TumaComputer

TumaComputer

Share

www.Tuma Computer .com

17/09/2024

በኢትዮጵያ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪነት ረጅም ዓመታትን ያስቆጠሩትና ታዋቂው ፖለቲከኛ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡

ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ በርካታ ፓርቲዎችን በሥሩ የያዘውን መድረክ ፓርቲ ሊቀመንበር የነበሩ ሲሆን በሀገሪቱ የሰላማዊ ፖለቲካ ትግል ውስጥ ስማቸው በጉልህ ከሚጠቀሱ የፖለቲካ አመራሮች አንዱ ነበሩ፡፡
ከፖለቲከኛነታቸው ባለፈ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮ ሳይንስ ተመራማሪም ነበሩ፡፡
ፕሮፌሰር በየነ የደርግ መንግስት ተገርስሶ ኢህአዴግ መንበሩን ከተቆጣጠረ በኋላ በሽግግር መንግስት ወቅት በትምህርት ሚኒስቴር ምክትል ሚኒስትርም ነበሩ፡፡ የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ኢሶዴፓ) ሊቀመንበርና እንዲሁም የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር የነበሩት በየነ ጴጥሮስ የሞቱት ረዘም ላለ ጊዜ በህክምና ሲረዱ ቆይተው መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡
ፕሮፌሰር በየነ በኢትዮጵያ ገንቢ የፖለቲካ ባህል ለመፍጠር ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረከቱ የሰላማዊ የፖለቲካ ትግል ምልክት እንደነበሩ አክለው የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፣ ያቆዩት ውርስ እና ቅርስ ፀንቶ እንዲቀጥል ነፍሳቸውም በሰላም እንድታርፍም ተመኝተዋል፡፡
ኢቢኤስ ቴሌቪዥንም በፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ህልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን እየገለጸ ለቤተሰቦቻቸውና ወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን ይመኛል፡፡

29/03/2024
15/03/2024

External HardDisk 1Tb

12/10/2021

WellCome This page

11/10/2021

WellCome to This Tuma computer page

Want your business to be the top-listed Computer & Electronics Service in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Website

Address

Addis Ababa