I Hope
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from I Hope, News & Media Website, ethiopia, Addis Ababa.
10/02/2026
ኢትዮጵያ ዝግጅቷን ጨርሳ እንግዶቿን በጉጉት እየጠበቀች ነው!
10/02/2026
የሻዕቢያ ምላሽ ለኤርትራ ህዝብ ቅንጣት ታክል ርህራሄ እንደሌለው ማሳያ ነው!
ለምስራቅ አፍሪካ የሰላም ተምሳሌት የሆነችው ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋር ሰላምን ለማጽናት የሄደችበት እልህ አስጨራሽ ጉዞ በአለም ሃገራት አስመስግኗታል።
የኢትዮጵያ መንግስት ለህዝቡ ያለውን አክብሮት እና ፍቅር በያንዳንዱ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በግልጽ እያሳየ ይገኛል።
በተቃራኒው ደግሞ የሻዕቢያ መንግስት ህዝቡን ጨቁኖ በመግዛት ለሃገሩ ብሎም ለኤርትራ ህዝብ ያለውን ጥላቻ እና ንቀት በግልጽ አሳይቷል።የኢትዮጵያ መንግስት በተደጋጋሚ የሰላም ድርድር ለማድረግ የሻዕቢያን መንግስት ደጅ የጠናች ሲሆን ያደግሞ ለኤርትራ እና ለህዝቦቿ ያላትን ትልቅ ክብር ያሳያል።
ሆኖም በቅርቡ የኤርትራ መንግስት በኢትዮጵያ ድንበር ዘልቆ በመግባት ጦሩን ማሰለፉን ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግስት የህዝቤን ህልውና አደጋ ላይ ይጥላል ስትል የኤርትራን መንግስት ከድንበሬ ጦርህን አውጣ በማለት አስጠንቅቃለጭ
ነገር ግን ለኤርትራ ህዝብ ቅንጣት ያክል እርህራሄ የሌለው የሻዕቢያ መንግስት የቶር ነጋሪቱን ለመደቆስ ያለመ ምላሽ ሰጥቷል።የኢትዮጵያ መንግስት ለህዝቡ ሲል ብዙ ነገር እይታገሰ ቢሆንም ኢሳያስ ደግሞ በተቃራኒው ደ*ም የጠማው ይመስላል።
10/02/2026
"የኢትዮጵያን የባህር በር የማግኘት ጥረት እደግፋለሁ" ፈረንሳይ
የፈረንሳይ መንግስት ኢትዮጵያ በሰላማዊ መንገድ የባህር በር ለማግኘት የምታደርገውን ጥረት እና የምታቀርበውን ጥያቄ እንደምትደግፍ በይፋ አስታውቋል።
የኢትዮጵያን የባህር በር ይገባኛል ጥያቄ ታሪካዊም ህጋዊም መብት እንዳላት አለም ሃገራት የተረዱ ሲሆን በሰላማዊ መንገድ የምታደርገውን ጥረት ደግሞ እጅግ የሚደነቅ ተብሎላታል።
10/02/2026
አንቶኒዮ ጉተሬዝ በአፍሪካ ህብረት ላይ በመገኘት በአሰብ ጉዳይ ላይ ሊመክሩ ነው!
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ከፊታችን በሚካሄደው የአፍሪካ ህብረት ላይ በመገኘት በኢትዮ ኤርትራ ውጥረት ላይ እንደሚመክሩ ተገለጸ።
በዚህም በአዲስ አበባ ጉብኝት የሚያደርጉት አንቶኒዮ ጉተሬዝ የሻዕቢያ መንግስት ኢትዮጵያላይ እያደረገ ያለውን ህገ ወጥ ድርጊት ላይ እንደሚወያዩም ይጠበቃል።
ጉተሬዝ በጉብኝታቸው በአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ላይ እንደሚሳተፉ የተነገረ ሲሆን፤ ጎን ለጎንም ከተለያዩ የአፍሪካ አገራት መሪዎች ጋር ይወያያሉ።
09/02/2026
ኢትዮጵያን ወግቶ አሸናፊ መሆን አይቻልም"
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
09/02/2026
ኢትዮጵያ ለሰላም ያላትን ቁርጠኝነት ስታሳይ ፣ ኤርትራ ግን ቀጠናውን የማተራመስ ፍላጎቷን በግልጽ አሳይታለች !!
ገንቢ የሆነ የዲፕሎማሲ ግንኙነት በጥርጣሬና የተሸሸጉ ፍላጎቶችን በመፈለግ ላይ ሳይሆን ፣ ትኩረትን ዋና ዋና የቀጠናው ጉዳዮች ላይ በማድረግ ችግሮችን መፍታትን ይጠይቃል።
ኢትዮጵያ ይህንን መርህ መሠረት በማድረግና ለቀጠናው ሰላም ቅድሚያ በመስጠት ፣ ልዩነቶችን በጠረጴዛ ዙሪያ ለመጨረስ ያላትን ቁርጠኝነት በግልጽ ደብዳቤ ብታሳውቅም ፣ በኤርትራ በኩል ግን ለቀረበው የሰላምና የውይይት ጥሪ ተገቢውን ምላሽ ከመስጠት ይልቅ ጉዳዩን ወደ ጎን በመተው ለውይይት ዝግጁ አለመሆኗን በግልጽ አሳይታለች።
ኢትዮጵያ አሁንም ቢሆን በሰላማዊ መንገድ ለመሳተፍ ያላትን ዝግጁነት እየገለጸች ባለችበት በዚህ ወቅት ፣ የኤርትራ እምቢተኝነት በቀጠናው የተረጋጋ ግንኙነት ለመፍጠር የሚደረገውን ጥረት የሚያደናቅፍና ሃገሪቱ ለሰላማዊ አማራጮች ያላትን ዝቅተኛ ፍላጎት የሚያንጸባርቅ ከመሆኑም በላይ የሻዕቢያ መንግስት ለቀጠናው አለመረጋጋት ዋና ተጠያቂ የሚያደርግ ነው።
09/02/2026
የኢትዮጵያ ሰላም መሆን ለቀጠናዉ መረጋጋት ትልቅ ዋስትና ነዉ !!
ኢትዮጵያ ለዘመናት የአብሮነት የልማት እና የሰላም ተምሳሌት ሆና ብትቆይም በኤርትራው አምባገነን መሪ ኢሳያስ አፈወርቂ የሚመራው ቡድን ግን አሁንም ካረጀው የጥላቻ እና የትንኮሳ ፖለቲካ ሊወጣ አልቻለም። የኢትዮጵያ መንግስት በጋራ እንልማ በጋራ እንበልፅግ የሚል የሰላም እጁን ቢዘረጋም አስመራ የሚገኘው ይኸው ኃይል ግን የኢትዮጵያን ሰላም ለማደፍረስ ጸረ-ሰላም ኃይሎችን በማሰልጠን እና በማስታጠቅ ክፉ ሴራውን ቀጥሏል። ይህ ዓይነቱ አፍራሽ ተግባር የቀጠናውን መረጋጋት የሚፈታተን ከመሆኑም በላይ የኤርትራ ህዝብ ከጎረቤቶቹ ጋር ተስማምቶ የመኖር መብቱን የሚነጥቅ የታሪክ ጠባሳ ነው።
ኢትዮጵያ ለማንኛውም ሰላማዊ ድርድር እና ዲፕሎማሲያዊ ንግግር በሯ ሁልጊዜም ክፍት ነው። ለጎረቤት ሀገራት ክብር እና ለቀጠናው ዕድገት ቅድሚያ የምትሰጠው ሀገራችን ኢትዮጵያ የሰላም አማራጭን የምትመርጠው ከፍርሃት ሳይሆን ለሰው ልጅ ህይወት እና ለልማት ካላት ጥልቅ ቁርጠኝነት የተነሳ ነው። ነገር ግን ይህ የትዕግስት እና የሰላም መንገድ እንደ ድክመት ተቆጥሮ የሀገርን ህልውና እና የህዝብን ደህንነት የሚፈታተን ትንኮሳ የሚቀጥል ከሆነ ኢትዮጵያ ራሷን የመከላከል የተፈጥሮ መብቷን ተጠቅማ አስፈላጊውን እርምጃ ለመውሰድ ወደኋላ አትልም።
በመሆኑም የኤርትራ መንግስት ከዚህ አደገኛ ጠብ አጫሪነት ተቆጥቦ ወደ ሰላማዊው ጠረጴዛ መምጣት ይኖርበታል። ነገሮች ከመስመር ወጥተው ወደማይመለስ ጥፋት ከማምራታቸው በፊት አምባገነናዊ ግትርነትን ትቶ ለህዝቦች ሰላም ቅድሚያ መስጠት ብልህነት ነው። ኢትዮጵያ ክብሯን እና ሰላሟን ለማስጠበቅ ምንጊዜም ዝግጁ ናት። ምርጫው ግን በአስመራ እጅ ላይ ነው። ሰላም ለኢትዮጵያ! ሰላም ለአፍሪካ ቀንድ!
09/02/2026
ሻዕቢያ ለሰላም ጥሪዎች ጀርባውን የሚሰጥ የቀጠናው ስጋት ነው!!
የሻዕቢያ አምባገነናዊ ስብስብ በአፍሪካ ቀንድ ውስጥ የሰላምን ጭላንጭል ለማጥፋት የሚጥር፣ በጦርነትና በግርግር የሚኖር የቀጠናው ዋነኛ ስጋት ነው። ኢትዮጵያ ለሰላም የዘረጋችውን እጅ ባለመቀበል እና የዲፕሎማሲ ጥሪዎችን በዛቻና በትንኮሳ በመመለስ ቡድኑ ከጥፋት ፖለቲካ ውጭ መኖር የማይችል የጦርነት አፍቃሪ መሆኑን ዳግም አረጋግጧል። ይህ ኋላቀር ስብስብ የሰለጠነ ውይይትን እንደ ድክመት የሚቆጥር፣ በሰው ልጅ ስቃይና በንጹሃን ደም የሚነግድ እንዲሁም የጎረቤት ሀገራትን ሰላም በማናጋት የራሱን እድሜ ለማራዘም የሚጋደል የጥፋት ቡድን ነው።
09/02/2026
ኢሳያስ የሰላም ፀር የሆነው ሰላም ካለ ህልውናው አደጋ ላይ ስለሚወድቅ ነው!!
የኢሳያስ አፈወርቂ አምባገነናዊ አገዛዝ ለሰላም ጥሪዎች ጀርባውን የሚሰጠው ሰላም በሰፈነበት ሁኔታ ውስጥ የጥፋት አጀንዳው ስለማይሰራና ህልውናው አደጋ ላይ ስለሚወድቅ ነው።
ኢሳያስ ስልጣኑን ለማራዘም የሚጠቀመው ብቸኛው ስልት ህዝብን በጦርነት ስጋት ውስጥ መቆለፍና ጎረቤት ሀገራትን ማተራመስ በመሆኑ ሰላም ለእሱ የህልውና ጠንቅ እንጂ ምርጫው አይደለም። ይህ የሰላም ፀር የሆነ ሰው በኢትዮጵያና በቀጠናው የሚታዩትን የዲፕሎማሲ ጭላንጭሎች ለማጨለም የሚጥር፣በሰለጠነ ውይይት ውስጥ መቆም የማይችል ኋላቀር አስተሳሰብ የተጠናወተው በመሆኑ ነው።
በአጭሩ የኢሳያስ ህልውና የተመሰረተው በንጹሃን ደም፣ በጦርነት ነጋሪት እና በቀጠናው አለመረጋጋት ላይ ብቻ በመሆኑ ለሰላም ጀርባውን የሰጠው በዚህ ምክንያት ነው።
09/02/2026
ህወሓት ጭነቀት ውስጥ ገብቷል!
ህወሓት ከሰሞኑ ብቻ ከባድ ኪሳራ አተናግዷል። በርካታ ታጣቂዎቹ እየከዱት ይገኛሉ። ከህዝብ የሚደርስበት ከፍተኛ ተቃውሞ እንዳለ ሆኖ በለኮሰው ጦርነት በቀድሞ አባላቶቹ ጭምር እየተጠቃ ይገኛል። ተኩስ ወዴት እንደሚተኩስ እንኳን ጠፍቶታል። የገዛ ታጣቂዎቹ እያፈነገጡ ከሃራ መሬት አባላት ጋር በመቀናጀት እያጠቁት ይገኛሉ። ከሰሞኑንም መቀመጫውን መቀሌ ያደረገው ህወሓት መቀሌን ለቅቆ ሽሬ ገብቷል። የመቀሌ ህዝብ ዝምታውን የሰበረ ይመስላል። ውስጥ ለውስጥ ህወሓትን የሚያወግዝ ሰልፍ ለማድረግ እንቅስቃሴ ጀምሯል። ለዚህም ይመስለናል ህወሓት ፈርቶ መቀሌን የለቀቀው። ህወሓት በሁሉም አቅጣጫ ከበባ ውስጥ ነው ያለው። ግራ ተጋብቷል። ከማን ጋር እንደሚዋጋ እራሱ አላወቀም። እራሱ በከፈተው ጦርነት እሳት ላይ ተጥዷል።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Culinary Team
Attire
Telephone
Website
Address
Addis Ababa