Seble tegu
ሰው ለምሆን ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው
ተለቀቀ
🙏
14/07/2023
ፍቅር 💞
08/07/2023
ደራሲ ኢንጅነር ዘገየ የታባለበት ያለ ምክንያት አይደለም ። ጠበቅ ያሉ ሃሳቦችን ። ወጣ ያሉ እይታዎችን የሚመነጩበት መፅሓፍቶችን ጀባ ብሎናል ።
1 እውነት አለኝ
2 ህፃንኤል
3 ደግሞ የአዳም እጅ አሻራ ይሰኛል ።
ከላይ የተቆረጠው ከአዳም እጅ አሻራ ነው ።
ስለ መፅሐፋ ተናግሬ ፡ አንብቤው አልጠግብም ።
08/07/2023
በርግጥ እምነት አንድ ነገር ነው ። የማይከፈል ። የማይታበል ። የማይሸጥ የማይለወጥ ። የማይፋቅ ። የማይጣመም ። የማይቃና ።
ይህ በእንዲህ እንዳለ አባት እና ልጅ በኩርሲ ወንበር ላይ ተቀምጠው ቡና ይጠጣሉ ።
ልጅ ፡ " አባየ "
አባት ፡" አቤት ዉዷ ልጀ "
ልጅ ፡ " አንድ ሲደመር አንድ ስንት ነው ?"
አባት ፡" አንድ ነው ።"
ልጅ ፡" ኧረ አባ ሁለት ነው ። "
አባት :" እሱ የቁጥር ህግ ነው "
ልጅ ትንሽ እንደማኩረፍ ብላ " እሽ አንድ ሲደመር ሁለትስ? "
አባት ፡" አሁንም አንድ ነው ።"
ልጅ ፡ " ኧረ አባ ውሃ ነው ። ከአንድ ኦክስጅን ከሁለት ሃይድሮጅን ስለሚሰራ ! "
አባት ፡" እሱም የኬሚስትሪ ህግ ነው ፡፡ "
ልጅ ግራ ተጋብታ ፡ " እሽ ያንተ ህግ የማነው ?"
አባት ፡" የህጎች ሁሉ የበላይ ህግ ።"
ልጅ ፡" እኮ ከወዴት ነው ?"
አባት ፡" ከፈጣሪ ነው ልጀ ።" ብሎ ይመልሳል ።
የህጎች ሁሉ የበላይ ህግ ፈጣሪን መፍራት ነው ። ሌሎች ሰዎች ለራሳቸው እንዲመች የቆጠሯቸው መሰናክሎች ናቸው ። የፈጣሪውን ህግ የሚያከብር አይሰርቅም ። አይታበይም ። አይገልም ። የሰው ሚስት አይደፍርም ።።።። ገፅ 123
አንድ ወቅት በወርሃ ፆም አንድ መለኩሴ ሲጓዙ አንድ ጠብደል መሃይም ዛፍ ተደግፎ ወተት ሲጠጣ ይደርሱበታል ። ቄሱ ይቀርቡት እና
" አንተ ምን ትጠጣለህ ?" ብለው ይጠይቁታል ።
ጥርሱን ፈገግ አድርጎ " ወተት ነው ። ይጠጣሉ አባቴ ?" ይላቸዋል ። የሚጠጣበትን እያሳያቸው ።
" በስመ አብ ፡ በወርሃ ፆም ምነው ምነው ፃ መንፈሰ ርኩስ " ብለው ከቅላቸው ፀበል ረጭተውት ፡ ከፀበሉ አጠጥተውት ይሄዳሉ ።
ከፊቱ ዘወር ሲሉ " አልቻልሁም አባቴ " ብሎ ብልቃጥ ወረወረባቸው ።
ቄሱ ደርሰው ሲያዩት መርዝ ጠጥቶ ነበር የወደቀ ። በዚህ ጊዜ ፈጥነው ካስጣሉት ወተት ግተውት ይጠብቁት ጀመር ።
ትንሽ ቆይቶ ልጅ ይነቃል ።
" ለምን በፆሙ ወተት አጠጡኝ ?" ሲል ጠየቃቸው ።
ቄሱም " አንደኛ ፀበሉን በመርዙ ስላረከስኸው ።ሁለተኛ ደግሞ ሳትፈልግ አማኝ ከምቶን ፈልገህ አህዛብ ብቶን ይሻላል ። በል በምታምነው ኑር ። " ብለውት ይሄዳሉ ።
ገፅ 39
ሁሉም ሰው የራሱ መንገድ አለው ። ነገር ግን ሌሎችን በመንገዱ ላይ እየረገጠ መራመድ ከጀመረ በራሱ መንገድ ሳይሆን በሌሎች ላይ እየተረማመደ ነው ።
ከአዳም ኦጅ አሻራ ለቅምሻ የተቀነጨበ ።
ዘገየ ታዴ ( engineer )
@@@
17/04/2023
07/12/2022
ራስህን አክብር!
የሰው ልጅ ሁሉ ትልቁ ህልሙ ተፈላጊነቱን ማሳየት ነው፤ በሰዎች መፈለግ እንደ ምግብ የሚርበን እንደ ውሀ የሚጠማን ነገር ነው።
ታዲያ ተፈላጊ ለመሆን ምን እናድርግ? ለራሳችን ትልቅ ቦታ መስጠትና የሰጠነውን ቦታ ወደ ተግባር ለመለወጥ ሁሌም መጣር፤ ለራስህ ያልሰጠኸውን ቦታ ሌሎች አይሰጡህም! ራስህን ስታከብር የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ ሁሉም ያከብርሀል።
========================
Click here to claim your Sponsored Listing.