Afar forces
🌎 አለም ከጉልበተኞችና ከአሸናፊዎች ጋር ናት..‼️
"ፈጣሪ ግን ምንግዜም ከተበዳዎች ጎን ነው 🇵🇸✅
02/06/2026
▪በዚህ ምስል ላይ እንደምንመለከተው ፤ በገጠራማው የአፋር ክልል የምርጫ ኮሮጆዎችን በግመል ጭኖ በበረሃማው መንገድ ሲጓዝ የምናየው ትዕይንት፣ ከአንድ ተራ ፎቶግራፍ የዘለለ እጅግ ጥልቅ የሆነ መልዕክት አለው። 🗳️
ይህ ምስል የነቃ ማህበረሰብን፣ ጽናትን እና የሀገር ፍቅርን በአንድ ላይ አጠቃልሎ የያዘ ህያው ማሳያ ነው።🗳️
ስለ አፋር ህዝብ ስናወራ ማስታወስ እና ማድነቅ የሚገባን በርካታ እውነታዎች አሉ...
የአፋርን ህዝብ ድምፁን ከመስጠት እና መፃኢ እጣፈንታውን ከመወሰን አላገደውም።
ዘመናዊውን የምርጫ ስርአት ከነባሩ የኑሮ ዘይቤው (ከግመል ጉዞ) ጋር አዋህዶ መብቱን ሲያስከብር ማየት፣ ማህበረሰቡ ምን ያህል ለዴሞክራሲያዊ መብቱ ቁርጠኛ እና የነቃ መሆኑን ይመሰክራል።
አፋር ከጥንት ጀምሮ የራሱ የሆነ የዳበረ የማህበራዊ አስተዳደር እና የፍትህ ስርአት ያለው ስልጡን ማህበረሰብ ነው። ባህላዊው የፍትህ እና አስተዳደር ስርአት (ማዳዓ) ዛሬም ድረስ ማህበረሰቡን በሰላም፣ በፍትህ እና በእኩልነት የሚያስተዳድር የረቀቀ የጥበብ ማሳያ ነው።🗳️
ምስሉ ላይ ያለው አባት የምርጫ ኮሮጆዎቹን በግመል ጭኖ መሳሪያውን አንግቦ በኩራት ሲጓዝ ማየት፣ የአፋር ህዝብ ለሀገሩም ሆነ ለመብቱ ዘብ የሚቆም ጀግና መሆኑን ያሳያል።
ተፈጥሮ የፈተነችውን አካባቢ በፅናት ተቋቁሞ፣ ከዘመኑ ጋር እኩል እየተራመደ ያለ ድንቅ ህዝብ ነው። 🗳️
ባጠቃላይ ይህ ምስል ትልቅ ትርጉም አለው። የአፋር ህዝብ ትዕግስቱ፣ እንግዳ ተቀባይነቱ፣ ባህሉን አክባሪነቱ እና ለሀገር ያለው ጥልቅ ፍቅር ሁሌም የሚያስደንቅ ነው።
የጥንት እሴቶቹን ሳይለቅ፣ የዘመናዊነትን እና የዴሞክራሲን ጎዳና በራሱ መንገድ እየተጓዘበት መሆኑ ክብር ይገባዋል።
ክብር ለዚህ ታላቅ፣ ስልጡን እና የነቃ ማህበረሰብ!
Like Share Repost 🙏
Viv Abdulfetah Mohammed
#አፋር #ኢትዮጵያ #ምርጫ #ዴሞክራሲ #ስልጣኔ
22/05/2026
ተፅዕኖ ፈጣሪው ኢትዮጵያዊው ቲክቶከር አዶናይ, .ለጉብኝት ወደ አትዮጵያ የመጣውን ከ19 ሚሊዮን በላይ ተከታይ ያለው ተፅዕኖ ፈጣሪው ቲክቶከር ን ወደ ሰው ዘር መገኛና የተለያዩ ፕላኔቶች ባለበት ወደሆነች ወደ አፋር ይዞት እንዲመጣ ጥሪያችንን እናቀርባለን ..🙏
ምክንያቱም አፋር ክልል ቢመጣ በዓለም ላይ ልዩ የሆኑ ብዙ አስደናቂ የተፈጥሮ እና የታሪክ ቦታዎችን መጎብኘት ይችላል። ከነዚህም መካከል ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው፦
ኤርታሌ (Erta Ale): በዓለም ላይ ካሉ ጥቂት ንቁ እሳተ ገሞራዎች (active volcanoes) አንዱ ነው። በተለይ ማታ ላይ የሚታየው የሚንቀለቀል የእሳት ሃይቅ (Lava Lake) እጅግ ማራኪ እና አስደናቂ ትዕይንት ነው።
ዳሎል እና የዳናኪል ስምጥ ሸለቆ (Dallol / Danakil Depression): ከባህር ወለል በታች የሚገኝ እና በዓለም ላይ ካሉ እጅግ ሙቀት የበዛባቸው ቦታዎች አንዱ ነው። እዚህ ቦታ ላይ በሚያማምሩ የተፈጥሮ ቀለማት ያሸበረቁ የፍል ውሃ ምንጮችን፣ የድንጋይ ቅርፆችን እና ሰፊ የጨው ሜዳዎችን ማየት ይቻላል።
ሀዳር (Hadar - የሉሲ መገኛ): ታዋቂዋ የ3.2 ሚሊዮን ዓመት እድሜ ያላት የ"ድንቅነሽ" (ሉሲ) ቅሪተ አካል የተገኘችበት ታሪካዊ ቦታ በመሆኑ፣ ለታሪክ እና ለቅሪተ አካል ጥናት አፍቃሪዎች ተመራጭ ነው።
አፍሬራ ሐይቅ (Lake Afrera): በዳናኪል ሸለቆ ውስጥ የሚገኝ እጅግ ጨዋማ የሆነ ሀይቅ ሲሆን፣ ባህላዊ እና ዘመናዊ የጨው ማውጣት ሂደትን ለመመልከት እንዲሁም በሀይቁ ላይ ለመዝናናት አመቺ ነው።
የአዋሽ ብሔራዊ ፓርክ (Awash National Park): ምንም እንኳን ፓርኩ በኦሮሚያ እና አፋር ክልሎች አዋሳኝ ላይ ቢገኝም፣ በአፋር በኩል ያሉትን የዱር እንስሳት (እንደ ሳላ፣ የሜዳ አህያ እና አእዋፋት) እንዲሁም የተፈጥሮ ፍል ውሃዎችን እና የአዋሽ ወንዝ ፏፏቴን መጎብኘት ይቻላል።
የአፋር ህዝብ ባህል እና የጨው ጉዞ (Afar Culture and Salt Caravans): በመቶዎች በሚቆጠሩ ግመሎች የሚደረገውን ጥንታዊ የጨው ማጓጓዝ ሂደት እና የእንግዳ ተቀባዩን የአፋር ህዝብ ልዩ ባህል፣ አኗኗር እና አለባበስ በቅርበት ማየት ሌላው ትልቅ የጉብኝቱ አካል ነው።
:
:
:
🔥🏜️ Visit Afar Ethiopia
09/05/2026
በነዳጅ የሚሰሩ እና ከ250 ሚልዮን ዶላር በላይ ግምት ያላቸው ተሽከርካሪዎች ጅቡቲ ላይ ከጥቅም ውጪ እየሆኑ ነው ተባለ!!
በጠ/ሚሩ የተላለፈውን ክልከላ በመጣስ ተሽከርካሪዎቹን ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባትና የፈቃድ ደብዳቤ ለማግኘት ለእያንዳንዱ እስከ አንድ ሚሊዮን ብር የሚደርስ የጉቦ ክፍያ እየተጠየቀ መሆኑ ታወቀ።
(መሰረት ሚዲያ)
09/05/2026
አፋር ጊዜው አሁን ነው!
የአፋር ምድር የሰው ልጅ መገኛ ብቻ ሳትሆን፣ የተፈጥሮ ድንቆችና ያልተገደቡ የኢኮኖሚ ዕድሎች መናኸሪያ ናት።
ዛሬ በአላሎባድ ፍልውሃ ላይ የታየው ዘመናዊ መሠረተ ልማት፣ ክልሉ የነበረውን "የተፈጥሮ ፀጋ" ወደ "ኢኮኖሚያዊ ስኬት" ለመቀየር የጀመረው ጉዞ ማሳያ ነው።
ይህ በአፋር ክልል በአላሎባድ ፍልውሃ ላይ የተጀመረው አዲስ የቱሪዝም ምዕራፍ፣ ለክልሉ ብቻ ሳይሆን ለኢትዮጵያም አዲስ የኢኮኖሚ ሞተር የመሆን ትልቅ ተስፋ አለው።
G-24 News Media ለኢንቨስተሮች የሚሆን፣ የክልሉን ፀጋዎች የሚያስተዋውቅና ጥሪ የሚያስተላልፍ ልዩ ትንታኔ እና የኢንቨስትመንት ጥሪ እነሆ ብሏል፦
አላሎባድ ተፈጥሯዊ ትኩስ ፍልውሃዎቹ እና አስደናቂ ቀለማቱ ለዓይን ማራኪ ብቻ ሳይሆኑ፣ ለጤናና ለፈውስ (Wellness Tourism) ትልቅ አቅም አላቸው።
ዘመናዊ መስተንግዶን ከተፈጥሮ ውበት ጋር አጣምሮ መያዙ፣ ዓለም አቀፍ ጎብኚዎችን ለመሳብ የሚያስችል "ደረጃውን የጠበቀ መዳረሻ" ያደርገዋል።
# አፋር ለምን ለኢንቨስትመንት ተመራጭ ናት?
አፋር "ያልተነካው ምድር" (The Untouched Frontier) ተብላ የምትጠራው ያለምክንያት አይደለም፦
* ቱሪዝም፦ ከኤርታ አሌ የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ እስከ ዳሎል አስደናቂ ቀለማት፣ ከአዋሽ ብሔራዊ ፓርክ እስከ አላሎባድ ፍልውሃዎች ድረስ ዓለምን ሊያስደንቁ የሚችሉ መዳረሻዎች ባለቤት ናት።
* ታዳሽ ኃይል፦ ክልሉ ለጂኦ-ተርማል (Geothermal) እና ለፀሐይ ኃይል ኢንቨስትመንት እጅግ ምቹ የሆነ መልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ አለው።
* ግብርና እና ማዕድን፦ ለሰፊ መስኖ ልማት የሚሆኑ ሰፋፊ መሬቶች እና የፖታሽ (Potash) ጨው ክምችት ለኢንዱስትሪ ባለቤቶች ትልቅ ዕድል ነው።
# "መቻል" የታየበት የአፋር ሕዝብ ፅናት!
የአፋር ሕዝብ በታሪክ ጠንካራ፣ እንግዳ ተቀባይና ሰላም ወዳድ ነው።
አሁን ላይ የታየው የመሪዎችና የሕዝቡ ቅንጅት፣ ክልሉን ወደ ሰላምና ልማት ቀጠናነት እየቀየረው ይገኛል። ይህ "መቻል" ለኢንቨስተሮች አስተማማኝ ዋስትና ነው።
# ለኢንቨስተሮች የቀረበ ጥሪ፦
"አፋር ጊዜው አሁን ነው!"
ለሀገር ውስጥና ለውጭ ኢንቨስተሮች በሙሉ!
ያልተዋወቀው የአፋር ቱሪዝም፣ ያልታረሰው መሬት እና ያልተቀዳው የተፈጥሮ ሃብት የእናንተን ኢንቨስትመንት ይጠብቃል።
በአፋር ክልል ኢንቨስት ማድረግ ማለት፦
1.በአጭር ጊዜ ትርፋማ መሆን፦ ያልተነኩ ዘርፎች ላይ ቀዳሚ መሆን።
2.ታሪክ መስራት፦ የሰው ልጅ መገኛ የሆነችውን ምድር ወደ ዓለም አቀፍ የቱሪዝም ማዕከልነት መቀየር።
3.የተመቻቸ ድጋፍ፦ የመንግሥትና የሕዝብ ትብብር ያለበት ምቹ ሁኔታ።
ኑ! በአፋር ምድር ላይ አሻራዎን ያኑሩ። አፋር ዛሬም ነገም ለስኬት ክፍት ናት።
# የ G-24 News Media መልዕክት!
እኛ በ G-24 News Media የአፋር ክልል እያሳየ ያለውን ይህን ፈጣን ለውጥ በታላቅ ኩራት እንዘግባለን።
ክልሉ ካለው ጂኦ-ፖለቲካዊ ጠቀሜታና ስትራቴጂካዊ ቦታ አንጻር፣ የአፋር መልማት የኢትዮጵያ ብልጽግና ዋስትና ነው።
09/05/2026
አቶ ያደታ/ሙራድ ጁነይዲ የብራይተን ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግል ማህበር ባለቤት ከሌሎች ወንድም ባለሃብቶች ጋር በመሆን በከ27 አመታት የውጭ ሃገር ስደት ቆይታ በኃላ ወደ ሃገር ቤት ለተመለሱት ለመጀመሪያው የኦሮሚያ ክልልዊ መንግስት ፕሬዚዳንት ክቡር አቶ ሃሰን አሊ ኢብራሂም ዘመናዊ መኖሪያ ቤትና ተሽከርካሪ በስጦታ መልክ አበርክተውላቸውል።
ክብር ለሚገባው እንዲህ በክብር ክብር ሲሰጠው እጅግ ደስ ይላል: ምስጋና ለባለፀጋው የሃገር ባለውለታው ለአቶ ያደታ/ሙራድ ጁነይዲ🙏
በ Negash Qemant
06/05/2026
🇮🇷 የኢራን ፓርላማ አፈ-ጉባኤ ሙሀመድ ባገር፡-
ሌላ ወታደራዊ ጥቃት የመከሰቱ እድል ጨርሶ ዝቅተኛ እንደሆነ አድርገን አንቆጥረውም፣ በተለይም የሽብር ጥቃቶች እና የውስጥ ክፍፍል የመከሰት እድሉ ዝቅተኛ ነው ብለን አናስብም። ለዚህም ጥንቃቄ ማድረጋችንን እንቀጥላለን።
የተከበረው የኢራን ሕዝብ ምንም ያህል ከባድ የኢኮኖሚ ጫና ቢገጥመውም ለእምነታችን ሲል እነዚህን ችግሮች ይቋቋማል።
05/05/2026
ሰበር‼️
በህግ የተሰጠኝ የህዝብ አደራ በዘር የተደራጀው የህወሓት ቡድን የተከፈለ መስዋእትነት እከፍላለሁኝ እንጂ ማህተምና ቁልፍን አላስደፍርም። እኔ እንደ ጌታቸው ረደ መምህር ሳልሆን ወታደር ነኝ"።
ጀንራል ፕሬዚዳንት ታደሰ ወረደ
05/05/2026
ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል የትግራይ ክልል ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ!
ዛሬ በተካሄደው 6ኛው ዘመን 6ኛው መደበኛ የትግራይ ምክር ቤት ጉባኤ ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል በአብዛኛው ድምፅ የክልሉ ፕሬዝዳንት ሆነው በይፋ ተመርጠዋል።
በዚሁ ስብሰባ ላይ ወይዘሮ ኪሮስ ሐጎስ አፈ-ጉባኤ፣ ወይዘሮ ምህረት በርሄ ደግሞ ምክትል አፈ-ጉባኤ ሆነው ተሰይመዋል።
ምክር ቤቱ ስራውን በይፋ የጀመረው የፕሪቶሪያው ስምምነት በፌደራል መንግስቱ በኩል ተጥሷል በሚል ሲሆን፣ አዲሱ ፕሬዝዳንትም እስከ ቀጣዩ ስብሰባ ድረስ በአስፈፃሚው አካል ላይ አስፈላጊውን ማስተካከያና ሹመት እንዲያደርጉ ሙሉ ስልጣን ተሰጥቷቸዋል።
ይህ እርምጃ በትግራይ ፖለቲካዊ መድረክ አዲስ ምዕራፍ የከፈተ ሲሆን፣ ከፌደራል መንግስቱ ጋር ያለውን ግንኙነት ወዴት ሊያመራው እንደሚችል የብዙዎች መነጋገሪያ ሆኗል።
02/05/2026
, ቃሉ በInstagram ገጹ 1m ተከታዮችን በማግኘቱ ደስታውን ለደጋፊዎቹ ጋር ለማክበር (Celebration) በዝግጅት ላይ ነበር።
ነገር ግን ነገሮች ከሱ እቅድ በላይ ሆኑ! በአንድ ለሊት በለቀቃት አንዲት "Viral" የሆነች ቪድዮ ብቻ ተከታዩ ከ1m ተነስቶ 2.4m ላይ አልፏል።
ይህንን ድንገተኛ ለውጥ የተመለከተው ቃሉ በገጹ ላይ
"ቀደማችሁኝ!"
ሲል በፈገግታ ስሜቱን አጋርቷል። እሱ ለ1m ሲዘጋጅ፣ አድናቂዎቹ ግን በድንቅ ጥበቡ ተማርከው ከ2 ሚሊዮን በላይ አደረሱት።
ይሄም የመጀመርያዉ ኢ/ያዊ በInstagram 2.5m በላይ ተከታይ ያለው ሁኖ ሪከርዱን ሰብሯል።
01/05/2026
የቀድሞ የኔቶ አዛዥ አሜሪካዊው ጄኔራል ዌስሊ ክላርክ፡-
በኢራን ጥቃቶች ለመተካት በጣም አስቸጋሪ የሆኑ ራዳሮችን አጥተናል። በአሁኑ ጊዜ የቶማሃውክ ሚሳኤሎች ክምችት ከ50% በታች ወርዷል።
አንድ ሶስተኛ የሚሆነውን የባለስቲክ ሚሳኤል መጥለፍ አቅማችንን እና ግማሽ የሚሆነውን የከፍተኛ አቅም "THAAD" ሚሳኤሎችን ክምችት አጥተናል።
እነዚህን ሚሳኤሎች በአንዳንድ ሁኔታዎች መልሶ መተካት በርካታ ዓመታት ይወስዳል።
ከኢራን ጋር በተደረገው ጦርነት ለቦምቦች የወጣው 25 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል፣ ነገር ግን ይህንን መሳሪያ ማምረት እና መተካት ከገንዘቡ የበለጠ ከባድ ነው።
Click here to claim your Sponsored Listing.