Abu Ruffa

Abu Ruffa

Share

☆━━━━━━━━ ʏᵃⁿⁱ ʙᵘᵘˡᵃ
ᴋᵃˢᵃˡ sᵃᵈᵘʰ
ᴀⁿ
ᴛᵃⁿⁱᵐ
ᴀᵇˡᵉ ʷᵃᵃ
ɴᵘᵐᵘᵏ ᴅᵉᵉˡᵘʰ ᴀⁿ ━━━━━━━☆ Afar state Afarlands daahuli

Photos from Abu Ruffa's post 27/01/2024

👉 Ethiopian Federal police

ልዩ ልዩ ሐሰተኛ ሰነዶችንና ዘዴዎችን በመጠቀም ህብረተሰቡን ሲያጭበረብሩና ሲያታልሉ የነበሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
አዲስ አበባ፣ ጥር 18 ቀን 2016 ዓ.ም (ኢፌፖሚ)፡-ልዩ ልዩ ሐሰተኛ ሰነዶችንና ዘዴዎችን በመጠቀም ህብረተሰቡን ሲያጭበረብሩና ሲያታልሉ የነበሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ።

ተጠርጣሪዎቹ በመንግስት ባለስልጣናት ስም እየተጠቀሙ ''እነ እከሌን እናውቃለን፤ ጉዳያችሁን እንጨርስላችኋለን'' እያሉ እያጭበረብሩና እያታለሉ ከህብረተሰቡ ከፍተኛ ገንዘብ የሚቀበሉ በመሆናቸው ፖሊስ ከነ-ኤግዚብቱ በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሚገኝ ገልጿል።

ከዚህም ባለፈ ተጠርጣሪዎቹ ባለሃብት ሳይሆኑ ባለሃብትና ከፍተኛ ገንዘብ እንዳላቸው ለማስመሰል በርካታ የአሜሪካን ዶላር በሳምሶናይት ይዘው ፎቶግራፍ በመነሳት እራሳቸውን እያሳዩ፣ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከላከያ ሠራዊት አባል ሳይሆኑ አባልና ኮሎኔል ነን እያሉ እንዲሁም የብሔሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት መሥሪያ ቤት የስራ ባልደረባ ሳይሆኑ ባልደረባና ደኅንነት ነን እያሉ በሐሰተኛ መታወቂያ ህብረተሰቡን ሲያጭበረብሩና ሲያታልሉ እንደ ቆዩ ፖሊስ አሰታውቋል።

ፖሊስ ምርመራውን በማስፋት ከፍርድ ቤት የመበርበሪያ ትዕዛዝ አውጥቶ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 አካባቢ በሚገኘው የተጠርጣሪ ሞቱማ ደለሳ ቦሮቃ መኖሪያ ቤት ውስጥ ባደረገው ብርበራ ለወንጀል ተግባር ማስፈፀሚያ የሚገለገልበት 90 ሺህ ብር፣ አንድ ሽጉጥ TISASTOTLYE/ ከ24 መሠል ጥይቶች እና ከ2 ካዝና ጋር እንዲሁም አይፎንና ሳምሰንግ ሞባይል፣ አንድ አፒድ ላፕቶፕ እና ሦስት ፍላሾች መያዙን ፖሊስ ጨምሮ ገልጿል።

እራሱን ኮሎኔል እና ደኅንነት እንደሆነ በማስመሰል የሚያታልለው ፋህሚ አብዲ ዩሱፍ እንደሆነም ታውቋል።

ህብረተሰቡ በወንጀል መከላከል ውስጥ እያደረገ ያለውን ተሳትፎ የበለጠ በማጠናከር በተመሳሳይ የወንጀል ተግባር የተሰማሩ ግለሰቦችንና ቡድኖችን በማጋለጥ አሳልፎ ለፖሊስ እንዲሰጥ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ጥሪውን ያቀርባል።

በመጨረሻም በነዚህ ሰዎች ተታለልኩ ወይም ተጭበረበርኩ የሚል ማንኛውም ሰው የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ ቢሮ ቀርቦ ሪፖርት እንዲያደርግ ተቋሙ አስታውቋል።

27/01/2024

Meqe xaagu taham

Photos from Abu Ruffa's post 26/01/2024

Sissik xaagu

Tahak gubal fooca akak tablen num, tawak ta saaqat yangudilb1 num, tonnah, qunxafoqol 1 num qideh kudem warsan.
Tama num edde garaye marak, elle kaa geennan ikkel, sissikuk lowsis gubat kaa haytaanam esserra.

raceena👉Deedal mawaara

19/01/2024

ጄነራል_አህመድ_መሀመድ_ባቤ😪 በ1970 ዓ.ም ጭቆናን በመቃወም የአፋር ህዝብ ነፃነት ለትጥቅ ትግል ወደ ጫካ ከገቡት የአፋር አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት ግንባር (አርዱፍ ኡጉጉሞ) ታጋዮች ጋር በመቀላቀል ከ30 ዓመታት በላይ የሠራዊቱ ዘመቻ መሪ በመሆን የመሩና #በ1995 ዓ.ም ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር የተደረሰውን ስምምነት ተከትሎ #በ1996 ዓ.ም ሰላማዊ ትግልን በመቀላቀል በዞን 3 አዋሽ ፋንቲ አሌ ወረዳ የተለያዩ ፅ/ቤቶችን በኃላፊነት በመገልገል ላይ የነበሩ ጀግና ለሰው ትሁትና ሩህሩህ የነበሩ
ጥር 9/ 2016 ዓ.ም ድንገት በመታመማቸው አድስ አበባ በህክምና ላይ እያለ ወደ ማይቀረው ጉዞ ጥሎን ሄዷል አና አላህ ጀነትን ይወፍቀው እያልኩኝ ለቤተሰቦቻቸውና መላው ወዳጅ ዘመዶቻቸውን መጽናናትን እመኛለሁ

ኢናሊላህ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን😭

16/01/2024

Kudrak tan gaba taamah Baxsale innal magcag gurusen kokkobi wagiitay👁

የሚገርም እጅ ስራ የተሰራው ልዩ እና ድንቅ ዲዛይን የተሰራ ተሽከርካሪ ተመልከቱት👁

16/01/2024

ኢራን በሶሪያ በእስራኤል የገደለውን የኢራን ጄኔራል ለመበቀል ትላንት ምሽት በኢራቅና ኩርዲስታን በሚገኘው የሞሳድ ቢሮ ላይ የሚሳኤል ጥቃት መፈጸም ታውቆዋል

15/01/2024

• አሪፍ ፀባይ አለዉ የምትለዉ ሰዉ ለብቻዉ ሲሆን ትክክለኛ ነገር ይሰራል?

• የካፌ አስተናጋጅ፣ ፅዳት የሚሰሩ ሰዎችን፣ ነዳጅ የሚቀዱ ሰዎችን እንዴት ነዉ የሚያነጋግራቸዉ?

• ሰዉ ገንዘቡንና ሰአቱን የሚጠቀምበት መንገድ የሰዉየዉን ስብእና በትክክል ይናገራል፡፡

አባቴ ሳምንቱን ሙሉ በስራ ተወጥሮ ነዉ የሚያሳልፈዉ፡፡ እቤት ሲመጣ እንኳን አመሻሽቶ፣ ከስራ ደክሞት ነበር፡፡

ማታ የቀረዉን ትንሽ ሰአት ለኛ 'እንደአባት' ለእናታችን ደግሞ 'እንደባል' የሚገባዉን ሁሉ ይረዳን፣ ያግዘን ነበር፡፡

በሱ እድሜ ያሉ ብዙ ሰዎች ልክ እቤት ሲገቡ ቲቪ ላይ ተጥደዉ እንደሚያመሹት ሳይሆን እኛን የቤት ስራ በማገዝ፣ እናቴን ደግሞ ከጎኗ ሆኖ ጅርባዋን ሲያሽ፣ እግሬን ቆረጠመኝ ስትለዉ እግሯን ቁጭ ብሎ በቫዝሊን ሲያስታምም ነበር ልጅነቴን የማስታዉሰዉ፡፡

እንደአባቴ አይነት 'የገባበትን ሃላፊነት በትክክል አዉቆ' ቤተሰቡን ብር ከመወርወር ባለፈ ተንከባክቦና ደግፎ አሳድጎናል፡፡

ለዚህ ነዉ መልካም የሆኑትን እንቁላሎች ከተበላሹት ለመለየት ዉሃ ዉስጥ የሚከተተዉ፡፡

የችግርና የመከራ ወቅት ሲጀመር የምትወደዉ ሰዉ ማንነት በትክክል እየጠራ፣ እየታየና እየተገለጠ ይመጣል፡፡

08/01/2024

😥ሼህ አብዱ ያሲንን በመግደል የተጠረጠረው መሀመድ ሽኩር አበባው ያለበትን የሚያውቅ ጥቆማ በመስጠት እንዲተባበር የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪ አቀረበ
**************

የመኖሪያ አድራሻው ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 የሆነውና ሟቹ ያሳድጉት የነበረው መሀመድ ሽኩር አበባው ሼህ አብዲ ያሲንን በመግደል ወንጀል ተጠርጥሮ ይፈለጋል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ የወንጀሉን ፈፃሚ በቁጥጥር ስር ለማዋል የክትትልና የምርመራ ቡድኖችን አዋቅሮ ክትትሉን አጠናክሮ ቀጥሏል።

ስለሆነም መሀመድ ሽኩር አበባው ያለበትን የሚያውቅም ሆነ ማንኛውም መረጃ ያለው በስልክ ቁጥር 011-1-11-01-11 ወይም በነፃ ስልክ ቁጥር 991 መረጃ በመስጠት እንዲተባበር የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል።

በወንጀል የተጠረጠረ ግለሠብን መደበቅም ሆነ እንዲያመልጥ መተባበር የሕግ ተጠያቂነት የሚያስከትል መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ በሼህ አብዱ ሞት የተሠማውን ሀዘን ገለጾ፤ ለቤተሰቦቻቸው እና ለእምነቱ ተከታዮች መፅናናትን ተመኝቷል።

07/01/2024
01/01/2024

Gabuuti, Djibouti 🇩🇯????

"Rabak masaaxanay raaqak saaxan"
QM, kah iyyanna immay,
Yabuutí tooboko taway abta gexso Qafar manó Djiboutil esseroh addat culsele.

Baatilih qado loqo nek qiden tooboko magaq gee kal, takke gaday, dansi kee farcataay, dokla macak faxximteeh?

Sinam isi tooboko hinnay, dubuk adam-baxiinó sabbatah luk sugen gaditté barnaamij elle soolissa baadal Qafar rabal gad kee dokla Qafar macah abtaah?

Yalli nee missoysay ikkal mano nek matan!!

17/12/2023

ወጣቱን አግተው 10 ሚሊዮን ብር የጠየቁ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

ታኅሣሥ 7/2016 (አዲስ ዋልታ) የአዲስ አበባ ፖሊስ ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎትና ከፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ ጋር ባደረጉት ጠንካራ ክትትል ወጣቱን አግተው 10 ሚሊዮን ብር የጠየቁ ሁለት ወንጀል ፈፃሚዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉ ተገለጸ።

የእገታ ወንጀል የተፈፀመበት ወጣት ልዑል መብራቱ ፀጋዬ በማህበራዊ መገናኛ አውታር አማካኝነት ባንቴ ይድረስን የተባለውን ግለሰብ ይተዋወቃል፡፡

ትውውቃቸው አንድ ወር ከሞላ በኋላ ባንቴ ይድረስ የተባለው ወንጀል ፈፃሚ የወንድሜ ጓደኛ ቤት ላሳይህ በማለት ወጣቱን ታኅሣሥ 2/2016 ዓ.ም ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ቁሊቲ መንደር 4 አካባቢ ይዞት ከሄደ በኋላ ከግብረ አበሩ ልዑል ጫላ ጋር በመሆን ያግቱታል፡፡

ወንጀል ፈፃሚዎች እጅግ ዘግናኝ ፊልሞችን እና ፎቶግራፎችን ለወላጆቹ በመላክ 10 ሚሊዮን ብር ካልተከፈላቸው ወጣቱን እንደሚገድሉት የማስፈራሪያ መልእክት ይልካሉ፡፡

የእገታ ወንጀል እንደተፈፀመ ሪፖርት የደረሰው የአዲስ አበባ ፖሊስ ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎትና ከፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ ጋር ባደረጉት ጠንካራ ክትትል ወንጀሉን በተፈፀመ በአራተኛው ቀን ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ስር በማዋል ወጣቱን ከእገታው ነፃ ማውጣት ተችሏል፡፡

ሁለቱ ግለሰቦች ወንጀሉን ለመፈፀም በ5 ሺሕ ብር ቤት መከራየታቸውንና የታጋቹ ወጣት ወላጅ አባት ውጭ ሀገር ይኖራሉ በሚል መረጃ ወንጀል መፈፀማቸውን በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የወንጀልና ትራፊክ አደጋ ምርመራ ኃላፊ ምክትል ኮማንደር ዘሪሁን ተፈራ ማሳወቃቸውን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

Want your public figure to be the top-listed Public Figure in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Telephone

Address

Afar State Dahuli
Addis Ababa