Hahu
Molleyobiel
18/02/2022
የፌስቡክ አካውንትዎን ደህንነት ለመጠበቅ ሊወሰዷቸው የሚገቡ የጥንቃቄ እርምጃዎች
=============
1. የይለፍ-ቃልዎን ደህንነት ማረጋገጥ
• የፌስቡክ አካውንቶን ለሌላ ማንኛውም የኦንላይን አገልግሎት ላይ አይጠቀሙ፤
• የይለፍ-ቃልዎን በፍፁም ለሌላ ሰው አያጋሩ፤
• የሚጠቀሙበት የይለፍ-ቃል ለመገመት አዳጋች የሆነ፣ በፍጹም የእርሶን ስም እና የተለመዱ ቃላትን ያልያዘ ሊሆን ይገባል፤
• የይለፍ-ቃልዎ ፣ኢ-ሜይልዎን፣ የስልክ ቁጥሮን ወይም የልደት ቀንዎን በፍፁም የሚጠቀም መሆን የለበትም፤
2. የሚያስሱትን ድረ-ገጽ መረጃ በፍጹም አያጋሩ
• አጥቂዎች ፌስቡክ የሚመስል የሐሰት ገጽ ፈጥረው በኢ-ሜይል አድራሻዎና በይለፍ ቃልዎ እንዲገቡ ሊጠይቁዎ ይችላሉ፤
• ሁልጊዜም መረጃ የሚያስሱበትን ድረ-ገጽ URL ትክክለኝነት ያረጋግጡ፤ አጠራጣሪ ነገር ሲያጋጥሞ www.facebook.com በማፈላለጊያው ላይ በመጻፍ ወደ ትክክለኛው የፌስቡክ ገጽ ለመመለስ ይሞክሩ፤
• ከሜታ /Meta/ ወይም ፌስቡክ የሚላክሎትን ኢ-ሜይል በፍጹም ለሌላ ሰው አያጋሩ፣ በተለይም ስለ አካውንቶ ምስጢራዊ መረጃዎችን የያዙ ከሆነ፤
• ስለፊሺንግ ጥቃት እና ጠንካራ የይለፍ-ቃል አጠባበቅ ላይ ያለዎትን እውቀትና ግንዛቤ በየጊዜው ያሳድጉ፤
3. ኮምፒውተርዎን ለሌላ ሰው የሚያጋሩ ከሆነ የፌስቡክ አካውንቶን ዘግተው መውጣትዎን /Log Out/ ማድረግዎን አይዘንጉ፤
• ኮምፒውተርዎን ዘግተው ሳይወጡ ወይም መሣሪያዎን ያዋሱ ከሆነም ከርቀት እንዴት መውጣት /Log Out Remotely/ እንደሚችሉ ይወቁ፤
• ከርቀት ሆነው ለሌላ አካል ካዋሱት ኮምፒውተር ላይ ለመውጣት(log out) ለማድረግ ወደ ፌስቡክ "Security and Login Setting" ሲገቡ ከዚህ በፊት ይገቡባቸው የነበሩ መሣሪያዎችን ዝርዝር የሚያቀርብልዎ ሲሆን ከዚህ ውስጥ የሚፈልጉት መሣሪያ ላይ "Logout" የሚለውን ትዕዛዝ በመጫን መውጣት ይችላሉ፤
4. ከማያውቋቸው ሰዎች የጓደኝነት ጥያቄ ሲላክልዎ አይቀበሉ
• ጠላፊዎች ሰዎችን ለማጥመድ ሲፈልጉ ሀሰተኛ አካውንት ሊፈጥሩ ይችላሉ፤
• የጠላፊዎች ጓደኛ መሆን ምን አልባት የእርሶን የፌስቡክ የፊት ገጽን /Timeline/ ሊበክሉ፣ የተለያዩ ጉዳዮችን በገጾ ላይ ሊያጋሩ ወይም በካይ መልዕክቶችን በመልዕክት መቀበያዎ ሊልኩብዎ ይችላሉ፤
5. ከበካይ ሶፍትዌሮች እራሶን ይጠብቁ
• አጥፊ ሶፍትዌሮች ኮምፒውተሮች፣ ሰርቨሮች /Server/ ወይም የኮምፒውተር ኔትወርክ ላይ ጉዳት ሊጥሉ ይችላሉ፤
• የተበከለ ኮምፒውተር ወይም መሣሪያ ምን ዓይነት ባህሪያት እንደሚያሳዩ እና እነዚህን በካይ ሶፍትዌሮችን እንዴት ማስወገድ እንደሚችሉ በሚመለከት ያለዎትን እውቀት ያዳብሩ፤
• ማፈላለጊያዎትን በየጊዜው ያዘምኑ፣ አጠራጣሪ መተግበሪያዎችን እና የማፈላለጊያ ማስታወቂያዎችን ያስወግዱ፤
6. አጠራጣሪ ማስፈንጠሪያዎችን /Links/ ከሚያውቁት ጓደኛ ወይም ድርጅት እንኳ ቢላክልዎ ከመክፈት ይቆጠቡ
• እነዚህ በፌስቡክ ወይም በኢ-ሜይል የሚላኩ ማስፈንጠሪያዎች /Links/ ሊሆኑ ይችላሉ፤
• ፌስቡክ ወይም Meta የይለፍ-ቃሎን በኢ-ሜይል እንዲያስገቡ በፍጹም እንደማይጠይቅዎ ይወቁ፤
• አጠራጣሪ ማስፈንጠሪያ ሲያጋጥሞ ለፌስቡክ ሪፖርት /report it/ ያድረጉ፤
7. ተጨማሪ የደህንነት መጠበቂያ መንገዶችን ይተግብሩ
• ከማይታወቁ አድራሻዎችና መሣሪያዎች ወደ አካውንትዎ የመግባት ሙከራ ሲደረግ የጥቆማ መረጃ እንዲደርሶ /get alerts about unrecognized logins/ ያድረጉ፤
• ባለሁለት ደረጃ የማንነት ማረጋገጫ ዘዴ /Set up two-factor authentication/ ይጠቀሙ፤
• ሌሎች የደህንነት ጉዳዮችን በተመለከተ የፌስቡክ Help & Support ላይ በመግባት ያለዎትን ግንዛቤ በየጊዜው ያሳድጉ፤
©ኢመደኤ
እንዲሁም ከዚህ በፊት የለቀቅኳቸውን ቪዲዮዎችን ብትከታተሉ ምርጥ እውቀትን ልታገኙ ትችላላችሁ
አሁንም የቴሌግራምና የYouTube ቻናሌን Subscribe በማድረግ ድጋፋችሁን አሳዩኝ።
✅✅✅ #ያወቁትን ማሳወቅ ብልህነት ነው!✅✅✅
የ YouTube ቻናል ሊንክ 👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UCZBIP6PqUdmmagdTjbyp_AQ
ቴሌግራም ቻናል
👇👇👇👇👇👇 https://t.me/MuhammedComputerTechnology
31/01/2022
E/r
የመሥቀል በአል በአርባምንጭ
Hahu Molleyobiel
25/04/2021
እንኩ ውሰዱት
18/04/2021
ውድ የs-information technology ተከታታዮቻችን ዛሬ ይዤላችሁ የመጣውት የአንድን ሰው አድራሻ እንዴት በቀላሉ ማወቅ እንችላለን የሚል ነው ከዚህም በተጨማሪ ስልካችሁ ጠፍቶ ወይም ተሰርቆም ቢሆን እንዴት መልሰን ማግኘት እንችላለ የሚል ነው ተከታተሉን።
1⃣ ይህንን ለማድረግ በቀጥታ የgoogle chrome app እንከፍትና የፈለግነውን የምስል ስም እንፅፍና ምስሉ ሲመጣልን የምስሉን ሊንክ ኮፒ በማድረግ እንወጣለን።
2⃣ iplogger የሚባል app ከplay store ላይ እናወርዳለን የapp ሊንክ የዮቲብ ዲስክሪብሽን ቦክስ ላይ አስቀምጫላችሁዋለው እሱን እንከፍትና ክሬት ሎገር የምትለውን ነክተን እንገባለን image/url የምትለውን ነክተን ከከፈትን በሁዋላ የምስሉን ሊንክ paste እናደርገና coment የሚለው ላይ የፈለግነውንእንፅፋለን።
3⃣ ኢሄንን አርገን ስንጨርስ ከስር የcopy ምልክቱዋን ተጭነን copy አርገን እንወጣለን ።
4⃣ በመቀጠል ወደፈለግነው የሶሻል ሚዲያ በመሄድ ሊንኩን ለመቆጣጠር ወደምንፈልገው ሰው እንልካለን ።
5⃣ ሰውየው ሲመለከተው ወደ iplogger በመመለስ ከiplogger ላይ የሰውየውን ip address በመያዝ ወደ googel chrome እንመለስና።
6⃣ ip2logger ብለን search እናደርግና try demo የምትለውን ስንነካ lookup የሚል ይመጣል እዛ ላይ copy ያደረግነውን ip adreess paste ስናደርግ በማይታመን ሁኔታ የሰውየውን ሙሉ የስል መረጃ ያመጣልናል
7⃣ በመቀጠል ከመጡት ምርጫዎች ውስጥ cordinet of city ፊትለፊት ያለቺውን ምልክት ተጭናችሁ copy ካደረጋችሁ በሁዋላ የሚመጣውን ነገር ደግሞ መገመት ይከብዳችሁዋል።
👉ቪዲዮን ሊንኩን በመጫን የሚገርመውን መጨረሻ ተመልከቱን በጣም ትወዱታላችሁ 100% ይስራል።
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://youtu.be/dIbZpzF_FMQ
16/04/2021
የጥድፊያ ዘመን
05/04/2021
የፌስቡክ አድራሻችንን ሙሉ በሙሉ እንዴት ማጥፋት ይቻላል…?
አንዳንዴ የማህበራዊ ትስስር ድረ ገጾችን መጠቀም ማቆም ወይም ራሳችንን ከገጾቸቹ ማግለል ሲያስፈልገን ይስተዋላል።
ከነዚህ ማህበራዊ ትስስር ድረ ገጾች አንዱ ፌስቡክ ሲሆን፥ ፌስቡክ በዓለማችን ላይ በርካታ ተጠቃሚዎች ያሉት የማህበራዊ ትስስር ድረ ገጽ ሲሆን፥ በየቀኑ 1 ነጥብ 3 ቢሊየን ተጠቃሚዎችን ያስተናግዳል።
በየእለቱ ለቁጥር አዳጋች እስኪሆን ድረስ በርካታ የፌስቡክ አድራሻዎች/አካውንቶች/ በየእለቱ የሚከፈቱ ሲሆን፥ በርካቶች የየእለት እንቅስቃሴያቸውን ሳይቀር በፌስቡክ ላይ ሲያሰፍሩ ይስተዋላል።
አንዳንዴ ግን ከፌስቡክ ዓለም ተላቀን ትክክለኛውን ዓለም መቀላቀል ሊያስፈልገን ይችላል፣ ሆኖም ግን ይህን ለማድረግ አብዛኞቻችን የፌስቡክ አድራሻችን እንዳይሰራ /deactivate/ ማድረግን ነው እንደ አማራጭ የምንጠቀመው።
ሆኖም ግን ፌስቡክን ዳግም መልሼ መጠቀም አልፈልግም የምንል ከሆነ ሙሉ በሙሉ አካውንቱን ማጥፋት /delete/ ማድረግ እንችላላን።
የፌስቡክ አድራሻችንን ሙሉ ለሙሉ ለማጥፋት ማድረግ ያለብን ቅደም ተከተሎች፦
ፌስቡክ ላይ ያሉንን መረጃዎች በሙሉ መሰብሰብ…
ፌስቡክን ቻው ብለን ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ከመሰናበታችን በፊት ያሉንን መረጃዎች ሰብስቦ መያዝ ይጠቅመናል።
ምክንያቱም ሌላ ቀን እነዚህ መረጃዎች ቢያስለፍገን እንኳ በቀላሉ ለማግኘት ስለሚረዳን ነው።
ይህን ለማድረግም Settings ውስጥ መግባት፤ General የሚለውን መጫን፤ በመቀጠል ከታች የሚመጣልንን Download a copy የሚለውን መምረጥ ይኖርብናል።
በዚሁ ጊዜ የሚመጣልንን My Archive መጫን፤ በሚመጣልን ስፍራ ላይ የፌስቡክ የይልፍ ቃል /password/ እንደ አዲስ በማስገባት ሰብሚት /Submit/ የሚለውን መጫን።
በዚሁ ጊዜም የፌስቡክ ኩባንያ በአካውንታችን ላይ ያለንን ሙሉ መረጃ በመሰብሰብ በፌስቡክ ላይ ባስመዘገብነው የኢሜይል አድራሻ አማካኝነት የሚልክልን ይሆናል።
የፌስቡክ አድራሻችንን እንዳይሰራ /deactivate/ ለማድረግ
ይህ ነገር ለበርካቶች ቀላል ሊሆን ይችላል፤ ሆኖም ግን የፌስቡክ አካውንታችን እንዳይሰራ ማድረግን አሁንም ቢሆን የማያውቁ ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ እና ይህንንም ጨምረን ልናካፍላችሁ ወደድን።
የፌስቡክ አድራሻችን እንዳይሰራ /deactivate/ ለማድረግ፦ ሴቲንግ /Settings/ ውስጥ መግባት፤ በስተቀኝ ከተዘረዘሩት ውስጥ /Account Ownership and Control / የሚለውን መጫን፤ ከሚመጡንል
ዝርዝሮች ውስጥ መጨረሻ ላይ ያለውን /Deactivation and Deletions/ የሚለውን መጫን ይጠበቅብናል።
ሁለት አማራጭ ይመጣልናል የመጀመሪያው / Deactivate account/ የሚል ሲሆን ይህንን ተጭነን password እንድናስገባ ይጋብዘናል ካስገባን በኋላ የፌስቡክ አካውንታችን እንደገና ከፍተን እስካልገባን ድረስ ይጠፋል ማለት ነው።
ሁለተኛው አማራጭ /Delete account/ የሚል ነው ይህንን ከተጫንን የሚጠይቀን ጥያቄ አለ አንዱን መርጠን continue to account deletion ስንጫን ብዙ አማራጮች ይመጣሉ አካውንታችን ከመጥፈቱ በፊት Download Your Information ከሚለው አማራጭ Download Info የሚለውን በመጫን የፌስቡክ ሙሉ መረጃችንን ማውረድ መቻል አለብን።
የፌስቡክ አድራሻንን ሙሉ በሙሉ ለማጥፋት /delete/ ለማድረግ
ይህንን በርካታ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች ለማወቅ የሚፈልጉት እንደሆነ ይታወቃል።
የፌስቡክ አድራሻንን ሙሉ በሙሉ ለማጥፋትም በመጀመሪያ ፌስቡካችን ውስጥ መግባት /Log into your Facebook account/።
በመቀጠልም በዚህ ሊንክ መግባት /https://
www.facebook.com/help/delete_account/
በመጨረሻም /Delete My Account/ የሚለውን በመጫን የፌስቡክ አድራሻ /አካውንታችንን ሙሉ በሙሉ ማጥፋት እንችላላን።
ይህንን ከማድረጋችን በፊት ግን እነዚህን ነገሮች ልብ ብንል
መጀመሪያ ፌስቡክ ላይ ያለንን ዳታዎች ሙሉ በሙሉ ኮፒ አድርገን መያዛችነን ማረጋጋጥ።
የፌስቡክ አድራሻችንን ሙሉ በሙሉ ካጠፋን በኋላ መልሰን ማግኘት ስለማንችል ከማጥፋታችን በፊት በደንብ አስበን መወሰን።
የፌስቡክ ኩባንያ በአካውንታችን ላይ ያሉ ፎቶግራፎች፣ መልእክቶች፣ ላይክ እና ኮሜንቶችን ሙሉ በሙሉ ለማጥፋት /delete/ ለማድረግ 90 ቀናት ነው የሚወስድበት።
በዚህ የ90 ቀናት ጊዜ ግን ማንኛውም ጓደኛችን ገጻችንን ከፍቶ ምንም መመልከት እንደማይችልም ተነግሯል።
ለጓደኞቻችን በቻት አማካኝነት የላክናቸው ፎቶግራፎች እና የፅሁፍ ምልእክቶች ግን አይጠፉም፤ ምክንያቱም ምልእክቱ የደረሳቸው ሰዎች የግል አካውንታቸው እስከሆነ ድረስ መረጃዎቻቸው የሚጠበቁ ይሆናል።
ስለዚህም የማንፈልጋቸውን ነገሮች ጓደኞቻችን እንዲያጠፉልን ማድረግ ይኖርብናል።
Share, Comment and like it. Lot’s of thanks!
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Telephone
Website
Address
Addis Ababa