Wereda 13 Communication

Wereda 13 Communication

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Wereda 13 Communication, News & Media Website, winget, Addis Ababa.

Photos from Addis ketema Wereda 13 Communication's post 25/02/2026
07/02/2024

በአዲስ ከተማ ወረዳ 13 አስተዳደር የኑሮ ውድነትና ገበያ ማረጋጋት ግብረሃይል ተቋቋሙ ወደ ስራ መግባቱ ተገለጸ፡፡ **************

በአዲስ ከተማ ወረዳ 13 አስተዳደር በቀጣይ ሶስት ወራት የሚታየውን የኑሮ ውድ ነት ለማሻሻል እና ገበያውን ለማረጋጋት አላማው ያደረገ ግብርሀይል በዛሬው እለት ተቋቁሞ ወደ ስራ መግባቱን የአዲስ ከተማ ወረዳ 13 ንግድ ጽ/ቤት ሀላፊ የሆኑት አቶ ጌታቸው ተሰማ አስታውቀው ግብረ ሀይሉ በሸማች ሱቆች ላይ የምርት እጥረት እንዳይከሰት አቅርቦት እንዲጨምር ማድረግ፣ ምርቶቹ ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ለሸማቹ ህብረተሰብ እንዲከፋፈል መከተታተልና መቆጣጠር እንዲሁም የፍጆታ ዕቃዎች የዋጋ ንረትን መፈተሽ ዋና ተግባሩ አድርጎ እንደሚንቀሳቀስ ተናግረዋል፡፡

አቶ ጌታቸው ጨምረው እንደገለጹት የኑሮ ውድነቱ በህብረተሰቡ ላይ እየፈጠረ የሚገኘውን ጫና በመገንዘብ ጉዳዩ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶት ግብርሀይሉ በአዲስ ከተማ ወረዳ 13 ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሃላፊ በአቶ ባጫ ፈረጃ ሰብሳቢነት እንዲመራ መደረጉን ገልጸው ንግድ ጽ/ቤት፣ ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት፣ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላትን በማካተት የኑሮ ውድነትን መከላከል ፣ገበያን ማረጋጋት፣ ገቢ መሰብሰብን እንዲሁም በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አቅርቦትን መጨመር የሚሉ ዋና ዋና ግቦች ዓላማ አድርጎ ወደ ስራ መግባቱን አስታውቀዋል፡፡

በስተመጨረሻም ሀላፊው ሕብረተሰቡ በሚፈልጋቸው ሸቀጦች ላይ ከፍተኛ የዋጋ ውድነት በመጨመር የማስመረር ተግባር በስፋት እንደሚስተዋል ገልጸው በእዚህም ሕገወጦች ተጠቃሚ ሲሆኑ ሕብረተሰቡ ደግሞ ከፍተኛ ተጎጂ እየሆነ መሆኑን በአግባቡ በመረዳት ግብርሀይሉ የተጣለበትን ከፍተኛ ሃላፊነት በመገንዘብ ህዝባችንን ለምሬት እየዳረገ ያለውን የኑሮ ውድነትና የገበያ አሻጥር በመቀልበስ የተረጋጋና ፍትሃዊ የገበያ ሁኔታ እንዲፈጠር እንዲረባረብ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡

Want your business to be the top-listed Media Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Website

Address

Winget
Addis Ababa