Al lukman

Al   lukman

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Al lukman, Halaba, Akaki Beseka.

12/10/2022

Halaba Media Network-ሀላባ ሚዲያ ኔትወርክ ሀላባ ሚዲያ ኔትወርክ የህዝብ ድምፅ፣የእርስዎ ደምጽ
ትክክለኛ መረጃን ለማህበረሰቡ በፍጥነት ማዳረስ እንዲሁም ለተጨቆኑ ድምጽ መሆን መለያችን ነው!! ሀላባ ሚዲያ ኔትወርክ የእርስዎ ተቀዳሚ ምርጫ።

12/10/2022

View your files - Files by Google Help On your Android device, open Files by Google . On the bottom, tap Browse

02/10/2022

የቁም ኑዛዜ ስጦታና ከውርስ መንቀል ያላቸው አንድነትና ልዩነት
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
👉የቁም ኑዛዜ ስጦታ ማለት ሟች ከሞተ በኋላ ተፈፃሚ የሚሆን ስጦታ ነው።
ሟች ከአንድ በላይ የሆኑ ልጆች ወይም ወራሾች ቢኖሩትና ከነዚያ መካከል ለአንደኛው የኑዛዜ ስጦታ ቢያደርግ የሌሎችን ወራሾች ከሟች ውርስ መነቀል አያስከትልም፡፡ ይህንንም የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 913 የኑዛዜው ቃል የተናዛዡን ተቃራኒ ሀሳብ የሚገልጽ ካልሆነ በቀር ከውርስ ሀብት አንድ ድርሻ ወይም አንድ ንብረት ሟቹ ለወራሾቹ መስጠቱ ተራ የሆነ የክፍያ ደንብ እንጂ እንደ ኑዛዜ ስጦታ ነው ተብሎ አይቆጠርም በማለት ይደነግጋል፡፡
ሰ/መ/ቁ 32337 ቅጽ 5፣ ፍ/ህ/ቁ. 882፣ 913፣ 2428፣ 2443
👉ከውርስ መንቀል
1 • ከውርስ መንቀል "Dishersion" የሚባለው ተናዛዡ የውርስ ህግ በሚደነግገው መሠረት ባደረገው ኑዛዜ ውስጥ ምክንያቱን በመግለጽ ወይም በዝምታ ከወራሾቹ አንዱን ወይም ከአንድ በላይ የሆኑት ወራሾቹ በውርሱ እንዳይካፈሉ ያደረገውን ኑዛዜ በውርስ ህግ ዕውቅናና ውጤት የሚሰጠው በሆነ ጊዜ ከውርሱ እንዳይሳተፉ የሚደረግበት ሥርዓት ነው፡፡
ተናዣዡ ከወራሾቹ አንደኛውን ከወራሽነት ለመንቀል የሚችል መሆኑ የፍትሐ ብሔር ህግ ቁጥር 937/1/ የሚደነግግ ሲሆነ ተናዣዡ ልጅን ወይም ወደታች የሚቆጠረውን በኑዛዜ ለመንቀል የደረሰበትን ምክንያት በኑዛዜው ውስጥ ካልገለፀ በቀር ልጅን ወይም ተወላጅን ለመንቀል ያደረገው ኑዛዜ እንደማይፀና በፍትሐ ብሔር ህግ ቁጥር 938/1/ ተደንግጓል፡፡
ሰ/መ/ቁ. 49713 ቅጽ 11፣ ፍ/ህ/ቁ. 937/1/፣ 938/1/
2 • ከውርስ መነቀል ማለት ከውርስ ሃብቱ ምንም አይነት ድርሻ አለማግኘት እንጂ አነስተኛ ድርሻ ማግኘት አይደለም፡፡
ሟች ባደረገው ኑዛዜ ወራሽ የሆነ ሰው በውርስ ሃብት ክፍፍል ድርሻው አንድ ተወላጅ ከሚደርሰው ከሩብ የበለጠ ጉዳት ቢደርስበት፤ ምንም እንኳን በህጉ አነጋገር ከውርሱ መነቀሉን ባያሳይም ክፍፍሉ እንዲቀር ጥያቄ ማቅረብ ይችላል፡፡
ሰ/መ/ቁ. 47622 ቅጽ 10፣ ፍ/ህ/ቁ. 1017፣ 1123(1)

02/10/2022

የካሣ አወሳሰን፣ ምትክ ቦታ አሰጣጥ እና መልሶ ማቋቋም በአዲሱ አዋጅ መሠረት
========================
ለሕዝብ ጥቅም መሬት ሲለቀቅ ለተነሺዎች ስለሚከፈል ካሣ
ለሕዝብ ጥቅም መሬት እንዲለቀቅ ሲደረግ ለተነሺው ባለው የንብረትና የይዞታ መብት መሠረት የንብረት እና የልማት ተነሽ ካሣ ይከፈላል፡፡
1. #የንብረት ካሣ
የመሬት ይዞታን እንዲለቅ የሚደረግ ባለይዞታ በመሬቱ ላይ ለሚገኘው ንብረት እንዲሁም በመሬቱ ላይ ሊደረገው ቋሚ ማሻሻያ ካሣ ይከፈለዋል፡፡
በሚለቀቀው የመሬት ይዞታ ላይ ለሰፈረው ንብረት የሚከፈል ካሣ ንብረቱን ለመተካት የሚያስችል ይሆናል፡፡
በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 2 የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ ለሚነሳው ቤት የሚከፈለው አነስተኛ የካሣ መጠን እንደየክልል፣ እንደ አዲስ አበባ እና ድሬደዋ ተጨባጭ ሁኔታ ወይም ክልል፣ አዲስ አበባ እና ድሬደዋ አስተዳደር በሚያወጣው ስታንዳርድ መሰረት ቢያንስ ዝቅተኛውን የቤት ደረጃ ሊያስገነባ የሚችል መሆን አለበት፡፡
በመሬት ይዞታው ላይ ለተደረገ ቋሚ ማሻሻል የሚከፈል ካሣ በመሬቱ ላይ የዋለውን ገንዘብና የጉልበት ዋጋ የሚተካ ክፍያ በአካባቢው ወቅታዊ ዋጋ ተሰልቶ ይሆናል፡፡
ንብረቱ ከሚገኝበት ስፍራ ወደ ሌላ አካባቢ ተዛውሮ እንደገና ሊተከልና አገልግልት ለመስጠት የሚችል ከሆነ የማንሻ፣ የማጓጓዣና መልሶ የመትከያ ወጪ የሚሸፍን ካሣ መከፈል አለበት፡፡ የተለያዩ ንብረቶች የሚሰለበት የካሣ ቀመር እና ዝርዝር አፈፃፀማቸው በደንብ ይወሰናል፡፡
2. #ስለ የልማት ተነሽ ካሳ እና ምትክ ቦታ
በቋሚነት ስለሚነሳ የገጠር መሬት ባለይዞታ የሚሰጥ ካሳ እና ምትክ ቦታ፦
የመሬት ይዞታውን በቋሚነት እንዲለቅ የሚደረግ የገጠር መሬት ባለይዞታ እንደአከባቢው ሁኔታ ከተወሰደበት መሬት ተመጣጣኝ ምርት የሚያስገኝ ምትክ መሬት የሚገኝ ሲሆን ምትክ መሬት ይሰጠዋል፡፡ ተመጣጣኝ ምትክ መሬት የሚሰጠው ከሆነ መሬቱን ከመልቀቁ በፊት በነበሩት ሶስት ዓመታት ውስጥ በየዓመቱ ከመሬቱ ሲያገኝ ከነበረው ከፍተኛውን የአንድ ዓመት ገቢ በወቅታዊ ዋጋ ተሰልቶ የልማት ተነሽ ካሳ ይከፈለዋል፤
ተመጣጣኝ ምትክ መሬት የማይሰጠው ከሆነ መሬቱን እንዲለቅ ከመደረጉ በፊት በነበሩት ሶስት ዓመታት ውስጥ ከመሬቱ ሲያገኝ የነበረውን ከፍተኛ ዓመታዊ ገቢ በአስራ አምስት ተባዝቶ የልማት ተነሽ ካሳ መከፈል አለበት፡፡
ከመኖሪያ ቦታው የሚነሳ ከሆነ ክልል፣ አዲስ አበባ ወይም ድሬደዋ ከተማ አሰተዳደሮች በሚያወጡት መመሪያ የሚወሰን ምትክ ቦታ እና የልማት ተነሽ ድጋፍ መከፈል አለበት፡፡
#በጊዜያዊነት ለሚለቀቅ መሬት የሚከፈል የልማት ተነሽ ካሣ በማንኛውም ሁኔታ በዘላቂነት ከሚከፈል የልማት ተነሽ ድጋፍ መብለጥ የለበትም፡፡
የዚህ ንዑስ አንቀፅ ዝርዝር አፈፃፀም ይህን አዋጅ ለማስፈጸም በሚወጣ ደንብ ይወሰናል፡፡
#በጊዜያዊነት ስለሚነሳ የገጠር መሬት ባለይዞታ የሚሰጥ የልማት ተነሽ ድጋፍ ካሳ፦
ይዞታውን ለተወሰነ ጊዜ እንዲለቅ ለሚደረግ የገጠር መሬት ባለይዞታ መሬቱ ከመለቀቁ በፊት በነበሩት ሶስት ዓመታት ውስጥ ያገኘው ከፍተኛ ዓመታዊ ገቢ መሬቱ እስከሚመለስ ድረስ ባለውጊ ዜ ታስቦ የልማት ተነሽ ድጋፍ ካሣ ይከፈለዋል፡፡
የሚከፈለው የልማት ተነሽ ካሣ መሬቱ የነበረውን ምርታማነት ለመመለስ የሚወስደውን በአካባቢ የግብርና ተቋም የሚወሰን ተጨማሪ ጊዜ ታሳቢ ማድረግ አለበት፡፡
መሬቱ ተመልሶ በፊት ይሰጥ የነበረውን አገልግልት መስጠት የማይችል ከሆነ በቋሚነት እንደለቀቀ ተቆጥሮ የልማት ተነሽ ካሳ ወይም ምትክ ቦታ ይሰጠዋል፤
መሬቱ በጊዜያዊነት በተለቀቀበት ጊዜ የተከፈለ የልማት ተነሽ ካሣ በቋሚነት እንደለቀቀ ተቆጥሮ ከሚከፈል ካሳ ተቀንሶ ለተነሺው ልዩነቱ ይሰጠዋል፡፡
በጊዜያዊነት ለሚለቀቅ መሬት የሚከፈል የልማት ተነሽ ካሣ በማንኛውም ሁኔታ በዘላቂነት ከሚከፈል የልማት ተነሽ ካሣ መብለጥ የለበትም፡፡

ስለወል ይዞታ የልማት ተነሺ ካሣ በቋሚነት ወይም በጊዜያዊነት ለሚለቀቅ የወል ይዞታ የልማት ተነሽ ካሣ ስሌት እና አከፋፈል ሁኔታ ክልል፣ አዲስ አበባ፣ ድሬደዋ በሚያወጣው መመሪያ የሚወሰን ሆኖ መመሪያው ሲወጣ፡-
ለተወሰደው የወል መሬት የልማት ተነሽ ካሣ ስሌት የወል መሬቱ ይሰጥ የነበረውን ጥቅም ወይም ጥቅሙ የቀረባቸውን የአኗኗር ዘይቤ ወይም መተዳደሪያ መሠረት ያደረገ ሊሆን ይገባል፡፡
#የወል መሬቱ ተጠቃሚዎች በግልጽ መለየት አለበት፡፡
በወል መሬቱ ላይ የሚገኙ የግልና የወል ንብረት መለየት አለበት፡፡
የወል መሬት በመወሰደ ምክንያት በካሣ የተገኘውን ገንዘብ ለማህበረሰቡ አባላት እኩል ሊከፈል ወይም በዓይነት ሊጠቀሙበት የሚችለበትን መንገድ መቅረጽ አለበት፡፡
በቋሚነት ስለሚነሳ የከተማ መሬት ባለይዞታ የሚሰጥ ልማት ተነሽ ካሳ እና ምትክ ቦታ የከተማ መሬት ባለይዞታ ከይዞታው በቋሚነት ተነሺ በሚሆንበት ጊዜ የሚከፈለው የልማት ተነሽ ካሣ እና የሚሰጠው ምትክ ቦታ በሚከተለው አግባብ ይሆናል፦
#በቋሚነት ለሚነሳ የከተማ መሬት ባለይዞታ ምትክ ቦታ ወይም መኖሪያ ቤት በግዥ እንዲያገኝ ይመቻቻል፡፡
የሚሰጠው ምትክ ቦታ ከሆነ በቦታው ቤት እስኪገነባ ለሁለት ዓመት የሚኖርበት ቤት ያለኪራይ ይሰጠዋል ወይም ለፈረሰበት ቤት በወቅታዊ የኪራይ ግምት ተሰልቶ የሁለት ዓመት የልማት ተነሽ ካሣ ይከፈለዋል፡፡
የሚሰጠው ምትክ ቤት ከሆነ ለፈረሰበት ቤት በወቅታዊ የኪራይ ግምት ተሰልቶ የአንድ ዓመት የልማት ተነሽ ካሣ ይከፈለዋል፡፡
የልማት ተነሽ ካሣ መጠን ቢያንስ የአካባቢውን ዝቅተኛ የቤት ኪራይ ለመከራየት ከሚያስችል ያነሰ መሆን የለበትም፡፡
ተነሺዎች በነበሩበት አካባቢ ለነበራቸው የማህበራዊ ትስስር መቋረጥና ለሚደርስ የሥነ-ልቦና ጉዳት ማካካሻ ይከፈላቸዋል፡፡ መጠኑ ይህን አዋጅ ለማስፈጸም በሚወጣ ደንብ ይወሰናል፤
የሚለቀቀው የሊዝ ይዞታ ከሆነ የሚሰጠው ምትክ ቦታ ከተለቀቀው መሬት በደረጃ እና በስፊት ተመጣጣኝ መሆን አለበት፡፡ ይህንን ለመፈፀም የማይቻል ከሆነ አማራጭ የአፈፃፀም ሁኔታ እንደየከተሞቹ ተጨባጭ ሁኔታ በመመሪያ የሚወሰን ይሆናል፡፡
የምትክ ቦታ ወይም ቤት አሰጣጥ፣ የልማት ተነሽ ካሣ እና ተያያዥ ጉዳዮች ዝርዝር አፈፃፀም ክልልች፣ አዲስ አበባ እና ድሬደዋ ከተማ አስተዳደሮች በሚያወጡት መመሪያ ይወሰናል፡፡
በጊዜያዊነት ስለሚነሳ የከተማ መሬት ባለይዞታ የሚሰጥ የልማት ተነሽ ድጋፍ፡-
በጊዜያዊነት ለሚነሳ የከተማ ባለይዞታ ተነስቶ ለሚቆይበት ጊዜ ምትክ ቤት ወይም በወቅታዊ የኪራይ ግምት ተሰልቶ ተመጣጣኝ ቤት የሚከራይበት ክፍያ እንዲያገኝ ይደረጋል፡፡
የከተማ ባለይዞታዎች በጊዜያዊነት በመነሳታቸው ምክንያት ሊጡት ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ካሳ ይከፈላቸዋል።
የዚህ ንዑስ አንቀጽ ዝርዝር አፈፃፀም ክልልች፣ አዲስ አበባ እና ድሬደዋ አስተዳደ ሮች በሚያወጡት መመሪያ ይወሰናል፡፡
3. #ገቢ በመቋረጡ ስለሚከፈል የኢኮኖሚ ጉዳት ካሣ
ለሕዝብ ጥቅም ተብሎ ቦታ እንዲለቀቅ ከመደረጉ ጋር በተያያዘ ከይዞታው ሳይነሳ በጊዜያዊነት ወይም በዘላቂነት ሲያገኝ የነበረው ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ለተቋረጠበት ሰው የጉዳት ካሳ የሚከፈል ሲሆን ካሳው ስለሚገባው ተጎጂ እና የጉዳት ካሣው መጠንና አይነት ክልል በሚያወጣው መመሪያ የሚወሰን ይሆናል።
የካሳዉን መጠንና ዓይነት ለመወሰን ከመቀጠር፣ ከንግድ፣ ከኪራይ ከእርሻ ውጪ መሬትን በመጠቀም የሚገኝ ገቢ እና የመሳሰለ ዓመታዊ የተጣራ ገቢን ታሳቢ ሊያደርግ ይችላል፡፡
4. #ከገጠር ወደ ከተማ ለተካለለ የከተማ አካባቢ ባለይዞታ የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ ስለመወሰን
#ከገጠር ወደ ከተማ በተካለለ የአርሶ አደር ይዞታ ከመኖሪያ ቤቱ ለሚነሳ ባለይዞታ በክልል፣ በአዲስ አበባ እና በድሬደዋ ካቢኔ የሚወሰን ሆኖ የከተማውን ስታንዳርድ በመጠበቅ ከ500 (አምስት መቶ) ሜትር ካሬ ያልበለጠ የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ መሰጠት አለበት፡፡
ዕድሜው 18 ዓመትና በላይ ለሆነው የባለይዞታውን ገቢ በመጋራት አብሮ የሚኖር አርሶ ወይም አርብቶ አደር ልጅ የቦታ ስፋቱ የከተማውን አነስተኛ የመሬት ይዞታ ደረጃ የሆነ ለመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ መሰጠት አለበት፡፡
ለመኖሪያ የሚሰጠው ጠቅላላ የቦታ መጠን ከነበረው የመኖሪያ ይዞታ በላይ መሆን የለበትም፡፡
የመኖሪያ ይዞታ መጠን የባለይዞታው መኖሪያ ቤት ያረፈበትና የአጥር ግቢውን ይጨምራል፡፡
የዚህ አንቀፅ ዝርዝሩ አፈፃፀም ክልል፣ አዲስ አበባ እና ድሬደዋ ከተማ አስተዳደሮች በሚያወጡት መመሪያ ይወሰናል፡፡
5. #መልሶ ስለማቋቋም
የክልል መንግሥት፣ የአዲስ አበባ እና የድሬደዋ አስተዳደር ለካሣ ክፍያ እና ለመልሶ ማቋሚያ ፈንድ ያቋቁማል፤
ክልልች፣ አዲስ አበባ እና ድሬደዋ ከተማ አስተዳደሮች ተነሺዎችን በዘላቂነት ለማቋቋም የሚያስችል ማቋቋሚያ ማዕቀፍ የመቅረጽ ግዴታ አለባቸው፡፡
የከተማ ወይም የወረዳ አስተዳደር በተቀረፀው ማቋቋሚያ ማዕቀፍና በሚመደበው ማስፈጸሚያ በጀት ተነሺዎችን የማቋቋም ግዴታ አለበት፤
በገጠርም ሆነ በከተማ ለሕዝብ ጥቅም መሬት የሚለቀቀው ለኢንቨስትመንት ከሆነ ተነሺዎች ከኢንቨስትመንቱ የሼር ባለቤት ሊሆኑ ይችላል፡፡
በገጠርም ሆነ በከተማ የልማት ተነሺ በሼር ለመጠቀም ፍላጎት ኖሮት ባለሀብቱ ይህንን ለማድረግ የሚያስችለው ሁኔታ ካለ ባለሀብቱ ለተነሺዎች የኢኮኖሚ አስቻይ ተለዋጭ መፍትሄ በተነሺው፣ በባለሀብቱ እና በአስተዳደሩ መሰጠት አለበት፡፡ ዝርዝሩ በደንብ ይወሰናል፡፡
የመልሶ ማቋቋሚያ ማዕቀፍ ይዘትና ዝርዝር አፈፃፀም በደንብ ይወሰናል፡፡
6. #ንብረት ስለመገመት
እንዲለቀቅ በሚፈለግ መሬት ላይ ለሚገኝ ንብረት ካሣ የሚወጣውን አገር አቀፍ ቀመር መሠረት በማድረግ በተመሰከረለት የግል ድርጅት ወይም ግለሰብ አማካሪዎች ይገመታል፡፡
የካሣውን መጠን የሚገምት የተመሰከረለት የግል ድርጅት ወይም ግለሰብ አማካሪዎች ከሌለ ራሱን የቻለ በመንግሥት በተቋቋመ ተቋም ይገመታል፡፡
የካሣውን መጠን የሚገምት ድርጅት ከሌለ የሚለቀቀው መሬት እንደሚገኝበት አካባቢ የሚመለከተው የወረዳ ወይም የከተማ አስተዳደር ተገቢው ሙያ ያላቸው አባላት የያዘ ገማች ኮሚቴ በማቋቋም የሚገመት ይሆናል፡፡
በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 3 መሠረት የሚቋቋመው ገማች ኮሚቴ ሥራውን የሚያከናውንበት የአሠራር ሥርዓት ክልል፣ አዲስ አበባ እና ድሬደዋ ከተማ አስተዳደሮች በሚያወጡት መመሪያ ይወሰናል፡፡
የሚነሳው ንብረት የተለየ እውቀት የሚጠይቅ ሲሆን አግባብ ባለው የመንግሥት ወይም የግል ድርጅት ሊገመት ይችላል፡፡
የሚነሳው ንብረት የመንግሥት መሠረተ ልማት ወይም የአገልግልት መስመር ከሆነ የካሣ ግምቱ የሚዘጋጀው በንብረቱ ባለቤት ይሆናል፡፡
የካሣ ግምት የሚሰላበት ነጠላ ዋጋ ቢበዛ በየሁለት ዓመቱ መከለስ አለበት።
ይህም ለሕዝብ ጥቅም ሲባል የመሬት ይዞታ የሚለቀቅበት፣ ካሣ የሚከፈልበት እና ተነሺዎች መልሰው የሚቋቋሙበትን ሁኔታ ለመወሰን የወጣ አዋጅ ቁጥር 1161/2011 አንቀጽ 11-17 በግልጽ ተደንግጓል።

©℗®

https://t.me/Consultancy2012
Call us for
©Tsegaye Demeke - Lawyer

30/09/2022

Southern Nations, Nationalities, and Peoples' Region Southern Nations, Nationalities, and Peoples' Region is one of the nine ethnically based regional states of Ethiopia. It was formed from the merger of five kililoch, called Regions 7 to 11, following the regional council elections on 21 June 1992. Its capital is Awasa.

29/09/2022
Want your school to be the top-listed School/college in Akaki Beseka?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Website

Address

Halaba
Akaki Beseka