏
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ😊
06/09/2025
አንዴ ከሄዱ የማይመለሱ 4 ነገሮች!
ምንጩ ያልታወቀ አንድ ማስታወሻ፡-
በሕይወታችሁ እንደገና ለመመለስ የሚያስቸግሯችሁ አራት ነገሮች፡-
“እድል” - አንዴ ካመለጣችሁ በኋላ!
“ቃል” - አንዴ ከአንደበታችሁ ከወጣ በኋላ!
“ጊዜ” - አንዴ ሳትጠቀሙበት ካለፈ በኋላ!
“አመኔታ” - አንዴ ከጎደለ በኋላ ለመመለስ አስቸጋሪ ነው፡፡
ሲብራራ . . .
1. “እድል” - በአጋጣሚም ሆነ ጠንክራችሁ በመስራታችሁ የመጣን እድል መለየት፣ ማክበርና በተገቢው ሁኔታ መጠቀም፡፡
2. “ቃል” - ሁኔታዎች ሲገፋፏችሁም ሆነ እንዲሁ ስለለመደባችሁ በቀላሉ የምትናገሯቸውን ሰው ጎጂ ንግግሮች በሚገባ ማሰብና ራስን መግታት፡፡
3. “ጊዜ” - በሆነ ባልሆነ የምታባክኑትና አሁን ባላችሁ እድሜ ማድረግ የሚገባችሁን ነገር ባለማድረግ የምታባክኑትን ጊዜ በጥንቃቄ መያዝ
4. “አመኔታ” - ሰዎች ሲያምኗችሁና ራሳቸውንም ሆነ ነገሮቻቸው በእናንተ ላይ ሲጥሉ እምነት ከማጉደል መጠበቅ፡፡
በሉ እንግዲህ፣ ያለፈው አልፏል፣ የባከነው ባክኗል፡፡ የተራረፈውን እንሰባስበውና ሕይወትን እንደገና በአዲስ መልክ እንጀምር፡፡
የተባረከ ምሽት ተመኘን🙏
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ😊
05/08/2025
ሕይወትን ቀለል ብናደርጋት ኖሮ!
ካነበብኩት ትንሽ ሰንበት ያለ አባባል ትዝ አለኝ . . .
• የተወለድነው በሌሎች ሰዎች እርዳታ ነው፡፡
• ስማችንን የተቀበልነው ሌሎች ሰዎች ባወጡልን መሰረት ነው፡፡
• የገቢ ምንጫችን የሚመጣው ከሌሎች ሰዎች ነው፡፡
• ክብርና እውቅና የሚሰጡን ሌሎች ሰዎች ናቸው፡፡
• ገላችንን ለመጀመሪያ ጊዜ ያጠቡን ሌሎች ሰዎች ናቸው፣ ለመጨረሻ ጊዜ የሚያጥቡንም ሌሎች ሰዎች ናቸው፡፡
• ከዚህ አለም ስንሰናበት ቤታችንና ንብረታችን በሌሎች ሰዎች ይወሰዳል፡፡
• እጃችንን ይዘው በመደገፍ መራመድ ያስለመዱን ሌሎች ሰዎች ናቸው፣ በመጨረሻም እጃችንን ይዘው በመደገፍ የሚያራምዱን ሌሎች ሰዎች ናቸው፡፡
• በመወለዳችን ምክንያት በደስታ የደገሱና የበሉት ሌሎች ሰዎች፣ ስንሞትም በኃዘን የሚደግሱና የቀብር ስርአታችን የሚከናወነው በሌሎች ሰዎች ነው፡፡
ይህ ሁሉ እውነታ እያለ “ነኝ” እና “አለኝ” በምንለው ነገር የምንመካበት ጉዳይ አይገባኝም፡፡ እስቲ ያወሳሰብናትን ሕይወትን ቀለል እናድርጋትና ለመከባበርና ለመዋደድ ቅድሚያን በመስጠት እንኑር፡፡
ቆንጆ ምሽት ተመኘን🙏
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ😊
3 Psychology Traps!
16/07/2025
ህይወቴ ባዶ ናት፣ ትርጉም የላትም፣ እንደበረሀ ደርቃለች ብለህ ተስፋ ልትቆርጥ ስትል አንጀት የሚያርስ መልስ የሚሰጥህ ፈጣሪህ አለ።
ወዳጄ የዘገየ ይመስልሀል እንጂ እሱን የሚቀድመው የለም!ያሰባችሁት ሁሉ (ከክፋት በስተቀር) እንዲሳካ ምኞቴ ነው!
አክባሪያችሁ ስነወርቅ ታዬ
12/07/2025
09/07/2025
ተለውጠሀል!
ሰዎች አንተን መስደብ ወይ በነገር መተንኮስ ከጀመሩ አድገሀል ማለት ነው፤ እህቴ በዙሪያሽ ያሉ ሰዎች ክፉ እየተናገሩ አላስቀምጥ ካሉሽ ተለውጠሻል ማለት ነው።
ምክንያቱም አርፎ የተቀመጠን ምንም የማይሰራን ሰው ማንም ዞር ብሎ አያየውም፤ የሚለፋን ራሱን ለማሻሻል የሚጥርን ሰው ግን የሚተቸው የሚሰድበው ብዙ ነው። ዴል ካርኒጌ "የሞተን ውሻ ማንም እንደማይደበድበው እወቅ" ይላል።
የተለየ ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
Click here to claim your Sponsored Listing.