Sbahe Tube

Sbahe Tube

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Sbahe Tube, Digital creator, Addis Ababa.

Photos from Sbahe Tube's post 02/06/2026

✍️ሐውለት አሕመድ እንደጻፈችው

ይቺም ሻማ ሰልችታለች‼️
===============

"በአገራችን ለሚቀጥሉት ብዙ አሥርት ዓመታት ምናልባትም አሁን በሕይወት የምንገኝ ሰዎች በአጠቃላይ ሳናይ የምንሞተው ነገር የመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ''ኃላፊነቴን በአግባቡ ስላልተወጣሁ ሥራዬን በፈቃዴ ለቅቄያለሁ፤ ከ'ኔ የተሻለ ሰው ይምራው'' የሚለው ነው።

በአርሲ ዞን በኦርቶዶክስ ክርስትና አማኞች እና አብያተ-ክርስትያናት ላይ በተደጋጋሚ ጥቃቶች እየተሰነዘሩ ብዙ ሰው በአሰቃቂ ሁኔታ ሞተ፤ አብያተ-ክርስትያናት እና ቅርሶችም ወደሙ፤ በነዋሪዎቹ ዘንድ ሥጋትና ጥርጣሬ ሰፈነ።

ይሄን ተደጋጋሚ ጥቃት ለማስቀረት የተሠራ ሥራ አለ? ሰላም ማስከበር 100% የክልሉ መንግሥት ሥራ አይደለም እንዴ? ምን አድርጓል? ሰላም ማስከበር ካቃታቸው በኢትዮጵያ ሕግ መሠረት ''አልቻልንም፤ የፌዴራል መንግሥት ጣልቃ ይግባልን'' ይባላል እኮ! መቼም ''እኔ ለዚህ ኃላፊነት ብቁ ሆኜ አልተገኘሁም፤ የተሻለ ብስለትና ልምድ ያለው ሰው ይተካኝ'' የሚሉ ኃላፊዎችን በሕይወት እያለን እንደማናይ እሙን ነው።

ሰው ባለቀ ቁጥር ይቺን ሻማ ብልጭ ማድረግ ምን ፋይዳ አለው? ይሰለቻል። የክልሉ መንግሥት ለዚህ ዞን ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ሕዝቡን ይጠብቅ። በጊዜ መፍትሔ ካልተሰጠው የዚህ ዳፋ የማይተርፈው ሰው የለም።

እንደ አንድ ተርታ ዜጋ በደረሰው ጉዳት ሐዘኔን ለመግለጽ እወዳለሁ።"

17/05/2026

" "
«ከአንቺ ጋር የመከረ ለራሱ መከረ»
እንዳለ ደራሲው፤ከነፍሳቸው ጋር የመከሩ፣ደጉ ሰው ደግነታቸው እንደቀጠለ ነው፣በቅርቡ በመሬታቸው ቤተክርስቲያን ሰርተው የሰጡ የመንግሥት ሚኒስቴሩ ደግነት እና የቤተክርስቲያን ፍቅር ቀጥሏል።

◉.የፖለቲካው ገመድ አሥሮ ያላስቀራቸው የክርስቶስና የቤተክርስቲያን ወዳጅ ሚኒስትሩ 🙏🙏
በክብር እና በአገልግሎት ስማቸው ሊቀ ሂሩያን ዲ/ን ተክለወልድ አጥናፉ የቀድሞው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ እና በአሁኑ ወቅት የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማክሮ ኢኮኖሚ አማካሪ በደግነታቸው ብዙዎችን እያነጋገሩ ይገኛሉ።

በወላይታ ዞን በዳሞት ጋሌ ወረዳ ቤተክህነት ቦዲቲ ከተማ አዲስ #በመጠናቀቅ ላይ ላለችው ለቦዲቲ ምሥራቀ ፀሐይ ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተክርስቲያን መስርያ የሚሆን ብር ገቢ አድርገዋል እግዚአብሔር ይስጥልን።

እግዚአብሔር ይጠብቅልን በነፍስ በስጋም።

እንዲህ ያሉትን አስተዋይና ደጋግ ሰዎች እግዚአብሔር ደያብዛልን በእውነት 🙏👏
Via Andualem Andualem Degefu

01/05/2026

◉.እኝህ አባት አዲስ አበባ ውስጥ ጋርመንት አቅጣጫ ስሄድ ፤ ጋርመንት ዐደባባይ ሳይሻገር ከአስፓልቱ በቀኝ በኩል #ፕላን _ኮፒ _ብሉ_ፕሪንት ከሚል ሕንፃ ሥር አሁን በዚህ ሰዓት ከልጃቸው ጋር መንገድ ዳር ተቀምጠው በመለመን ላይ የሚገኙ ናቸው።

◉.ትራንስፖርት ውስጥ ሆኘ እያለፍኩ ድንገት በካሜራዬ አስቀርቻቸው ነው ።

◉.እውነተኛ ካህናት በችግር ጅራፍ እየተገረፉ ነው ። እባካችሁ አካባቢው ላይ የምትገኙ ልባም ኦርቶዶክሳዊያን ምእመናን በአካል ቦታው ላይ ሄዳችሁ አግኟቸውና እንርዳቸው ።
Please 🙏🙏🙏

06/04/2026

አምላከ መምህራን በዕድሜና በጤና ይጠብቅልን🙏

✞ በሰሙነ ሕማማት ይህንን አድርጉ ✞
( በሊቀ ሊቃውንት ስምዐ ኮነ መልአክ )
————————————
ለኹሉም እንዲዳረስ ሼር ይደረግ !

ሰሙነ ሕማማት አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለዓለም ሁሉ ቤዛ ሆኖ ተላልፎ መሰጠቱን የምናስታውስበት ሳምንት ነው።

ይህንን ምክንያት በማድረግ የሥርዓት ለውጥ ሲደረግ ሲመለከቱ ግራ የሚጋቡና ሥርዓተ አምልኮውን በሚገባ ከመከታተል ይልቅ ሥርዓት የጣሱ እየመሰላቸው የሚጨነቁ ስላሉ ልናደርገው የሚገባንን እጽፍላችኋለሁ።

1️⃣. በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ብሎ ፊትንና መላ ሰውነትን በትዕምርተ መስቀል {በመስቀል ምልክት} ማማተብ አይከለከልም። ከካህን እጅ ቡራኬ አንቀበልም በካህኑ እጅ ያለውን መስቀል አንሳለምምና ማማተብም የለብንም በሚል ፍልስፍና ካልሆነ ማማተብ ክልክል ነው ተብሎ የተጻፈበት ቦታ የለምና።

2️⃣. የሚከለከል ጸሎት የሌለ መሆኑን አውቃችሁ ያስለመዳችሁትን ጸሎት በትጋት ጸልዩ። መሥዋዕት ካለመሠዋታችን ቅዳሴ ካለመቀደሳችን በቀር በዚህ ሳምንት ከብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ጀምሮ እስከ ሊቃውንት ድርሳናት ድረስ በቤተ ክርስቲያን የማይጸለይ ጸሎት የለምና።

3️⃣. ሰላምታ መስጠት ከጸሎተ ሐሙስ ዕለት በቀር አልተከለከለም፤ እሱም ቢሆን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በይሁዳ ሰላምታ ተላልፎ መሰጠቱን ለማስተዎስ እንጅ ሌላ የተለየ ምክንያት ስለሌለው በመርሳት ወይም በሌላ ከድፍረት በተለየ ምክንያት ሰላምታ ያቀረበላችሁን ሰው ልታስደነግጡና ትልቅ ኃጢአት እንደሠራ አድርጋችሁ ልታስጨንቁት አይገባም።

4️⃣. “በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ አምላክ” ብሎ መጻሕፍትን ማንበብ ወይም ሌላ ሥራን መጀመር ይቻላል። ስመ እግዚአብሔር መጥራት የምንከለከልበት ጊዜ መቸም የለምና።

5️⃣. የጌታችንን ሕማሙንና ሞቱን የሚያስታውሱ መጻሕፍትን በማንበብና በመስማት ጊዜአችንን መወሰን ይገባናል።

6️⃣. በዚህ ሳምንት ተድላ ደስታን ሲያደርጉ መገኘት ከአይሁድ ጋር እንደ መተባበር የሚያስቆጥር ስለሆነ አብዝቶ በመብላትና በመጠጣት፣ ያማረውንና ጌጠኛውን ልብስ በመልበስ፣ ባልና ሚስት በምንጣፍ በመገናኘት እንዲሁም በልዩ ልዩ ምክንያት ከምናደርጋቸው ተድላ ደስታዎች መራቅ ይገባናል። ቅዱሳን በዘመናቸው ሁሉ ባሰቡት ጊዜ የሚያስጨንቃቸውን የክርስቶስን መከራ እያሰብን ለጥቂት ጊዜም እንኳን ቢሆን የክርስቶስን መከራ በሰውነታችን ማሰብ ይገባናል።

የተቻለው እንደ ጴጥሮስ የራሱን ኃጢአት እያሰበ እንደ ማርያም መግደላዊት የክርስቶስን ሞት እያዘከረ ሊያለቅስ ይገባዋል።
በወዲያኛው ዓለም ከማልቀስ የሚያድነን ዛሬ የራሳችንን ኃጢአት አስበን የክርስቶስን ሞት አዘክረን የምናለቅሰው ለቅሶ ነው እንጅ ዛሬ ከተደሰትን ደስታችንን በዚህ ዓለም ማድረጋችን አይደለምን?

7️⃣. በተቻለን መጠን በቤተ ክርስቲያን መዋል ይገባናል፤ ሕማማተ መስቀልን የሚያስታውሱ መጻሕፍት የሚነበቡበት ሳምንት ስለሆነ ነው። ነገር ግን በልዩ ልዩ ምክንያት በቤተ ክርስቲያን መዋል እንኳን ባይቻላችሁ ባላችሁበት ቦታ ሁናችሁ እየዋሻችሁ በሐሰት የከሰሱትን፣ እየቀማችሁ ልብሱን የገፈፉትን፣ ሰው እየደበደባችሁ በጅራፍ የገረፉትን፣ በወንድሞቻችሁና በእኅቶቻችሁ ላይ እየፈረዳችሁ በክርስቶስ ላይ የፈረዱበትን፣ በሰዎች ላይ እየተዘባበታችሁ የተዘባበቱበትን፣ በሳቅና በሽንገላ ሰውን እየሸነገላችሁ ሽንገላ በተሞላበት ሰላምታ ጌታውንና መምህሩን አሳልፎ የሰጠ ይሁዳን ልትመስሉ አይገባም።

ይልቁንም በአይሁድ እጅ ተላልፎ ቢሰጥም ንጹሓ ባሕርይ መሆኑን በማመን እስከ ቀራንዮ የተከተሉትን ደቀመዛሙርት ልትመስሉ ይገባል። እግራችሁ በመቅደሱ ውስጥ ባይቆምም ልባችሁን ከመቅደስ ልታወጡት አይገባም። እያዘናችሁ ባላችሁበት ቦታ ዋሉ።

8️⃣. በቤታችሁም ሆነ በቤተ ክርስቲያን አብዝታችሁ ስገዱ። ስለሁላችንም ቤዛ የሚሆን ክርስቶስ በፊታችን መስቀል ተሸክሞ ሲወድቅ እያያችሁት ትቆማላችሁን? አይሁድ ገፍተውት አንድ ጊዜ ወደ ምድር በወደቀ ጊዜ ለወደቀው መውደቅ ዘመናችንን ሙሉ ብንወድቅ ብንነሣ ውለታ መክፈል እንችል ይመስላችኋል?
ቅዱሳን ሳያቋርጡ ሲሰግዱ የሚኖሩት ክርስቶስ በፊታቸው በአይሁድ እጅ እየተገፋ መስቀሉን እንደተሸከመ ሲወድቅ በዓይነ ሕሊናቸው ስለሚያዩት ነው።
በስንክሳር ተጽፎ የምናገኘው ዜና ሞታቸው እየሰገዱ ሳሉ ሞት ነፍሳቸውን ከሥጋቸው ለይቶ እንደሚወስዳትና ለስገደት ታጥቀው እንደተንበረከኩ እንደሚገኙ ይነግረናል። የተሰቀለውን ክርስቶስን የሚያስብ ሰው ለሰውነቱ ዕረፍትን አይሻም።

9️⃣. ከሁሉም ሰው ጋር ፍቅርን አድርጉ። ሰውን ለመውደድ ምክንያት አታብጁ። ክርስቶስ አሳልፎ የሰጠውን ይሁዳን “ወዳጄ” ብሎ ሲጠራው አትሰሙትም?

እግዚአብሔርን አንተን ያለ ምክንያት እንደ ወደደህ አንተም ያለ ምክንያት ሰውን መውደድ ልመድ። ክርስቶስ አንተን ጠላቱ ሆነህ ሳለ ፍቅርን ካላጎደለብህ ለጠላትህ ፍቅርን አታጉድልበት።

ክርስቶስ ይሁዳን ‘’ወዳጀ’’ ብሎ ከጠራው አንተም ይሁዳዎችህን ወዳጀ ብለህ ጥራቸው። አውቃለሁ ጠላትን መውደድ መራራ ሐሞትን ከመጠጣት በላይ መራራ ነው። ነገር ግን እኔም ለይሁዳዎቻችን ፍቅርን እንስጥ ማለቴ መራራ ሐሞት የጠጣ ክርስቶስን እንድንመስለው ነው።

1️⃣0️⃣. ለሁሉም መስጠት በምትችሉት መጠን ስጡ እንጅ አትቀበሉ። ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ብፁዕ ነውና በመስጠታችሁ ብፁዓን ተብለው ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ከሚገቡት ትቆጠራላችሁ።

ምናልባትም የምትሰጡት ገንዘብ ባይኖራችሁ ዕዳ ይሆንባችሁም ቢሆንም ገንዘብ ለሰጧችሁ ባለጠጎች የምትሰጡት ጸሎት ሊኖራችሁ ይገባል። ከምንጊዜውም የበለጠውን ስጦታ የተቀበልንበት ሳምንት መሆኑን እያሰባችሁ አንዳች የምጸጡት ሥጋዊም ሆነ መንፈሳዊ ስጦታ የሌላችሁ ባዶዎች እንዳትሆኑ ተጠንቀቁ።

ከሁሉ በላይ የሆነውን ስጦታ የጌታን ሥጋና ደም እነሆ ተቀብለናል።

ክርስቶስ መድኃኒነ
መጽአ ወሐመ በእንቲአነ
ወበሕማማቲሁ ቤዘወነ‼

( ሊቀ ሊቃውንት ስምዐ ኮነ መልአክ )
የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት የሊቃውንት ጉባዔ ሰብሳቢ
የዐራቱ ጉባዔያት ምስክር መምህር

Photos from Sbahe Tube's post 09/02/2026

❝ማዕከለ አሥዋክ ዘጸገዬ ጽጌ ሃይማኖት ❞
“በእሾኽ መካከል ሆኖ የሃይማኖት አበባ ያፈራ የዘመናችን ድንቅ ሰው!!!!”
⛪️⛪️⛪️⛪️ እልልልልል መታደል ነው!!!!
*****************************************
◉.በሥጋዊ ዓለም እየኖሩ ነፍስን ማንገሥ እንደዚህ ነው።
◉እግዚአብሔርንና ቅድስት ቤተክርስቲያንን ያከበረ ከነፍሱ ጋር የመከረ ብልህ ሰው ነው።

◉.የቀድሞ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ዝምተኛው ምሁር እና አሁን ላይ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚንስትር ማክሮ ኢኮኖሚ ጉዳዮች አማካሪ የሆኑት #ክቡር አቶ ተክለወልድ አጥናፉ

◉.ወላይታ ሀገረስብከት ቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ሄምበቾ ከተማ ላይ ባላቸው የግል ይዞታቸው ላይ በ18 ወር ጊዜ የቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ሰርተው አስረክበዋል።

እግዚአብሔር ይመስገን🙏🙏🙏

28/01/2026

ለልጇ ስትነግረው ሞት እንደምትፈራ
ወሰዷት በሐሴት መላእክተ ሐራ።
፨፨፨፨
፨፨፨፨፨፨፨፨
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ/፪/
ሞታ ለማርያም የዓፅብ ለኲሉ
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
እንኳን አደረሳችሁ ❤❤❤

18/01/2026

እንኳን "ለከተራ" በዓል አደረሳችሁ!!

07/01/2026

አማን በአማን/፪/
መንክር ስብሐተ ልደቱ

‟ቤዛ ኲሉ ዓለም ዮም ተወልደ ዘይከውን ፍስሐ ለኲሉ

ለሁሉም ፍጥረት የደስታቸው ምንጭ የሚሆን የዓለሙ ቤዛ አማኑኤል ዛሬ በቤተልሔም ዋሻ ተወለደ❤❤❤
‟እሰይ እሰይ ተወለደ የዓለም መድኃኒት ❤❤❤

እንኳን አደረሳችሁ!!!

05/01/2026

❝ ❞
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ከልዕልና ሥፍራህ ወርደህ እንደ ድኃ በከብቶች በረት መተኛትህ በጨርቅ መጠቅለልህ ሰውን ስለመውደድህ ነው።

◉.ልብስህ እሳት መጎናጸፊያህ እሳት የሆንክ ጌታ በብርዱ ወራት የእንስሳት እስትንፋስ መሻትህ ይኽ ሁሉ ሰውን ስለመውደድህ ነው።

◉.እንደ ሽፍታ ወንበዴ በሽፍቶች እጅ ተይዘህ ለፍርድ መቅረብህ ሰውን ስለመውደድህ ነው!!

◉.መላእክት ደፍረው ማየት የማይችሉት ፊትህ ላይ የመርገም ልጆች አይሁድ ምራቃቸውን ሲተፉብህ ዝም ማለትህ ይኽ ሁሉ ሰውን ስለመውደድህ ነው።

◉.ከሊቶስትራ እስከ ቀራንዮ እየወደቅክ እየተነሳህ መስቀሉን ተሸክመህ መጓዝህ ሰውን ስለመውደድህ ነው።

◉.በዕለተ ዓርብ ነፍስህን አሳልፈህ እስከመስጠት የተቀበልከው መከራ ይኽ ሁሉ ሰውን ስለመውደድህ ነው።

◉.ሙታንን ከመቃብር የምታነሣ አምላክ ወደ መቃብር መውረድህ ሰውን ስለመውደድህም አይደል?

◉.ጌታ ሆይ!! ሰው ግን ምን ቢያደርግልህ ነው እንዲህ መውደድህ?
◉.ሕግ ያፈረሰው ሰው፣ሆኖ ሳለ
◉.የምትወለድበት ሥፍራ የከለከለህ ሰው ሆኖ ሳለ
◉.ወደ ግብጽ በረኻ በሕጻንነትህ ለስደት ያበቃህ ሰው ሰው ሆኖ ሳለ
◉.አሳልፎ ለሞት የሰጠኽ ሰው ሆኖ ሳለ
◉.በመስቀል ላይ በችንካር ቸንክሮ የሰቀለህ ሰው ሰው ሆኖ ሳለ
◉.ወደ መቃብር ያወረደህ ሰው፣መቃብርህን በወንበዴዎች ያስጠበቀ የሰው ልጅ ሆኖ ሳለ ሰውን እጅግ መውደድህ እንደምን ያለ ፍቅር ነው!!!
◉.ይኽንን ሊመረምር ኅሊናዬ በነፋስ አውታር ተጭኖ ወደ ላይ አየር ወጣ ወደ ጥልቁም ወረደ፡ከአድማስ እስከ አድማስ ተሽከረከረ የፍቅርህን መጠን ግን ሊደርስበት አልቻለምና አቅቶት ወደ ቀደመ አኗኗሩ ይመለሳል።

Want your business to be the top-listed Media Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Address

Addis Ababa