Wollo Times

Wollo Times

Share

https://t.me/ethifirst ኑ ተከተሉን ስለ ሐገራችን እና አለም አቀፍ የሆኑ ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ጉዳዮች የተጣራ መረጃ ያገኛሉ ። ስለተከተሉን ለእርስዎ ትልቅ አክብሮት አለን !! እናመሰግናለን

09/05/2026

ማንኛውንም መስዋዕትነት በመክፈል የኢትዮጵያን እና የህዝቦቿን ራዕይ ዕውን ለማድረግ ዝግጁ ነን።
ሌተናል ጄኔራል ዘውዱ በላይ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሚያዚያ 29 ቀን 2018 ዓ.ም

ኢትዮጵያ እና ህዝቦቿ መጪዎችን ጊዜያት ዕውን ለማድረግ ቀጣይነት ያለው የማደግ እና የመልማት ፍላጎቶችን ለማሳካት ያስችላት ዘንድ በዲሞክራሲያዊ መንገድ ለምታኖራቸው መሠረቶች ማንኛውንም መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ ነን ሲሉ የማዕከላዊ ዕዝ አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ዘውዱ በላይ ገልፀዋል።

በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ተልዕኮውን እየፈፀመ የሚገኘውን የማዕከላዊ ዕዝ ጋሻ ኮር አይበገሬ ክፍለጦር በጠላት ላይ የተጎናፀፋቸውን ድሎች በተመለከቱበት ወቅት በቀጠናው አንፃራዊ ሰላም እንዲሰፍን ላደረጉ የሰራዊት አመራሮችና አባላት እንዲሁም የመስተዳድር አካላት ምስጋና አቅርበዋል።

በማዕከላዊ ዕዝ የጋሻ ኮር አዛዥ ብርጋዲየር ጄኔራል ጥላሁን ዱጋሳ የባዕዳን ተልዕኮ ፈፃሚ ሀይሎች በምዕራብ ሸዋ ዞን በመንቀሳቀስ ህዝቡን ለእንግልት ሲዳርጉ የነበሩ የሸኔ ቡድንና ፅንፈኛውን ሀይል ከዞኑ ማፅዳት ችለናል ብለዋል።

የጋሻ ኮር የሰራዊት አባላት በጠላት ላይ የበላይነትን በመውሰድ በቀጠናው ለህዝብ አገልግሎት የሚሰጡ የመንግስት ተቋማት መደበኛ ስራቸውን በመከወን ላይ መሆናቸውን የገለፁት ብርጋደር ጄኔራል ጥላሁን ዱጋሳ ፀረ ሰላም ቡድኖችን ተከታትሎ የማጽዳቱ ግዳጅ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል። ዘገባው የመሀመድ አህመድ ነው

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official

Photos from Wollo Times's post 06/05/2026

ቻይና ለኢራን የኒውክሌር ኃይልን ድጋፏን አስታወቀች‼️

የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት እንደዘገበው፤ ቻይና የኢራን መንግሥት የኒውክሌር ቴክኖሎጂን ለሰላማዊ ዓላማዎች የመጠቀም "ሕጋዊ መብት" እንዳለው በመግለጽ በይፋ ድጋፏን ገልጻለች።

ቤጂንግ የኢራንን የኒውክሌር መርሃ ግብር በተመለከተ ያላትን የቆየ አቋም በድጋሚ ያረጋገጠች ሲሆን፣ ይህም በዓለም አቀፍ ደረጃ በትኩረት እየተጠበቀ ነው።

ይህ የቻይና ድጋፍ በኢራን እና በምዕራባውያን ኃይሎች መካከል ያለውን ውጥረት ሊያባብሰው እንደሚችል ተገምቷል።

Wollo Times

https://www.facebook.com/wollotimes12

Photos from Wollo Times's post 06/05/2026

የእስራኤል የሚዲያ ተቋም "ቻናል 12" እና "i24" እንዲህ የሚል ዘገባ አውጥተዋል ፡-

"በጦር መሰሪያ ምርት ፍጥነት ከቱርክ ጋር መወዳደር አንችልም።

ቱርክ በዓለም አቀፍ ደረጀ ከፍ ብለ ማንም የማያውቀውን ምስጥራዊ ስትራቴጂካዊ የጦር መሳሪያዎችን እና የጦርነት ሰረአት ቴክኖሎጂዎችን እየሰራች ትገኛለች፣ ቱርክ የጦር መሳሪያ ውድድሩን ስታሸንፍ ታፈራግጠናለች"።

በነገራችን ላይ በአንድ ወቅት ፕሬዝዳንት ረጀብ ጠይብ ኤርዶጋን ለህዝባቸው እንዲህ ሲሉ ተናግረው ነበር:-''በአሁኑ ጊዜ በይፈ ከገለፀናቸው መሰሪያዎች ቢያንስ በአስር እጥፍ የሚበልጡ የጦር መሳሪያ ቴክኖሎጂዎች አሉን፣ እና እስካሁን ያልገለጽናቸው መሳሪያዎችን በሂደት ሲናሰያቸው ሁሉንም ያደንቀሉ።

ጊዜው ሲደርስ ጠላት እነዚህን ሚስጥራዊ መሳሪያዎቻችንን ይጋፈጣል''፤ እኛ ከአላህ ቀጥሎ በራሳችን የጦር መሰሪያ አቅም እንታማመናለን እንጂ፣ በሌሎች ሀይል ላይ አንመካም"።

ቱርክ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ በዛሬው ቀን በታሪኳ "ICBM" አህጉር አቋረጭ ፈጣን ሚሳኤሏን በይፈ ስታሳይ ይህ በእስራኤል ከፍተኛ ስጋት እንደሚጥል ግልፅ ነው።

Wollo Times

https://www.facebook.com/wollotimes12

Photos from Wollo Times's post 04/05/2026

ሰበር መረጃ ኢራን ሁለት የአሜሪካ የጦር መርከቦችን
መምታቷን አስታወቀች ‼️

የኢራን አብነታዊ ዘብ IRGC የባህር ሀይል እንደተናገረው
የአሜሪካ ሁለት ግዙፍ የጦር መርከቦችን ሆርሙዝን ለማለፍ ሲሞክሩ በሁለት ሚሳኤል መምታቱን አስታወቀ ።

Wollo Times

Photos from Wollo Times's post 04/05/2026

ፓኪስታን በአሜሪካ ቁጥጥር ስር የነበሩ የኢራን መርከበኞችን ልታስረክብ ነው

ፓኪስታን በአሜሪካ ቁጥጥር ስር የነበሩ 22 የኢራን መርከበኞችን ለቴህራን ልታስረክብ ነው
ፓኪስታን በአሜሪካ ጦር ተይዘው የነበረ የአንድ የኢራን መርከብ 22 አባላትን ዛሬ ሰኞ ለቴህራን እንደምታስረክብ አረጋግጣለች።

የእስላማባድ ባለስልጣናት ይህንን ውሳኔ "የመተማመን መገንቢያ እርምጃ" ሲሉ የገለጹት ሲሆን፤ ይህም በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ አካባቢ ያለውን ከፍተኛ ውጥረት ለማርገብ ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

መርከበኞቹ በአሜሪካ የባህር ኃይል ቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ በፓኪስታን በኩል አልፈው ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ስምምነት ላይ ተደርሷል።

ይህ የፓኪስታን እርምጃ በቅርቡ በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ላይ በተፈጠረው ወታደራዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ፍጥጫ ሳቢያ በኢራን እና በምዕራባውያን ሀገራት መካከል የሻከረውን ግንኙነት ለማለስለስ የሚረዳ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ተደርጎ ተወስዷል።

ርክክቡ ዛሬ ሰኞ እለት እንደሚከናወን የሚጠበቅ ሲሆን፤ እስላማባድ በቀጣናው ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን ያላትን ፍላጎት የምታሳይበት እንደሆነም አስታውቃለች መባሉን የዘገበው አናዶሉ ነው።

Wollo Times

https://www.facebook.com/wollotimes12

02/05/2026

የሕውሓቱ ጀነራል የፌዴራል መንግስቱ ላይ ዛቱ፡፡

ብልጽግናን ለማስወገድ ተዘጋጅተናል ሲሉ በአደባባይ ወጥተው ተናግረዋል፡፡ የጀነራል ታደሰን እንቅስቃሴ እግር በእግር እንዲከታተሉ ትእዛዝ የተሰጣቸው እኚህ ጀነራል፤ ሁሉም ነገር አልቋል በቅርቡ ጠብቁን ብለዋል፡፡ ይህ የጀነራሉ ዛቻ የተሰማው ከአሜሪካ እስከ አውሮፓ ህብረት ጦርነት እንዳይፈነዳ እያስጠነቀቁ ባለበት ወቅት ነው፡፡
የሕውሓት ፖለቲካዊ አመራሮች እና ወታደራዊ አዛዦች 4ኪሎ ላይ የሚያሰሙትን ዛቻ ቀጥለውበታል፡፡

ከሰሞኑ የቡድኑ አመራር አዲስአለም ባሌማ ‹‹ለሁሉም ነገር ተዘጋጅተናል፤ ሎጀስቲክ አዘጋጅተናል፤ከፋኖም ከሻብያም ጋር ተጣምረናል›› ማለታቸው አይዘነጋም፡፡ ዛሬ ደግሞ ከሕውሓት ወታደራዊ አዛዦች መሀል አንዱ የሆኑት የአርሚ 60 አዛዥ ብርጋዴር ጀነራል ህንፃ ወልደጊዮርጊስ ብልጽግናን ለመጣል ተዘጋጅተናል የሚል ከፕሪቶሪያ ስምምነት ያፈነገጠ አስተያየት ሰጥተዋል፡፡

ጀነራሉ የህወሓት ልሳን ለሆነው ወይን ሚዲያ በወቅታዊ ጉዳይ በሰጡት ማብራሪያ፣ “ማንም መጠራጠር የሌለብት ሁሉም ነገር አልቋል” ሲሉ ፉከራ አሰምተዋል፡፡ ጀነራሉ ብዙዎች ተሰውተውለታል ያሉትን በተናጠል ክልላዊ ምርጫ የተመሰረተውን፣ የህወሓት መንግሥት መመለስ የህልውና ጉዳይ ነው ብለዋል፡፡

የሁለት ዓመቱን ደም አፋሳሽ ጦርነት መሬት ለማስመለስ ሳይሆን፣ 2.8 ሚሊዮን ህዝብ የመረጠጠውን መንግሥት ለማስመለስ ነው ያሉት ጀነራሉ፤ በጦርነቱ አንድ ሚሊዮን ገደማ ሰው ሞቷል የሚባለውን አስተባብለው፤ “አንድ ሚሊዮን ሰው ሞቷል የሚለውን ተውት፣ የተገደሉት በሺዎች የሚቆጠሩ ናቸው” ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

ጀነራሉ መስዋእት ከፍለንበታል ያሉትን ህወሓት መራሹን መንግሥት ለመመለስ ሙሉ ዝግጁ አለን ብለዋል፡፡ ዳግም ጦርነት ይቀሰቀሳል ተብሎ ከፍተኛ ስጋት ስለፈጠረው ውጥረት ማብራሪያ የሰጡት ጀነራሉ፣ “ድጋሜ ከተዋጋን የነብረውን መንግስት ለመመለስ ነው” ይላሉ፡፡

የፕሪቶሪያው ስምምነት ከዚህ በኋካ ዋጋ እንደሌለው የገለጹም ሲሆን፤ ከዚህ በኋላ ወደኋላ የሚመለስን ኃይል የለም ብለዋል፡፡ የፌደራል መንግሥት በስምምነት ሰበብ ትግራይ ከፋፍሏል በማለት የከሰሱ ሲሆን፣ እንደ ጌታቸው ረዳ ያሉ ግለሰቦችንም እንደ ጠላት እንታገላቸዋለን ብለዋል፡፡

ጀነራሉ ትግራይ ከድተዋል ያሏቸውን ኃይሎች ከፌደራል መንግሥት ጎን ተሰልፈው፣ የህወሓት አመራሮችን ለማጥቃት እየተዘጋጁ ነው በማለት ከሰዋል፡፡ በዚህም የህወሓት አመራሮች የጥቃት ኢላማ በመሆናቸው በነጻነት መንቀሳቀስ እንዳይችሉ መሆኑን የጠቆሙ ሲሆን፣ በእነ ደብረጽዮን በኩል ከወዲሁ ደብብቆሽ መጀመሩን ጠቁመዋል፡፡

ከባለፈው ጦርነት ተምረናል ያሉት ጀነራሉ፣ ዳግም ውጊያ ከተቀሰቀሰ እንደበፊቱ በቀላሉ እጅ አንስጥም ብለዋል፡፡ የህወሓትን መንግሥት በመመለስ የቤት ሥራችንን ጨርሰናል ያሉት እኚሁ ወታደራዊ አዛዥ፣ ቀጣዩ ጉዞ የትግራይን ብሔራዊ ጥቅም ማስከበር ነው ብለዋል፡፡

Wollo Times

https://www.facebook.com/wollotimes12

30/04/2026

ሰበር ኢራን የአሜሪካን እገዳ በወታደራዊ ኃይል ታነሳለች።

የቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር #ሞታኪ “የባህር ኃይል እገዳ ማለት የጦርነት አዋጅ ማለት ነው” ብለዋል።

የቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚኒስት ሞታኪ“ #ተዋጊዎቻችን ነገ ወይም በሚቀጥለው ሳምንት እርምጃ ሊወስዱ ይችላሉ።” ብለዋል ።

Wollo Times




https://www.facebook.com/wollotimes12

30/04/2026

"እኛ አፋሮች ከአክሱም ሙስሊሞች ጎን ነን! "
ፍትህ ለአክሱም ሙስሊሞች!!!. ✊

"ወንድምህን ስትወደው ለአላህ ብለህ ውደደው" 💝

"ረሱል ﷺ🤍❤️‍🩹🫶💝

#ፍትህለአክሱምሙስሊሞች‼️✊
#ፍትህለአክሱምሙስሊሞች‼️✊

#ፍትህለአክሱምሙስሊሞች!

Wollo Times
https://www.facebook.com/share/1DmcLXERwH/

29/04/2026

ሰበር ሰበር 52 የኢራን መርከቦች እገዳውን ጥሰው አለፉ‼️

የትራምፕ እገዳ የት ነው ?
ባለፉት 72 ሰዓታት ውስጥ ብቻ 52 የኢራን መርከቦች ዩናይትድ ስቴትስ በኢራን የውሃ ክልል ላይ የጣለችውን እገዳ ጥሰው ማለፋቸውን የኢራን ፋርስ የዜና ወኪል ዘግቧል።

​እስከ ሰኞ ምሽት 4፡00 ሰዓት በአካባቢው አቆጣጠር ያለውን የሳተላይት መከታተያ መረጃ ጠቅሶ የወጣው ዘገባ እንደሚያመለክተው መስመሩን ካለፉት መርከቦች መካከል 31ዱ የነዳጅ ጫኝ መርከቦች ሲሆኑ 21ዱ ደግሞ የጭነት መርከቦች ናቸው።

Wollo Times

https://www.facebook.com/wollotimes12

Photos from Wollo Times's post 29/04/2026

ገንዘብ ካለ. . በሆርሙዝ መንገድ አለ ።
ይህችን የቅንጦት መርከብ ፡ መርከብ ወይም ጀልባ ብቻ. ብሎ መጥራት ትንሽ ይከብዳል ።
ምክንያቱም አጠቃላይ አሰራሯ ከመርከብም ሆነ ከጀልባ በላይ ነው ።
ኖርድ በሚል ስያሜ የምትታወቀውና ፡ ንብረትነቷ የሩሲያዊው ቢሊየነር አሌክሲ ሞርዳሾቭ የሆነችው ይህች የቅንጦት ጀልባ አንድ ጊዜ ነዳጅ ከሞላች ፡ የአለምን ግማሽ መዞር የምትችል ሲሆን በላይዋ ሁለት ሄሊኮፕተር ማሳረፍ የሚችል ሄሊፓድ ተሰርቶላታል ።...
ብዙ የቅንጦት ጀልባዎች ሄሊፓድ ስላላቸው ይህ አይገርም ይሆናል ። የዚች ጀልባ የሚለየው ሄሊኮፕተሮቹ ከጀልባዋ አናት ላይ ካረፉ በኋላ በሊፍት መሰል ነገር ወደታች ይወሰዱና ፡ በጀልባዋ የታችኛው ክፍል በተዘጋጀላቸው ቤት ( ሀንጋር ) ውስጥ እንዲቆሙ ይደረጋል ።....
ለአጠቃላይ ግንባታዋ አምስት መቶ ሚሊየን ዶላር የወጣባትና ፡ የቅንጦት ጀልባዎችን በጥራት በመስራት በሚታወቀው የጀርመኑ ላርሰን ኩባንያ የተገነባችው .. ይህች ውድ ጀልባ ፡ እስከ 36 እንግዶችን ማስተናገድ የሚችሉ ፡ ከእምነበረድ የተሰራ መታጠቢያ ቤት ያላቸው 20 እጅግ ዘመናዊ ማረፊያ ክፍሎች አሏት ።.....
142 ሜትር በምትረዝመውና በ ባለ ስድስት ፎቋ ፡ ኖርድ የቅንጦት ጀልባ ውስጥ ያለው ይህ ብቻ አይደለም ፡ ትልቅ የመዋኛ ገንዳ . .. ዘመናዊ የድምፅ እና የምስል መሳሪያዎች የተሟሉለት ሲኒማ ቤት ፡ ጂም. . ሳውና እና ስፓ በውስጧ ይዛለች ።
እና ከአንዱ ፎቅ ወደሌላኛው ለመሄድ የሚያገለግሉ ዘመናዊ የመስታወት ሊፍቶችም ተገጥመውላታል ።
እንዲሁም በውስጧ አነስተኛ ሰርጓጅ መርከብ እንዲኖራት ተደርጋ የተሰራች ናት ......
ይህች ተንቀሳቃሽ ቤተመንግስት ሰሞኑን ዱባይ ቆይታ ነበር ፡ እና ከትናንት ወዲያ ወደ ኦማን ለመጓዝ ፈልጋ ጉዞ ጀመረች ።....
ኖርድ ከዱባይ በኦማን በኩል ወደ ሲሸልስ ልታደርግ ባሰበችው በዚህ ጉዞ ፡ ሆርሙዝን ማቋረጥ ግድ ነው ። እና ጉዞዋን ወደ ሆርሙዝ አድርጋ መንገድ ጀመረች ።.....
በሺህ የሚቆጠሩ ምስኪን መርከቦች መንገድ ተዘግቶባቸው ቆመዋል ። የቅንጦት ጀልባዋ ኖርድ በየቦታው የቆሙትን መርከቦች ሰላም እያለች በልበሙሉነት እየተጓዘች ወደተዘጋው ሆርሙዝ ደረሰች ።......
የኢራን የባህር ሀይል አባላት ኖርድ ማን እንደሆነችና ወዴት እንደምትሄድ ሁሉንም ያውቃሉ ።
እና ይህችን የወዳጅ ሀገር ሰው የሆነውን የሩሲያዊው ቢሊየነር ግዙፍ ጀልባ ፡ በሆርሙዝ ልታልፍ ስትመጣ አንዳች ችግር እንዳያጋጥማት አድርገው አሳልፈዋታል ።..
በአካባቢው ችግር ከተፈጠረ ከባለፉት ሁለት ወራት ጀምሮ ብዙ መርከቦች ወደዚህ ስፍራ መምጣት በማይደፍሩበት ወቅት ፡ 500 ሚሊየን ( ግማሽ ቢሊየን ዶላር ) ዋጋ ያላት የኖርድ በልበ ሙሉነት ሆርሙዝን ለማቋረጥ መድፈር ፡ ብዙዎችን ያስገረመ ጉዳይ ሆኗል

Wollo Times

https://www.facebook.com/wollotimes12

27/04/2026

አባት ሁለት ሴት ልጆቹን አንዷን ለገበሬ አንዷን ደሞ ለሸክላ ሰሪ ነበር የዳረው ፤ ከአመት በኋላ ሊጠይቃቸው ብሎ ከአገር ወጣ ።

ጥየቃውን የቤቱ ታላቅ ከሆነችው ለገበሬው ከዳራት ልጁ ጀመረ ፤ እሷም እጅግ በደስታ ተቀበለችው ።

አባት ልጁን ፦ "እንዴት ነሽ ኑሮ እንዴት ይዞሻል በምንስ እየኖርሽ ነው" ብሎ ጠየቃት

ልጅ ፦ "ባለቤቴ መሬት ተከራይቶ ነው ያረሰው ፣ እህሉን ደግሞ በብድር ነው የወሰደው አሁን ዘርቶታል ። ዝናብ እየጠበቅን ነው፤ ከዘነበ ምርቱ ጥሩ ይሆናል ኑሯችንም ይሻሻላል ፤ ካልዘነበ ግን አደጋ ውስጥ ነን" አለችው ።

ከዚያ ይህ አባት ወደ ሁለተኛ ልጁ አመራ እሷም በደስታ ተቀበለችው።
አባት ፦ "ኑሮ እንዴት ነው በምንስ ነው የምትኖሩት"አላት ።
ልጅ ፦ "ባለቤቴ በብድር ነው የሸክላ አፈር የገዛው ፤ አሁን ብዙ የሸክላ ምርት አዘጋጅቶ መድረቁን እየተጠባበቀ ነው ። በየቀኑ ፀሀይ የሚወጣ ከሆነ ምርቱ ይሄድለታል ፤ በኑሯችን ላይም ለውጥ ይኖራል። የሚዘንብ ከሆነ ግን ሸክላው ይበላሻል " አለችው ።

አባት ልጆቹን ከጎበኘ በኋላ ወደ አገሩ ተመለሰ ፤ ቤቱ ሲደርስ የልጆቹ እናት ስለ ልጆቹ ሁኔታ ጠየቀችው ። እሱም እንዲህ አላት ፦ ከዘነበም አልሀምዱሊላህ በይ_ካልዘነበም_ አልሀምዱሊላህ _በይ።" አላት

እንግዲህ የህይወት ነገር እንዲህ ነው ፤ አንዱ የሚፈልገውን ሌላው አይፈልገውም ፤ ላንዱ የሚስማማው ለሌላው አይስማማውም፤ ለአንዱ መሰናክሉ ለሌላው የስኬት መንገዱ ነው ። ብናዝንም ብንደሰትም ብናጣም ብናገኝም አልሀምዱሊላህ ☝️

Wollo Times

https://www.facebook.com/wollotimes12

Want your business to be the top-listed Media Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Telephone

Website

Address


America
Addis Ababa