Christ Embassy Church - Summit 72

Christ Embassy Church - Summit 72

Share

ለህይወቶ ትርጉም ይሰጣል! giving your life a meaning

30/05/2026

RHAPSODY OF REALITIES
(Amharic) 🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Saturday 30, May 2026
ቅዳሜ፣ ግንቦት 22 ቀን 2018 ዓ.ም.

📜 ስኬት፣ ድል እና ጭማሪ
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

📖 “በፈሳሽ ውኃ ዳር እንደ ተተከለች [እንደተንከባከቧት]፥ ፍሬዋን በየጊዜዋ እንደምትሰጥ፥ ቅጠልዋም እንደማይረግፍ ወይም እንደማይጠወልግ ዛፍ ይሆናል፤ የሚሠራውም ሁሉ ይከናወንለታል [ወደ ሙሉ ብስለትም ይደርሳል]።” (መዝሙር 1:3 በአምፕሊፋይድ ትርጉም )።

👤 ፓስተር ክሪስ
════════
እግዚአብሔር ውድቀትን ፈጽሞ አይፈጥርም። አንድ ሰው ከክርስቶስ ጋር ሲቀላቀል፣ ለስኬት፣ ለድል እና ለጭማሪ ብቻ ተብሎ ወደተዘጋጀ ሕይወት ይገባል። በእናንተ ውስጥ ያለው የእግዚአብሔር ተፈጥሮ ብቃትን፣ እድገትን እና ታላቅነትን ያመጣል። ይህ የአዲሱ ፍጥረት ሕይወት እውነታ ነው።

እኔ ወደዚህ ግንዛቤ የገባሁት በጣም ቀደም ብዬ ነው። ዘጠኝ ዓመት ሳይሞላኝ ነው ዳግም የተወለድኩት፣ ብዙም ሳይቆይ ወንጌልን መስበክ ጀመርኩ። ጓደኞቼን ወደ ክርስቶስ መማረክ ጀመርኩ፤ ከአሥር ዓመቴ በኋላ ብዙም ሳይቆይ፣ ኅብረት ጀመርኩ። በአሥራ አምስት ዓመቴ ቀድሞውኑ ትላልቅ የወንጌል ስርጭቶችን አከናውን ነበር። ይህንን መንገድ ለረጅም ጊዜ ስለድሄኩበት፣ ያለ ምንም ጥርጥር ቃሉ እንደሚሠራ ለማወቅ ችያለሁ።

እግዚአብሔር በመንገዱን ሲያሳችሁና አእምሯችሁ በእርሱ ላይ ሲጸና፣ በእርሱ ስለታመናችሁ ፍጹም ሰላም እንደሚጠብቃችሁ ቃሉ ያውጃል። ያ ሰላም የብልጽግና ሰላም ነው፣ ይህም ያለማቋረጥ ወደፊት የሚገሰግስ ሕይወት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ በክርስቶስ ስላለው ሰው ሲናገርም፦ “የሚሠራውም ሁሉ ይከናወንለታል” ይላል።

በቃሉ የሚኖር ሰው ዕጣ ፈንታው ይህ ነው፤ በመክፈቻ ጥቅሳችን ላይ እንዳየነው። የክፉዎችን ምክር የማይከተል ሰው የተባረከ ነው። አንዳንዶች አምላክ የሌላቸው ጓደኞች፣ ዘመዶች ወይም ጎረቤቶች ውሳኔዎቻቸውን እንዲቀርጹ ይፈቅዳሉ፤ በፍጹም ይህ መሆን የለበትም!

የተባረከ ሰው በእግዚአብሔር ቃል ደስ ይለዋል፣ ቀንም ሌሊትም ያሰላስለዋል። ለቃሉ ትኩረት ይሰጣል፣ በቃሉም ሕይወቱን ይቀርጸዋል። ውጤቱም አስደናቂ ነው፦ በውኃ ፈሳሾች አጠገብ እንደተተከለች፣ ፍሬዋን በየጊዜዋ እንደምትሰጥ፣ ቅጠሏም እንደማይጠወልግ ዛፍ ይሆናል፤ ይህ ማለት በእናንተ ዘንድ ውድቀት የለም ማለት ነው። ምን ዓይነት ሕይወት ነው!

ራሳችሁን ለቃሉ ስትሰጡ፣ ሕይወት ወደላይ እና ወደፊት ብቻ ለሚደረግ የአንድ አቅጣጫ ጉዞ ያዘጋጃችኋል ። ቃሉ ዘር ነው፣ ማሰላሰል ደግሞ ቃሉ ስኬትን፣ ድልን እና ክብርን ብቻ እንድታስቡ አእምሯችሁን እንዲገዛ በመንፈሳችሁ ውስጥ ስር እንዲሰድ ያደርገዋል። ሕይወታችሁ የቃሉ መገለጫ ይሆናል፣ ይህም መልካም ስኬት እንዲኖራችሁ ያደርጋል (ኢያሱ 1:8)። ሃሌሉያ።

ጸሎት
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ውድ አባት ሆይ፣ በክርስቶስ ስለሰጠኸኝ የማያልቅ የስኬት ሕይወት አመሰግንሃለሁ። ቃልህ በእኔ ውስጥ በኃይል ይሠራል፣ ብቃትን፣ ብልጽግናን እና ድልን ያመጣል፤ ስኬትን በስኬት ላይ እደረርባለሁ። በየቀኑ ቃልህን አስማለሁ፣ ቃልህን እናገራለሁ፣ እንዲሁም በቃሉ ብርሃን እመላለሳለሁ፤ በኢየሱስ ስም። አሜን።

ለተጨማሪ ጥናት
├─ኢያሱ 1:8 3
├─ዮሐንስ 1:2
├─ምሳሌ 4:20-22

━━━━//━━━

29/05/2026

RHAPSODY OF REALITIES
(Amharic) 🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Friday 29, May 2026
አርብ፣ ግንቦት 21 ቀን 2018 ዓ.ም.

📜ጸጋ፣ ምሕረት እና ሰላም
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

📖“ከእግዚአብሔር አብና ከአብ ልጅ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ምሕረት ሰላምም በእውነትና በፍቅር ከእኛ ጋር ይሆናሉ።” (2 ዮሐንስ 1:3)።

👤 ፓስተር ክሪስ
════════
በብዙዎቹ የሐዋርያት መልእክቶች ውስጥ፣ መንፈስ ቅዱስ ኃይለኛ በረከትን (ቡራኬን) ያጎላል። ለምሳሌ፣ በጳውሎስ አንዳንድ ጽሑፎች ውስጥ “ጸጋ፣ ምሕረትና ሰላም” በሚሉ ቃላት ይጀምራል፤ በ1ኛ ጢሞቴዎስ 1:2 ላይ “ከአባታችን ከእግዚአብሔር ከጌታችንም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ምሕረት ሰላምም ይሁን” እንደሚለው። ይህንኑ በረከት ለጢሞቴዎስ በጻፈው በሁለተኛው መልእክቱ እና ለቲቶም በጻፈው ላይ ደግሞታል።

ሐዋርያው ዮሐንስም ይህንኑ ይደግመዋል፦ “ጸጋና ምሕረት ሰላምም ከእግዚአብሔር አብና ከጌታ ከኢየሱስ ክርስቶስ ከእናንተ ጋር ይሆናሉ” (2 ዮሐንስ 1:3)። ሐዋርያት ለምን ሁልጊዜ ጸጋን፣ ምሕረትንና ሰላምን ያውጁ ነበር? ምክንያቱም በክርስቲያናዊ ሕይወታችሁ ውስጥ ያላቸው ፋይዳ እጅግ የላቀ ስለሆነ ነው።

መፅሐፈ ቅዱሳት በእግዚአብሔር ፊት ጸጋን ስላገኙ ወንዶችንና ሴቶችን ይገልጣሉ። ለምሳሌ፣ ኖኅ፣ በምድር ላይ ፍርድ በታወጀበት ጊዜ እንኳ በጌታ ፊት ጸጋን አግኝቷል። ዘፍጥረት 6:8 “ኖኅ ግን በእግዚአብሔር ፊት ጸጋን አገኘ” ይለናል። ጸጋው ለጥበቃና ለድል አበቃው። ይህም ጸጋ ሰውን ሲያገኘው፣ ምሕረት እንደሚከተለው ያሳያል።
ጸጋ፣ ምሕረትና ሰላም አብረው ይሠራሉ። ሮሜ 5:1-2 ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን ሰላም በቆምንበት ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ጋር ያገናኘዋል፦ “እንግዲህ በእምነት ከጸደቅን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ከእግዚአብሔር ጋር ሰላም አለን፤ በእርሱም ደግሞ ወደ ቆምንበት ወደዚህ ጸጋ በእምነት መግባትን አግኝተናል።”

በእግዚአብሔር ፊት ጸጋን ስታገኙ፣ እርሱ ለእናንተ መሐሪ ይሆናል። ዕብራውያን 4:16 “እንግዲህ ምሕረትን እንድንቀበል በሚያስፈልገንም ጊዜ የሚረዳንን ጸጋ እንድናገኝ ወደ ጸጋው ዙፋን በድፍረት እንቅረብ” ይላል። ጸጋ ማለት ለእናንተ የተሰጠ መለኮታዊ ሞገስ ነው። በሰው ሕይወት ላይ የሚሠራ የእግዚአብሔር ሥራ ነው።

በብሉይ ኪዳን “ቼን” የሚለው የዕብራይስጥ ቃል ትርጉሙ የእግዚአብሔር ጸጋ ሞገስ ማለት ነው። በዚያ ጸጋ፣ በዚያ መለኮታዊ ሞገስ አማካኝነት፣ ስኬታማ እንድትሆኑ በሕይወታችሁ ላይ ተጽዕኖውን ያሳርፋል። ጸጋው በአእምሯችሁ ላይ ይሠራል፣ ትክክለኛውን ነገር እንድታስቡ ይረዳችኋል። ልባችሁን ያነሳሳል፣ ከተፈጥሯዊ ችሎታችሁ ወይም ከሰው ልጅ ብልሃት በላይ ትክክለኛ ውሳኔዎችን እንድታደርጉ ይመራችኋል።

ጸጋ ይሸፍናችኋል፣ ይከልላችኋል፣ ይጠብቃችኋል፣ እንዲሁም ከከባድ ስህተቶች ይጠብቃችኋል። በዚህ ንቃተ-ህሊና ተመላለሱ። ለሰው ልጅ ብልሃትና ችሎታ ብቻ አልተተዋችሁም፤ የሰማይ ተጽዕኖ በሕይወታችሁ ላይ ነው፣ እርምጃችሁን ይመራል እንዲሁም ከተፈጥሮ አቅም በላይ የሆኑ ውጤቶችን እንድታመጡ ያደርጋችኋል። እግዚአብሔር በክርስቶስ የሰጣችሁ ሕይወት ይህ ነው።

ጸሎት
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ውድ አባት ሆይ፣ በሕይወቴ ውስጥ ለሚሠራው ስለ ተትረፈረፈ ጸጋህ፣ ምሕረትህና ሰላምህ አመሰግንሃለሁ። መለኮታዊ ተጽዕኖህ ሐሳቤን፣ ውሳኔዬንና ተግባሬን ይመራል፤ በድል እንድጸና በማድረግ በስኬትና በጽድቅ መንገድ ይመራኛል፤ በኢየሱስ ስም። አሜን።

ለተጨማሪ ጥናት
├─ዕብራውያን 4:16
├─2 ጴጥሮስ 3:18
├─2 ቆሮንቶስ 9:8

━━━━//━━━

28/05/2026

RHAPSODY OF REALITIES
(Amharic) 🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Thursday 28, May 2026
ሐሙስ፣ ግንቦት 20 ቀን 2018 ዓ.ም.

📜 በመለኮታዊ ኃይሉ የተጠበቃችሁ
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

📖 “እግዚአብሔር የኃይልና የፍቅር ራስንም የመግዛት መንፈስ እንጂ የፍርሃት መንፈስ አልሰጠንምና” (2 ጢሞቴዎስ 1:7)።

👤 ፓስተር ክሪስ
════════
የመክፈቻ ጥቅሳችን ፍርሃት የመንፈሳዊ ማንነታችሁ ወይም የተፈጥሯችሁ አካል እንዳልሆነ በግልጽ ያሳያል። ስለዚህ ፍርሃት ሊቆጣጠራችሁ ሲሞክር ከተሰማችሁ፣ እምቢ በሉት (አትቀበሉት)። መፅሐፍ ቅዱስን ስታጠኑ፣ በጥንት ዘመን ጌታ ለማንኛውም ሰው በተገለጠበት ጊዜ ሁሉ፣ ብዙ ጊዜ ፣ የመጀመሪያ ቃላቱ በኢሳይያስ 41:10፣ በኢያሱ 1:9 እና በራዕይ 1:17 ላይ እንደምታዩት “አትፍሩ” የሚል ነበር።

በዓለም ላይ ምንም ዓይነት ነገር ቢከሰት ፍርሃትን እንድንቃወም ያዘናል። እናንተ በሕይወታችሁ ላይ የእግዚአብሔር ማኅተም አለባችሁ፤ ይህም ከሚጎዳ ወይም ከሚያስር ከማንኛውም ነገር የሚለያችሁ መለኮታዊ አዋጅ ነው። እናንተ ለእግዚአብሔር የተለያችሁ ናችሁ። “በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ” (ዮሐንስ 3:16) የሚለውን የጌታን ቃል አስታውሱ።

ምክንያቱም የእርሱ የጥበቃ ማኅተም በእናንተ ላይ ስለሆነ ነው (ኤፌሶን 1:13)። ሁልጊዜም በድፍረት እንዲህ ብላችሁ አውጁ፦ “እግዚአብሔር ብርሃኔና መድኃኒቴ ነው፤ የሚያስፈራኝ ማን ነው? እግዚአብሔር የሕይወቴ መታመኛ ነው፤ የሚያስደነግጠኝ ማን ነው?” (መዝሙር 27:1)።

እናንተ የደኅንነትን ክብር በውስጣችሁ ተሸከማችኋል። እናንተ ማምለጫ ፍለጋ፣ ወደ ችግር ውስጥ አትገቡም፤ ከማንኛውም ችግር ወይም አደጋ ጋር፣ ደኅንነት አብሮ አለ፤ መታደጋችሁ እርግጥ ነው። ተግዳሮቱ ከመገለጡ አስቀደሞ ፣ እናንተ ቀድማችሁ በድል ውስጥ ናችሁ። ስለዚህ በሕይወታችሁ፣ በአገልግሎታችሁና በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴያችሁ ምንም ነገር እንዲያስፈራችሁ ወይም እንዲያስደነግጣችሁ አትፍቀዱ።

ሁኔታዎች አስጊ ቢመስሉም፣ ማንነታችሁን አስታውሱ፡- እናንተ ከአሸናፊዎች በላይ ናችሁ (ሮሜ 8:37)። ጌታ ራሱ ደኅንነታችሁ ነው። እናንተ በመለኮታዊ ኃይሉ የተጠበቃችሁ፣ በፊቱ የተከለላችሁ፣ እና ለዘለቄታው ድል የታጨችሁ ናችሁ። 2 ቆሮንቶስ 2:14 እንዲህ ይላል፡- “ነገር ግን በክርስቶስ ሁልጊዜ ድል በመንሳቱ ለሚያዞረን... ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን።” ሃሌሉያ!

ስለዚህ፣ በድፍረትና በዓላማ ኑሩ፤ በሥልጣን ተናገሩ። ከዚህ ዓለም እንዳልሆናችሁ በመገንዘብ ተመላለሱ። በእናንተ ውስጥ ያለው ሕይወት ከማንኛውም ቀውስ የላቀ ነው፣ በእናንተ ውስጥ ያለው የእግዚአብሔር መንፈስም ከጉዳት በላይ ይጠብቃችኋል። መጽሐፍ ቅዱስ “በእናንተ ያለው በዓለም ካለው ይበልጣል” ይላል (1 ዮሐንስ 4:4)።

የእምነት አዋጅ
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ጌታ መጠጊያዬና ኃይሌ፣ መድኃኒቴም ነው፤ በእርሱም ከክፉ ነገር ሁሉ ተከልያለሁ እንዲሁም ተጠብቄአለሁ። በእኔ ውስጥ ያለው የእርሱ ሕይወት ከማንኛውም ቀውስ የላቀ ነው፤ ከሚጎዳ ወይም ከሚያስር ከማንኛውም ነገር በላይ ሁልጊዜም ከፍ አድርጎ ያኖረኛል። የኃይል፣ የፍቅር እና ራስን የመግዛት መንፈስ አለኝ። ሃሌሉያ!

ለተጨማሪ ጥናት
├─መዝሙር 27:1
├─ኢሳይያስ 41:10
├─1 ዮሐንስ 4:18


━━━━//━━━

27/05/2026

RHAPSODY OF REALITIES
(Amharic) 🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Wednesday 27, May 2026
ረቡዕ፣ ግንቦት 19 ቀን 2018 ዓ.ም.

📜በሃገራት ላይ የእግዚአብሔርን ቃል አውጁ
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

📖 “ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ዓለምን ያሸንፋልና፤ ዓለምንም የሚያሸንፈው እምነታችን ነው።” (1ኛ ዮሐንስ 5፡4)

👤 ፓስተር ክሪስ
════════
ዛሬ፣ በዓለም ውስጥ ለአገራት ምሪት ሰጪ አድርገው ራሳቸውን የሚያቀርቡ ስርዓቶችና ድምፆች አሉ፤ ነገር ግን ሐሳቦቻቸው ለብዙ አገሮች ውድቀት፣ መደናገር እና የኢኮኖሚ መመሰቃቀልን ነው ያመጡት። እነዚህ መፍትሄ እንሰጣለን ብለው የሚናገሩ ድርጅቶች ናቸው፤ ነገር ግን መሪዎችን አሳስተዋል፣ ኢኮኖሚዎችን ሽባ አድርገዋል፣ እና አገሮችን ወደ አላስፈላጊ ጥልቅ ዕዳ አስገብተዋል።

ብዙ መንግሥታት፣ በዓለም አቀፍ ችግር ጊዜ፣ ምንም ሳይለዩ እነዚህን ድምፆች ተከተሉ፤ ውጤቱም እጅግ የከፋ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ ስለ እንደነዚህ ያሉ ተፅእኖዎች አስቀድሞ አስጠንቅቆናል፤ “እነርሱ ከዓለም ናቸው፤ ስለዚህ ከዓለም የሆነውን ይናገራሉ ዓለሙም ይሰማቸዋል።” (1ኛ ዮሐንስ 4፡5)።

ነገር ግን ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን! በምድር ላይ ረዳት አልባ ሆነን የምንመለከት አይደለንም። እንደ የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን፣ እኛ ሥልጣን አለን፤ እንገዛለን እናም ነገሮችን እንቀይራለን። በጸሎታችን እና በእምነታችን ሥራ የጨለማ ዕቅዶችን ማፍረስ እንችላለን። እኛ በቦታችን እስካለን እና በእምነት እነሱን ተቃውመን እስከቆምን ድረስ፣ ምንም አይነት ድርጅት፣ ሀሳብ ወይም መዋቅር አገራትን ሊቆጣጠር አይችልም።

ኃላፊነታችን በመንፈስ መቆም እና ቃሉን በአገሮችና በመሪዎቻቸው ላይ ማወጅ ነው። ሰላሙንና ብልጽግናውን በአገሮች ላይ አውጁ። እርሱም እንዲህ እንድናደርግ አዞናል፤ ሉቃስ 10፡5-6 “ወደምትገቡበት ቤት ሁሉ አስቀድማችሁ፦ ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን በሉ። በዚያም የሰላም ልጅ ቢኖር፥ ሰላማችሁ ያድርበታል፤ አለዚያም ይመለስላችኋል።”

በስሙ ሃገሮችን ለመባረክ አስደናቂ ሥልጣን አለን፤ “በቅኖች በረከት ከተማ ከፍ ከፍ ትላለች፤…” (ምሳሌ 11፡11)። በበረከት ቃላት፣ የዓለም ከተሞችና ሃገሮች ከፍ ከፍ ይላሉ። ካጭበርባሪዎች ባርነት፣ ከኢኮኖሚ ችግሮችና ከዕዳ ይነሳሉ፣ እና እግዚአብሔር ለእነርሱ ወዳቀደው ፍጻሜ ይገባሉ።

በእምነታችንና በምልጃችን፣ የእግዚአብሔር ፈቃድ በምድር ላይ ያሸንፋል። ስለዚህ፣ ስለ ሃገራትና ስለ መሪዎቻቸው መጸለይ ቀጥሉ። እንደዚህ ስታደርጉ፣ የጨለማ ኃይሎችና ዕቅዶቻቸው ዝም ታሰኛላችሁ፣ ጽድቅም በሃገራት ውስጥ ይመሠረታል። መሪዎች እንዳይታለሉ፣ ሃገራቸውን ከሕገወጥና ከግፍ ዕዳ እንዲሁም ከክፉ ቁጥጥር ለማውጣት መለኮታዊ ጥበብ እንዲመራቸው አውጁ። ሃሌሉያ።

የእምነት አዋጅ
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ሃገራት ከማታለል ነጻ ወጥተዋል፣ መሪዎቻቸውም የእግዚአብሔርን ጽድቅ በምድራቸው ላይ ለማስፋፋትና ለመመስረት መለኮታዊ ጥበብን ይቀበላሉ። የዓለም ሃገራት ጠላቶች እቅዳቸው ፈርሷል፤ የኢየሱስ ስም ሥልጣን እና የክርስቶስ ድል በሁሉም ሃገራት ውስጥ ይፈጸማል። አሜን።

ለተጨማሪ ጥናት
├─1ኛ ዮሐንስ 5፡4
├─1ኛ ዮሐንስ 4፡4-5
├─ዳንኤል 4፡26

━━━━//━━━

26/05/2026

RHAPSODY OF REALITIES
(Amharic) 🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Tuesday 26, May 2026
ማክሰኞ፣ ግንቦት 18 ቀን 2018 ዓ.ም.

📜 ስኬት ናችሁ
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

📖 “ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ዓለምን ያሸንፋልና፤ ዓለምንም የሚያሸንፈው እምነታችን ነው።” (1ኛ ዮሐንስ 5፡4)

👤 ፓስተር ክሪስ
════════
የብርቱካን ፍሬ ትንሽ እና የማይታይ ሊመስል ይችላል፤ ነገር ግን በውስጡ የብርቱካን ዛፍ የመሆን ኃይል አለው፣ እና ዛፉም በውስጣቸው ብዙ ዘሮችን ወደ ያዘ ብዙ ፍሬ ይቀየራል። የብርቱካኑ ዛፍ የሚሆነው ሁሉም ነገር በዚያች በፍሬዋ ውስጥ አስቀደሞ የነበረ ነው። ፍሬው እንደ ብርቱካን "መሆን" የሚፈልግ አይደለም፤ መጀመሪያውንም ብርቱካን ነው። በውስጡ ያለውን እንዲያሳይ ትክክለኛ አካባቢ ብቻ ያፈልጋል።

ለምሳሌ፣ ያ የብርቱካን ፍሬ አፍ ቢኖረው እና፣ “እኔ ብርቱካን ነኝ” ብሎ ቢናገር፣ አንድ ሰው “ብርቱካን አትመስልም፤ አትጎርር” ብሎ ሊመልስለት ይችላል። ነገር ግን ያ ፍሬ እየዋሸ ወይም እይጎረረ አይደለም፤ የብርቱካን ተፈጥሮ ይዟል፤ በትክክለኛ ቦታ አስቀምጡት እና ተመልከቱ።

ገና ታዳጊ እያለሁ ራሴን የማየው እንደዚህ ነበር። በሕይወቴ ሁልግዜም ስኬታማ የሆንኩበት ምክንያት የእግዚአብሔር ሕይወት፣ የእርሱ ዘር፣ በእኔ ውስጥ ስለነበረ ነው፣ እናም ያንን ማወጅ ጀመርኩ፣ እንደሁም “ስኬታማ ሕይወት”በሚል ስያሜ ሴሚናሮችን ማካሄድ ጀመርኩ። እንዲህ እላለሁ፦ “እኔ ስኬት ነኝ”፤ አንዳንድ ሰዎች ግን “ምን እየተናገረ ነው?” ብለው ይደነቃሉ፤ ነገር ግን እኔ አውቃለሁ።

እኔ ይህን የምልበት ምክንያት ማድረግ የምፈልገውን ሁሉ ስላደረኩ አይደለም። እኔ ይህን የምናገረው በእኔ ውስጥ ያለውን ስለማውቅ ነው። ይህ ነው ክርስቶስ ለእኛ የሰጠን ሕይወት፤ እናንተ አንድ ቦታ ለመከናወን የምትሄዱ ስኬቶች ናችሁ። እናንተን የማያውቋችሁ ሰዎች አይደላችሁም ብለው ሊናገሩ ይችላሉ፣ የዛም ምክንያት እውነተኛ ማንነታችሁን ስለማያውቁ ነው። በሕይወታችሁ ያለውን የእግዚአብሔርን ሥራ አይረዱም።

እናንተ በክርስቶስ ኢየሱስ ማብቂያ ለሌለው ድሎች፣ ክብር እና ልህቀት የተፈጠራችህ የእግዚአብሔር የእጁ ሥራ ናችሁ፣ (ኤፌሶን 2፡10)። ቃሉ ስለ እናንተን በተመለከተ እንዲህ ይላል፤ የምታደርጉት ሁሉ ይሳካል፤ (መዝሙር 1፡3)። በቃሉ ውስጥ ቆዩ እና የማንነታችሁ እውነትን ኑሩ፤ እናም እግዚአብሔር በእናንተ ውስጥ ያስቀመጠው ነገር በሁሉ ቦታ ይገለጣል።

ጸሎት
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ውድ አባት ሆይ፣ ማንነቴን ስለሚገልጸው እውነት ስለሆነው ቃልህን አመሰግንሃለሁ። በድል እና በስኬት አስተሳሰብ እኖራለሁ፣ እናም የክርስቶስን እውነታዎች በሕይወቴ እገልጻለሁ። እምነቴ ያሸንፋል፣ ውጤቶቼ ሁሉ በመንፈሴ ውስጥ የክብርህና የጽድቅህ መገለጫ ናቸው። በኢየሱስ ስም። አሜን።

ለተጨማሪ ጥናት
├─ ኢያሱ 1፡8
├─ 2ኛ ቆሮንቶስ 2፡14
├─ ሮሜ 8፡37

━━━━//━━━

23/05/2026

RHAPSODY OF REALITIES
(Amharic) 🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Saturday 23 , May 2026
ቅዳሜ፣ ግንቦት 15 ቀን 2018 ዓ.ም

📜ክርስቶስ-ዋናው የማዕዘን ድንጋይ
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

📖“ኢየሱስ እንዲህ አላቸው። ግንበኞች የናቁት ድንጋይ እርሱ የማዕዘን ራስ ሆነ፤ ይህም ከጌታ ዘንድ ሆነ፥ ለዓይኖቻችንም ድንቅ ነው የሚለውን ከቶ በመጽሐፍ አላነበባችሁምን?” (ማቴዎስ 21፡42)

👤 ፓስተር ክሪስ
════════
ባለፈው ጥናታችን፣ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የቤተ ክርስቲያን መሠረት እንደሆነ፣ በመጽሐፍ ውስጥ እጅግ ግልጽ የሆነውን እውነት ተምረናል። ይህ የሆነ ሀሳብ ወይም ተራ ምልከታ አይደለም። በማቴዎስ 21፡42 በትንቢት ግንበኞች የናቁት፣ በእግዚአብሔር ግን የማዕዘን ራስ እንዲሆን የተመረጠው ዓለት ተብሎ የተነገረለት፣ እርሱ እንደሆነ አመልክቷል።

ሐዋርያው ጳውሎስ፣ በግልጽ በ1ኛ ቆሮንቶስ 3፡11 በመንፈስ እንዲህ ብሏል፣ “ከተመሠረተው በቀር ማንም ሌላ መሠረት ሊመሠርት አይችልምና፥ እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።” ይህ ሁሉን ያረጋግጣል። ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛው መሠረት ነው። ሌላ መሠረት ሊጣል አይችልም።

ይህ ከኢሳይያስ ትንቢት ጋር ይጣጣማል፣ “ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። እነሆ፥ በጽዮን ድንጋይን ለመሠረት አስቀምጣለሁ፤ የተፈተነውን፥ የከበረውን፥ መሠረቱ የጸናውን የማዕዘን ድንጋይ፤ የሚያምን አያፍርም።” (ኢሳይያስ 28፡16)። እዚህ ላይ እግዚአብሔር ስለ አንድ ሰው እያወራ ነው- ስለ ክርስቶስ ኢየሱስ። ከመዝሙር 118፡22 ላይም እንዲህ በማለት ተመሳሳይ ቃል ይጠቅሳል፣ “ኢየሱስ እንዲህ አላቸው። ግንበኞች የናቁት ድንጋይ እርሱ የማዕዘን ራስ ሆነ፤ ይህም ከጌታ ዘንድ ሆነ፥ ለዓይኖቻችንም ድንቅ ነው የሚለውን ከቶ በመጽሐፍ አላነበባችሁምን?” (ማቴዎስ 21፡42)

የክርስቶስ ባዓለም ያለመፈለግ የእግዚአብሔርን እቅድ አላደናቀፈውም፤ እንደውም እንዲፈጸም ነው ያደረገው። እነርሱ የናቁት የእግዚአብሔር የዘላለም መሠረት ሆነ። በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 4፣ ሐዋርያቶቹ ይህንን እውነት በድፍረት በማወጅ ያለ ስህተት እንድንረዳው አድርገዋል፣ ”እናንተ ግንበኞች የናቃችሁት፥ የማዕዘን ራስ የሆነው ይህ ድንጋይ ነው።” (የሐዋርያት ሥራ 4፡11)።

ለዚህም ነው ጌታ ኢየሱስ በማቴዎስ 16 “ዓለት” ብሎ የተናገረው መገለጥም ጴጥሮስም ያልሆነው። መጽሐፍት በተደጋጋሚ ክርስቶስን ዓለት፣ የማዕዘን ድንጋይ፣ መሠረት እንዲሁም የማዕዘን ራስ ብለው ጠርተውታል። ጳውሎስ በመንፈስ በመመራት በኤፌሶን 2፡20 እንዲህ ብሏል፣ ” በሐዋርያትና በነቢያት መሠረት ላይ ታንጻችኋል፥ የማዕዘኑም ራስ ድንጋይ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤” (ኤፌሶን 2፡20)።

የቤተ ክርስቲያን መሠረት ክርስቶስ ነው፤ በእርሱ የሚያምኑ ሁሉ በዚህ ዓለት የጸኑ ፣ የማይነቃነቁ እና ለዘላለም አሸናፊዎች ናቸው! ይህ የወንጌል ክብር ነው። ሃሌሉያ!

የእምነት አዋጅ
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
የቤተ ክርስቲያን የጸና መሠረትና የማዕዘን ራስ በሆነው በክርስቶስ ጸንቻለሁ። እምነቴ በእርሱ ላይ ብቻ ነው፣ ህይወቴ በማይናወጠው በእርሱ እውነት ላይ የታነጸ ነው። ዓለት በሆነው በክርስቶስ ኢየሱስ መሰረት ስለያዝኩ በመረጋጋት፣ በራስ መተማመን እና በድል እመላለሳለሁ። አሜን!

ለተጨማሪ ጥናት
├─ 1ኛ ጴጥሮስ 2፡6
├─ ኢሳይያስ 8፡14
├─ መዝሙር 118፡22-23

━━━━//━━━

21/05/2026

RHAPSODY OF REALITIES
(Amharic) 🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Thursday 21, May 2026
ግንቦት 13 ቀን 2018 ዓ.ም.

📜ትክክለኛውን ምክር ለማግኘት ቃሉን ተጠቀሙ
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

📖“ከዚያን ቀን ጀምሮ ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ይሄድ ዘንድ ከሽማግሎችና ከካህናት አለቆች ከጻፎችም ብዙ መከራ ይቀበልና ይገደል ዘንድ በሦስተኛውም ቀን ይነሣ ዘንድ እንዲገባው ለደቀ መዛሙርቱ ይገልጥላቸው ጀመር” (ማቴዎስ 16:21)

👤 ፓስተር ክሪስ
════════

ማቴዎስ 16 በጌታ በኢየሱስና በደቀ መዛሙርቱ መካከል ስለነበረ ወሳኝ ቅጽበት ይነግረናል። እርሱ ክርስቶስ እንደሆነ ከሰበኩና ካወጁ
በኋላ፣ ጌታ ወደ ውስጥ በማተኮር፣ ሊመጣ ያለውን መግለጥ ጀመረ። ደቀ መዛሙርቱንም ማንነቱን ለጊዜው እንዳይገልጡ አዘዛቸው።

ከአፍታ በኋላ ወደ እየሩሳሌም እንደሚሄድ፣ ብዙ ስቃይ እንደሚያሳልፍ፣ እንደሚገደል እና በትንሳኤ እንደሚነሳ አብራራላቸው። ይህን ሁሉ ከሰሙ በኋላ፣ ጴጥሮስ የማይታመን ነገር አደረገ። መጽሐፍ ቅዱስ ጴጥሮስ ጌታን ገለል አድርጎ ወሰደና “….ጴጥሮስም ወደ እርሱ ወስዶ። አይሁንብህ ጌታ ሆይ፤ ይህ ከቶ አይደርስብህም ብሎ ሊገሥጸው ጀመረ።” ይላል (ማቴዎስ 16፡22)

እስኪ አስቡት፣ ጴጥሮስ ጌታን ሲገስጸው። በጴጥሮስ በኩል የሚናገረው ሰይጣን እንደሆነ ጌታ ያውቅ ስለነበር ለሰይጣን እንዲህ በማለት በቀጥታ ምላሽ ሰጥቷል፣ “….ወደ ኋላዬ ሂድ፥ አንተ ሰይጣን፤ የሰውን እንጂ የእግዚአብሔርን አታስብምና ዕንቅፋት ሆነህብኛል አለው።” (ማቴዎስ 16፡23)

እነዚያን ቃላት በአንደበቱ ያስቀመጠው ሰይጣን እንደነበረ ስላላወቀ፣ ጴጥሮስ፣ በሁኔታው ሳይደናበር አልቀረም። ለማን እንደምትናገሩ ማወቅ ግድ ይላችኋል። የእግዚአብሔር የሆነን ነገር ብቻ ተወጡ። ሰይጣንን ለመደገፍ ድምፃችሁን አታውሱ።

ቃሉን ማወቅና አእምሯችሁን እንዲያድሰው ማድረግ አስፈላጊ የሚሆነው ለዚህ ነው። ቃሉ በሙላት ይኑርባችሁ (ቆላስይስ 3፡16)። የእግዚአብሔር ቃል እውቀት መለየት እንድትችሉ ያደርጋችኋል፤ መልካሙን ከክፉ እንዲሁም በጎ፣ መልካምና ፍጹም የሆነውን የእግዚአብሔርን ፈቃድ ምን እንደሆነ ፈትናችሁ እንድታውቁ ያደርጋችኋል (ሮሜ 12፡2)። በእግዚአብሔር ቃል ብርሃን ከእናንተ፣ ከሰይጣን ወይም ከእግዚአብሔር የሚመጣውን መለየት ትችላላችሁ።

ጸሎት
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ውድ አባት ሆይ፣ መረዳት እና መለየትን ስለሚሰጠኝ ቃልህ አመሰግናለሁ። ልቤ በእውነትህ የጸና ነው፤ ከአንተ ዘንድ ያልሆነውን ሃሳብ፣ ድምጽ እና ተጽእኖ እለያለሁ። የቃልህ እውቀት ይመራኛል፣ ሁል ጊዜም ከፈቃድህ ጋር የሚስማማ ንግግርን እናገራለሁ። በድል እመላለሳለሁ፣ በክርስቶስ በሆንኩት ማንነቴ ንቃተ-ህሊና እኖራለሁ። ሃሌሉያ!

ለተጨማሪ ጥናት
├─ ቆላስይስ 3፡2
├─ ሮሜ 8፡5
├─ ኢሳይያስ 55፡ 8-9
└─

━━━━//━━━

20/05/2026

RHAPSODY OF REALITIES
(Amharic) 🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Wednesday 20, May 2026
ረቡዕ፣ ግንቦት 12 ቀን 2018 ዓ.ም.

📜ሰይጣናዊ ተፅእኖዎችን ቆርጣችሁ ጣሉ
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

📖ደሴቲቱንም ሁሉ እስከ ጳፉ በዞሩ ጊዜ፥ በርያሱስ የሚሉትን ጠንቋይና ሐሰተኛ ነቢይ የሆነውን አንድ አይሁዳዊ ሰው አገኙ (የሐዋርያት ሥራ 13:6)

👤 ፓስተር ክሪስ
════════

የሐዋርያት ሥራ 13፣ ሰይጣን ወንጌል ወደሰዎች በተለይም በመሪነት ስፍራዎች ላይ ወዳሉት ሊደርስ ባለበት ጊዜ፣ እንዴት ለመቋቋም እንደሚሞክር ግልፅ የሆነ ማሳያን ይሰጠናል። ሳኦል (ጳውሎስ) እና በርናባስ ወንጌልን በመስበክ በጳፉ ደሴት ባለፉ ጊዜ፣ የሆነው በሐዋርያት ሥራ 13:6 ላይ እንደምሳሌ ሆኖ ይታያል። መጽሐፍ ቅዱስ "አስተዋይ ሰው" ብሎ የሚገልፀው አገረ ገዥ ሰርግዮስ ጳውሎስ፣ የእግዚአብሔርን ቃል መስማት ፈልጎ በርናባስና ሳኦልን (ጳውሎስን) አስጠርቶ ነበር (ሐዋርያት ሥራ 13:7)። ስለኢየሱስ ክርስቶስ የበለጠ ማወቅ ፈለጎ ነበር።

ነገር ግን ያ እንዲሆን ያልፈቀደ ከእርሱ ጋር በቅርበት የተገናኘ አንድ ሰው ነበር፤ ይህንን የሐዋርያት ሥራ 13:6-8 የአምፕሊፋይድ ክላሲክ ትርጉም ይገልጠዋል: "የቆጵሮስን ደሴት ከዳር እስከ ዳር አቋርጠው ጳፉ በደረሱ ጊዜ፣ በርያሱስ የተባለ አንድ አይሁዳዊ ጠንቋይ ወይም አስማተኛና ሐሰተኛ ነቢይ አገኙ፤ እርሱም ሰርግዮስ ጳውሎስ ከተባለው ብልህና አስተዋይ አገረ ገዥ ጋር በቅርበት ነበረ። ይህ አገረ ገዥ፣ [በክርስቶስ ስለሚገኘው በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ ስላለው መዳን] የእግዚአብሔርን ቃል ለመስማት ፈልጎ በርናባስንና ሳውልን አስጠራቸው። ጠቢቡ ሰው ኤልማስ ግን፣ [እራሱ ለራሱ የሰጠው] የስሙ ትርጒም እንዲህ ነበርና፣ አገረ ገዡ እምነቱን እንዳይቀበል ለማደናቀፍ ስለ ፈለገ ተቃወማቸው።" መሪው የእግዚአብሔርን ቃል እንዳይቀበል በመቋቋም ለማስቆም ሞከረ።

ከዚያም መጽሐፍ ቅዱስ "ጳውሎስ የተባለው ሳውል ግን መንፈስ ቅዱስን ተሞልቶ ትኵር ብሎ ሲመለከተው። አንተ ተንኰል ሁሉ ክፋትም ሁሉ የሞላብህ፥ የዲያብሎስ ልጅ፥ የጽድቅም ሁሉ ጠላት፥ የቀናውን የጌታን መንገድ ከማጣመም አታርፍምን? ...አለው" ይላል (ሐዋርያት ሥራ 13:9-10)። ጳውሎስ እየተናገረ የነበረው በጥርጣሬ ወይም በስሜት አልነበረም። የተናገረው በመንፈስ ቅዱስ በመነሳሳት ነበር። የዲያቢሎስ ልጅ፤ የጽድቅ ሁሉ ጠላት ሲል እውነተኛ በሆነው ማንነቱ ጠራው።

በብዙ የአለም መሪዎች ዙሪያ እንዲህ ያሉ እውነትን የሚያጣምሙና የእግዚአብሔርን ቃል እንዳይሰሙ የሚከላከሉ ሰዎች አሉ።
በጸሎት የምንቆመው እንዲህ ያሉ ሰዎችን ተፅእኖ ከሃገራት መሪዎች ላይ የምንቆርጠው በዚያ ስለሆነ ነው።

በተደጋጋሚ፣ በአለም ዙረያ ላሉ ለሃገራት መሪዎች፣ ለመንግስታትና ለተቋሞች ስትጸልዩ፣ የዚህ አለም "ኤልማስ" ምክሮች ከንቱናድምጽ አልባ መሆናቸውን አ ውጁ፤ ከመሪዎች ላይ ያላቸውን ተፅእኖ ቁረጡ። በአለም ዙሪያ ሁሉ የፕሬዝዳንቶች፣ የነገስታት፣ የገዢዎች፣ የህግ አውጪዎችና የውሳኔ አስተላላፊ ሰዎች ልቦች የእግዚአብሔርን ቃል ለመስማትና ለመቀበል ክፍት እንዲሆኑና ወንጌል በሕይወታቸው ላይ ውጤት እንዲያፈራ ጸልዩ።

እንዲሁም ወንጌል መሰበክ እንዲችል፣ ሰዎችም በነፃት መቀበል እንዲችሉና በአለም ዙሪያ ሁሉ በፍጥነት እንዲስፋፋ መንፈስ ቅዱስ ሽንገላን የመለየት አስተውሎት እንዲሰጣቸውና የጽድቅ ተፅእኖዎች እንዲከቧቸው ጸልዩ። ሃሌሉያ!



የእምነት አዋጅ
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
በሃገራት ውስጥ ባሉ መሪዎችና ውሳኔ አስተላላፊዎች ልቦች ውስጥ የእግዚአብሔር ቃል ዛሬ እንዲያይል እጸልያለሁ። ወንጌልን የሚቋቋምና ከእውነት የሚመልሳቸው እያንዳንዱ የሰይጣን ተፅእኖ በመንፈስ ቅዱስ ሃይል የተቆረጠ ነው። የእግዚአብሔር ጥበብና ጽድቅ ሃገራትን ይገዛል፤ እውነቱም ያለተቋቋሚ ተመስርቷል፤ በኢየሱስ ስም። አሜን።

ለተጨማሪ ጥናት
├─ 2ኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 15:31
├─ መዝሙረ ዳዊት 33:10
├─ መጽሐፈ ምሳሌ 21:30
└─

━━━━//━━━

19/05/2026

RHAPSODY OF REALITIES
(Amharic) 🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Tuesday 19 , May 2026
ማክሰኞ፣ ግንቦት 11 ቀን 2018 ዓ.ም

📜ሁልጊዜም ፈቃዱን ይጠብቃል
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

📖አኪጦፌል ከአቤሴሎም ጋር በሴራ አንድ ነው ብለው ለዳዊት ነገሩት፤ ዳዊትም። አቤቱ፥ የአኪጦፌልን ምክር ስንፍና አድርገህ እንድትለውጥ እለምንሃለሁ አለ (2ኛ ሳሙኤል 15:31)

👤 ፓስተር ክሪስ
════════
በቀድሞ ጥናታችን፣ የዳዊት ልጅ አቤሴሎም፣ እንዴት በአባቱ ላይ ጠንካራ አመፅን እንደመራ ጠቅሰን ነበር። አኪጦፌል ከእግዚአብሔር የሚናገር ሰው እንደሚከበር ያክል የተከበረ ነበር፣ ነገር ግን በዳዊት ላይ አመፁን የበለጠ በማፋፋም ከአቤሴሎም ጎራ ተቀላቀለ። ከዚህ የተነሳ፣ ዳዊት የአኪጦፌልን ጥበብ ወደሞኝነት እንዲቀይርለት ወደ ጌታ ጸለየ።

የዳዊት ጸሎት አንዳች አስደናቂ ነገር አስከተለ። ዳዊት ለእግዚአብሔር ወደሚያመልከበት ተራራ ራስ ሄደ፣ በዚያም አርካዊው ኩሲ
ሊገናኘው እንደመጣ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። የእግዚአብሔር መልስ ስትራቴጂካዊ ቦታ ሊይዝ ባለው ሰው መልክ ተገልጦ መጣ።

ዳዊት ወዲያው ያ ምን ማለት እንደነበርና ምን ማድረግ እንደነበረበት ተረዳ። ኩሲ ወደከተማ እንዲመለስና እሱን (ዳዊትን) እንዳገለገለ፣ ራሱን ለአቤሴሎም አገልጋይ አድርጎ እንዲያቀርብ ነገረው። አላማው ግልፅ ነበር፤ ኩሲ ይህን በማድረጉ በአቤሴሎም ሰፈር ሆኖ የአኪጦፌልን ምክር የሚቃወምበትና የሚያሸንፍበት ስፍራ ላይ እንዲሆን ነበር።

ይህ እግዚአብሔር እቅዱን እንዴት እንደሚያስጠብቅ የሚያስታውቅ አስደናቂ ማሳያ ነው። በተንኮለኛ አማካሪዎች አማካኝነት ሰይጣናዊ ስትራቴጂዎች በሚነሱበት ጊዜ እንኳን እግዚአብሔር እነዚያን ወጥመዶች ከንቱ የሚያደርጉና የሚያፈርሱ የእርሱ የራሱ የጥበብና የጽድቅ መሳሪያዎች የሆኑ ህዝቦች አሉት።

ስለዚህ፣ መሪ ከሆናችሁ፣ ውሳኔዎቻችሁን የሚያውቁና በዚያም ላይ ተፅእኖ ማሳደር የሚችሉ፣ በካቢኔያቸሁ ወይም በውስጥ ዙሪያችሁ ያሉት ሰዎች ማንነት ተፅእኖ እንዳለው ማወቅ ያስፈልጋችኋል። የእግዚአብሔር እቅድ እንዲያይልና በአለማችን ላይ ማሸነፉን እንዲቀጥል የሚያደርጉ፤ ለጽድቅና ለእውነት ድምፅ ሆነው የሚቆሙ ሊሆኑ ይገባቸዋል።

እግዚአብሔር፣ በጥበቡ፣ ሁልጊዜም የእርሱ "ኩሲ" የሆኑ፣ ክፉ ምክሮችን ከንቱ የሚያደርጉና የእግዚአብሔር ፈቃድ መፈፀሙን የሚያረጋግጡ፣ በመንፈስ ቅዱስ ወደ ስፍራው የመጡ ወንዶችና ሴቶች በሃገራት መሪዎች መካከል አሉት። ጽድቅን እንዲጠብቁና በሃገራት ላይ ያለውን እቅድ ለማስፋፋት እንዲረዷቸው ስትራቴጂካዊ በሆነ መንገድ እርሱ ያስቀመጣቸውን ወንዶችና ሴቶች ለይተው ያውቋቸው ዘንድ ሁልጊዜ ለመሪዎች ጸልዩ። ሃሌሉያ!



ጸሎት
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ውድ አባት ሆይ፤ ልጆችህ የወንጌልህን እውነት አፅንተው ሲይዙና ጽድቅን በአለም ዙሪያ ሲመሰርቱ የአንተ ጥበብና ጽድቅ በሃገራት ላይ አይሎ ይገለጣል። የአንተ ፈቃድ በምድር ላይ ይፈፀማል፤ ግዛትህም ሳይገደብ ይስፋፋል፤ በኢየሱስ ስም። አሜን።

ለተጨማሪ ጥናት
├─ መጽሐፈ ምሳሌ 21:30
├─ ትንቢተ ኢሳይያስ 8:10
├─መጽሐፈ ኢዮብ 5:12
└─

━━━━//━━━

18/05/2026

MON MAY 18 2026
(Rhapsody of reality Amharic)🇪🇹🇪🇹🇪🇹

በመምራት ውስጥ መንፈሳዊ የመለየት አስተውሎት

በዚያም ወራት የመከራት የአኪጦፌል ምክር የእግዚአብሔርን ቃል እንደ መጠየቅ ነበረች፤ የአኪጦፌልም ምክር ሁሉ ከዳዊትና ከአቤሴሎም ጋር እንዲህ ነበረች (2ኛ ሳሙኤል 16:23)

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ክፉ ምክር አደጋ በተደጋጋሚ ያስጠነቅቀናል። መጽሐፍ ቅዱስ ይህንን ምክሩ ሰው የእግዚአብሔርን ቃል እንደሚጠይቅ ያክል ሆኖ እስኪታይ ድረስ እንዲህ ያለ ክብደትን በተሸከመለት በአኪጦፌል ታሪክ ይገልጣል (2ኛ ሳሙኤል 16:23)።

በዳዊት ብቻ ሳይሆን፣ በኋላም በአቤሴሎም፣ የተከበረ፣ የታመነና እነርሱም የሚተማመኑበት ሰው ነበር። ሆኖም ግን፣ መታወቂያው ይህ ቢሆንም፣ የክፉ ሴራ ተካፋይ ሆነ። አቤሴሎም በአባቱ በዳዊት ላይ ሲያምፅ፣ ሴራው ብርታትን አገኘ፣ ሰዎችም ወደ አቤሴሎም መጨመራቸው ቀጠለ (2ኛ ሳሙኤል 15:12)። በዚያ አመፅ መካከል፣ አኪጦፌል ከአቤሴሎም ጋር ተባበረ።

ከዚያም ወሬው ዳዊት ጋር ደረሰ: "አኪጦፌል ከአቤሴሎም ጋር በሴራ አንድ ነው" (2ኛ ሳሙኤል 15:31)። አኪጦፌል ከአቤሴሎም ጎራ መሆኑ ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ነበረው። ምክንያቱም የእርሱ ምክር ሃያል፣ የሚያሳምንና ተፅእኖ ፈጣሪ ነበር። ነገር ግን ዳዊት አልተደናገጠም ወይም አኪጦፌልን በሰዋዊ ብልጠት ለመብለጥ አልሞከረም። እንዲህ ብሎ ጸለየ: "አቤቱ፥ የአኪጦፌልን ምክር ስንፍና አድርገህ እንድትለውጥ እለምንሃለሁ" (2ኛ ሳሙኤል 15:31)።

ይህ ጸሎት አስፈላጊ እውነትን ይገልጣል፤ ምክር ምንም ያክል የብልህ መስሎ ቢታይ፣ ከእግዚአብሔር እቅድ ጋር ከተቃረነ መሸነፍ ይችላል። ለዚህ ነው የመለየት አስተውሎት ለመሪዎች መሰረታዊ የሆነው። በመሪዎች ዙሪያ ያለ ድምፅ ሁሉ ለመርዳት የሚላክ አይደለም። አንዳንድ አማካሪዎች ራሳቸውን እንደ ጠቢብ አድርገው ቢያቀርቡም መሻታቸው ግን ማሳት፣ መከፋፈልና ማውደም ነው።

መልካሙን ገፍተው ያስወጣሉ፣ ፃድቁን ተቃውመው ይናገራሉ፣ እንዲሁም እግዚአብሔር እየገነባ ያለውን የሚያዳክም ሃሳብ ለመትከል ይሞክራሉ። ነገር ግን መለኮታዊ ፍርድ ከሚደርስበት ያለፉ አይደሉም። ጌታ ሊያጋልጣቸው፣ ዝም ሊያሰኛቸውና ጥበባቸውን ወደ ሞኝነት ሊቀይረው ይችላል።

ክርስቲያን እንደመሆናችን፣ ሃገራት ላይ፣ መሪዎቻቸው ላይ፣ ቤተሰቦቻቸውና ፍፃሜያቸው ላይ ተፅእኖ ለማምጣት በክርስቶስ ያለንን ስልጣን መረዳትና መጠቀም አለብን። ስለዚህ በስልጣን ስፍራ ላይ ያሉት ሰዎች በእውነት የተመሩ፣ በጽድቅ ምክር የተከበቡና የእግዚአብሔርን እቅድ ለመፈፀም የበረቱ ይሆኑ ዘንድ ሁልጊዜ በማስተዋል ጸልዩ።

አሳች አጀንዳዎችን እንዲለዩና ድል እንዲያደርጉ፣ እንዲሁም በእግዚአብሔር ጥበብ ይመላለሱ ዘንድ የእግዚአብሔር መንፈስ በቀጣይነት የመለየትን አስተውሎት እንዲሰጣቸው ጸልዩ። እግዚአብሔር ይመስገን!

PRAYER / CONFESSION

ውድ አባት ሆይ፤ በእኔና በቤተክርስቲያንህ ውስጥ እየሰራ ስላለው የመንፈስህ ጥበብ አመሰግንሃለሁ። በጽድቅ ምክር ይከበቡ ዘንድና በእውነት የተመሩ ይሆኑ ዘንድ በሃገራትና በተቋማት ውስጥ ላሉ መሪዎች እፀልያለሁ። እያንዳንዱ የሽንገላ ተፅእኖ ተጋልጧል፣ እንዲሁም የአንተን እቅድ የሚቃወም እያንዳንዱ ምክር ወደ ሞኝነት ተቀይሯል። በምድር ላይ ጥበብህ አይሎ ይገለጣል፤ ፈቃድህም ተመስርቷል፤ በኢየሱስ ስም። አሜን።

FURTHER STUDY
መዝሙረ ዳዊት 33:10-11; መጽሀፈ ምሳሌ 21:30; መጽሀፈ ሳሙኤል ካልእ 17:23

1-YEAR BIBLE READING PLAN
የዮሐንስ ወንጌል 8:31-47 & መጽሀፈ ነገስት ቀዳማዊ 22

2-YEAR BIBLE READING PLAN
1 ኛ ቆሮንጦስ 10:14-21 & መጽሀፈ ምሳሌ 14

Want your place of worship to be the top-listed Place Of Worship in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Website

Address


Summit 72
Addis Ababa
1000