Bruk tech

Bruk tech

Share

የተለያዩ ነገሮችን በዚህ ቻናል ያገኛሉ @@@@🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰

27/03/2024

 የሳይበር ምህዳር ምንድነው
ሳይበር:- የሰው ልጅ የእርስ በርስ ግንኙነቱ ማደግ የፈጠረው ረቂቅ የቴክኖሎጂ ውጤት እና መሰረተ-ልማት፣ የመረጃ እንዲሁም የሰዎች መስተጋበር የሚገለጽበት ፈጠራ ነው፡፡
የሳይበር ምህዳር የምንለው የተለያዩ የኢንፎርሜሽን መሰረተ-ልማቶች ማለትም ኮምፒውተሮች ፣ራውተሮች፣የኮምፒውተር ኔትዎርኮች፣ወ.ዘ.ተ. ተሳስረው የፈጠሩት ምናባዊ ዓለም ሲሆን በዚህ ምህዳር ውስጥ ኢንፎርሜሽን ይቀመጣል፣ይሰራጫል፣እንዲሁም ይተነተናል፡፡
የሳይበር ምህዳሩን አንዳንዶች በቴክኖሎጂ አማካኝነት የሰው ልጅ የተቆጣጠረው አምስተኛው ግዛት በማለት ይጠሩታል፡፡ ይህም ከየብስ ፣ ውሃ ፣ የአየር እንዲሁም የውጫዊው የህዋ ግዛት መካከከል በመመደብ፡፡
የሳይበር ምህዳር፡ የብዙዎቻችን የእለት ተእለት እንቅስቃሴ አካል ከሆነም ውሎ አድሯል፡፡ ይህ ሲባል ለስራ ፣ለትምህርት ፣ ለመዝናኛ ከመጥቀምም አልፎ ለተለያዩ የእርስ በርስ ግንኙነቶች ማሳለጫ አድርገን የምንጠቀምበት ዋነኛ መሳሪያ በመሆን ላይ ይገኛል፡፡ ከዚህ አልፎ የምህዳሩ እውን መሆን የኢንፎርሜሽን ዋጋ ከምንጊዜውም በላይ እንዲጨምር ምክንያት እየሆነ ይገኛል፡፡
የሳይበር ምህዳር አካላት
የሳይበር ምህዳር የምንለው ኮምፒውተሮች ብቻ የሚፈጥሩት ሳይሆን የተለያዩ አካላት ተሳስረው እውን ያደረጉት ምህዳር ነው፡፡ እነዚህ የሳይበር ምህዳር አካላት ከላይኛው የምህዳሩ ክፍል እስከ ታችኛው ድረስ በ4 ዋና ዋና ክፍለች ከፋፍሎ ማየት ይቻላል፡፡
የውስጠኛው የምህዳሩ ክፍል፡ የሳይበር ምህዳር እውን እንዲሆን መሰረት የጣለው አካላዊ ወይም ፊዚካል ደረጃ የምንለው ነው፡፡ ይህም የተለያዩ ማሽኖች፣ኮምፒውተሮች፣ኬብሎችና የመሳሰሉ አካላት ጥምረት ነው፡፡
ሁለተኛው የሳይበር ምህዳር ውስጥ የሚቀመጠው፣ የሚተነተነው እና የሚሰራጨው ኢንፎርሜሽን ነው፡፡
ሶስተኛው የሳይበር ምህዳር ክፍል ለኢንፎርሜሽን መፈጠር፣ መተንተንና መሰራጨት መሰረት የሆኑ የተለያዩ አገልግሎቶች ናቸው፡፡ ለዚህ ጥሩ ምሳሌ የሚሆነው የኢንተርኔት አገልግሎት ፕላትፎርሞች ናቸው፡፡
እንዲሁም የመጨረሻው እና ውጫዊ ክፍሉ፡ የሳይበር ምህዳሩን የሚጠቀመው፣ ኢንፎርሜሽን እና ቴክኖሎጂውን የሚያንቀሳቅሰው የሰው ልጅ የሳይበር ምህዳር ውጨኛው ክፍል ነው፡፡
የሳይበር ምህዳሩ ልዩ ባህሪያት
ያልተማከለ ወይም ልዩ የተማከለ አስተዳደር የሌለው ሲሆን ይህም ለቁጥጥር አዳጋች እንዲሆን ያደርገዋል፡፡
ለግለሰቦች እና ለቡድኖች ከፍተኛ ሃይል የሚሰጥ ሲሆን የግለሰቦች እና ቡድኖች አስተሳሰብ፣እምነት እና እሴቶችን ማንጸባረቅ የሚያስችላቸው ነው፡፡
የጎንዮሽ እና ትስስራዊ ሃይል የሚያበረታታ ነው፡፡
ዓለም አቀፋዊ እና ድንበር የለሽ ነው፡፡
እውቀት መረጃና ምናባዊነት ላይ ያተኩራል
ለደካሞች ልዩ ተጠቃሚነትን የሚሰጥ ነው
ሁሉም ጋር የደራሽነት አቅም ያለው፡፡
በከፍተኛ ሁኔታ ተለዋዋጭ የሆነ ፍልስፍናዊ ባህሪ ያለው ነው፡፡
በእነዚህ ልዩ ባህሪያት ምክንያት ምህዳሩ ለተጠቃሚዎች መልካም እድሎችን ይዞ መጥቷል፡፡ በዚህም ምክንያት ዓለማችን ከጊዜ ወደ ጊዜ የተለየ መልክ እየያዘች ከመምጣቷ ባሻገር የእውቀት እና የኢንፎርሜሽን ማህበረሰብ እየተፈጠረ ይገኛል፡፡ ሆኖም ግን እነዚህ መልካም እድሎች ካመጧቸው ቱሩፋቶች ጎን ለጎን ምህዳሩ የተለያዩ የደህንነት ስጋቶችን ይዞ መጥቷል፡፡ እነዚህን ስጋቶች ለመቋቋምና ምህዳሩ ያለውን መልካም ጎኖች አሟጦ ለመጠቀም ሃገራት የደህንነት ስትራቴጂዎች ከቴክኖሎጂ፣ ከሰው ልጆች እንዲሁም ከኢንፈርሜሽን ደህንነት አስተዳደር እና አሰራር ስርዓቶች አንጻር ቀርጸው በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛሉ፡፡ ከስትራቴጂዎች መካከልም የኢንፎርሜሽን ደህንነት ገዥ ሰነዶች በዋናነት

08/05/2022

Cloud Storage ምንድን ነው?

▫️ ክላውድ ስቶሬጅ የምንለው በኮምፒውተር ወይም በሞባይል ስልክዎት የትኛውም ክፍል ላይ የተቀመጠ ፋይልና ዳታ በሌላ ድርጅት በተዘጋጀ የዳታ ማስቀመጫ ላይ የኢንተርኔት ግንኙነትን በመጠቀም የምናስቀምጥበት ነው፡፡

▫️ በአሁን ሰዓት ይሄን አገልግሎት የተለያዮ ድርጅቶች እየሰጡ ሲሆን በዋናነት Microsoft, Google, and Amazon ትልቁን ቦታ በመያዝ የሚጠቀሱ ሲሆኑ ፋይሎችን እና ዶክመንቶችን ለማስቀመጫ ድርጅቶቹ ለመጠቀሚያ የሚያስፈልግ ስም እና የይለፍ ቃል በማዘጋጀት የተወሰኑ ፋይሎችን በነፃ እንዲሁም በክፍያ እንድናስቀምጥ ያደርጋል፡፡

▫️ መጠባበቂያ ፋይሎችን እና ዶክመንቶችን ክላውድ ስቶሬጂ አገልግሎትን መጠቀም ፍላጎት እየጨመረ የመጣ እና የተለያዮ ጥቅሞች ሲኖሩት ከነዚህም ውስጥ ፋይሎች ጥብቅ በሆነ ቦታ መቀመጣቸው፣ የምናስቀምጠውን ፋይል ከየትኛውም ቦታና በማንኛውም ኮምፒውተር ላይ ሆነን መጠቀም እንችላለን እንዲሁም የግል ፋይሎቻችን የተቀመጠበት ኮምፒውተር ቢሰረቅ፣ ቢበላሽ ወይም በእሳት ቢቃጠል ካስቀመጥንበት ድርጂት ፋይሎቹን ካለምንም ችግር እናገኛለን፡፡

▫️ ባክአፕ ክላውድ በመጠቀም ፋይል እና ዳታ ስናስቀምጥ ኮምፒውተራችን የተገናኘበት የኢንተርኔት ግንኙነት ፍጥነት የሚወስነው ይሆናል ትልቅ መጠን ያላቸውን ፋይሎች ለማስቀመጥ ቀናትን ሊፈጅ የሚችል ሲሆን አገልግሎቱን ለመስጠት Amazon S3፣ Google Mozy እና Microsoft Sky Drive የሚሉ ሶፍትዌሮችን አዘጋጅተዋል፡፡

▫️ ማክሮሶፍት ድርጅት ላይ ለማስቀመጥ Sky Driveን በመጠቀም እስከ 25 GB በነፃ ማንኛውም ሰው ማስቀመጥ የሚችል ሲሆን ባጠቃላይ በነፃ ከሰጠን በላይ ለማስቀመጥ ክፍያ የሚያስፈልግ በመሆኑ ክፍያው የሚወሰነው እንደምናስቀምጠው ዳታ መጠን፣ አገልግሎቱን እንደተጠቀምነው ብዛት እንዲሁም የፋይሎቹ ቁጥር ነው፡፡

▫️ በተጨማሪም Google ድርጅት ላይ ለማስቀመጥ Google Driveን በመጠቀም እስከ 15 GB በነፃ ማንኛውም ሰው ከስልክዎ ላይ ያሉትን ፎቶና የመሳሰሉት መረጃዎች ማስቀመጥ የሚችል ሲሆን ባጠቃላይ በነፃ ከሰጠን ስቶሬጅ በላይ ለማስቀመጥ ክፍያ የሚያስፈልግ በመሆኑ ክፍያው የሚወሰነው እንደምናስቀምጠው ዳታ መጠን፣ አገልግሎቱን እንደተጠቀምነው ብዛት እንዲሁም የፋይሎቹ ቁጥር ነው፡፡
𝔟𝔯𝔲𝔨 𝔱𝔠𝔥

13/04/2022

Bruke tech beqerb qen ytebkugn
🎧🎤🎬🎨🎮📱💻📲🖥🖨🖱🗜💽💿🎞📞📺📻🎙📠🎚

26/09/2021
Want your public figure to be the top-listed Public Figure in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Website

Address

Addis Ababa