Yetneberk Tadele
Fact based insights on Ethiopia’s politics, economy & society. Open dialogue via comments & messages NB: Please read our RULES before commenting on this page
1.
No hate speech is allowed
2. Do not use obscene, rude, crude, or insulting nicknames towards the admin of this page.
3. Do not harass, threaten, embarrass, swear at, sexually harass or abuse another participant.
4. For your safety, please do not post personal information like (ID number, phone number, smart card number) on our wall or in the comments.
5. One-liner comments that are negative, def
ህገ መንግስቱ እንዳይሻሻል!!!!....እኔ ለበርካታ አመታት የኢትዮጵያ ወቅታዊ ዋነኛ ችግር ህገ-መንግስቱ ብቻ መስሎ ነበር የሚታየኝ። ህገ መንግስቱ ተሻሽሎ የሀገራችን አስተዳደር ከቋንቋ ጫንቃ ላይ ቢወርድ ችግራችን ሁሉ ኢምንት ሆኖ ይሰማኝ ነበር። በዚህም ምክኒያት ብዙ ጊዜ “ህገ-መንግስቱ ይቀደድ” እስከማለት ደርሼ ነበር።.....
....መኖር ደግ ነው፣ ዛሬ እየቆየሁ ብዙ ነገር ሳስተውል የኢትዮጵያ ችግር ህገ መንግስቱ ብቻ እንዳልሆነ እየተገነዘብኩ ነው። የህገ መንግስቱ መሻሻል ብቻውን ለኢትዮጵያ ሰላምና መረጋጋት የህዝብ መደማመጥና መግባባት የሚያመጣ መስሎ አልታየኝም።.....
ዛሬ “ህገ-መንግስቱ ይሻሻል” የሚለው ጥያቄ የየትኛውም የፖለቲካ ፓርቲ ወይም የየትኛውም የትጥቅ ታጋይ ጥያቄ አለመሆኑን ከመረዳቴም ውጪ ከዚያ በላይ የሆኑ ብዙ ጉዳዮች እንዳሉ ተገንዝብያለሁ! ይልቁንም “ህገ መንግስቱ ይሻሻል” የሚል ጥያቄ ማንሳት ከገዢው ፓርቲ ብቻ ሳይሆን ከተቃውሞው ጎራም ጋር የሚያጋጭ ጥያቄ ሆኖ ታይቶኛል።.....
እንግዲህ ሳይቸግረኝ የብቻ ጉዞ ጀምሬ በአውሬ መበላት አልሻም። ከሁሉም መጋጨት አልፈልግምና እባካችሁ “ህገ-መንግስቱ አይሻሻል”.........!!!!
ህገ መንግስቱን "እየሞትንበትም እንኑርበት" የሚል ህዝብ ቁጥር እየበዛ ከመጣ እንግዲህ በብዙሀን ድምጽ መሸነፍ የሚለውን አስተሳሰብ እቀበላለሁና..... ህገ-መንግስቱን አታሻሽሉት!! እየሞታችሁ ኑሩበት!!!!
ሀገሬንም ቢሆን ሼጬ ረሀቤን ላስታግስ እያለ በየዩትዩቡ ላይ አጀንዳ እየቀፈለ የግሉን መከራ በሀገር ላይ ጥሎ የሚበላ ጎጠኛ ሁሉ ነው እየተነሳ እንደ ታማኝ በየነ ያለን ታላቅ ሰው ልሳደብ የሚል! ጠባብ መንደርተኛ!!
07/05/2026
ታማኝ ለጎጠኛ ለጠባብ ነውጤ አይመችም!!!
ታማኝ በየነን ወይስ.....?
06/05/2026
ስማኝማ ባሻዬ:- ካለ ፌርማታህ አልተንቀዠቀዠክም፣ ለሺህ ትችቶች ሺህ መልስ እያለህ ከሚዛንህ ውልፍት ሳትል ራስህን አክብረህ ተከብረሃል።
ሰማንያ ሚሊዮን ኢትዮጵያዊ በኢህአዴግ የጭቆና በትር እየተገረፈ በአርምሞ ልጓም በተጠፈነገ ጊዜ ሞትን ሳትፈራ ቀና ብለው ሊያዩት የሚያርደውን መንግስት ፊት ለፊት ተጋፍጠሃል።
ስለ ሃይማኖት ሳትዘፍን ይሄ ወፈ-ሰማይ ሃይማኖተኛ ሁላ እንደ ግሪሳ ይነሳብሃል፤ ስለ ብሔር ሳታቀነቅን ሰርክ "ኢትዮጵያ፥ኢትዮጵያ" ማለትህ ያንገበገበው ሁላ ኢትዮጵያ አማራ ወይም ትግራይ ብቻ ትመስል የጎሪጥ ያይሃል።
ዘፈን ኢትዮጵያ ውስጥ ሚያዝያ ስምንት ከቀኑ 8:00 ሰዓት 2018 ዓ.ም የተጀመረ ይመስል ሁሉም ዘፋኝነትህን እያወገዘ ለራሱ የፅድቅን አክሊል ይሾማል።
ባንተ ልክ ለኢትዮጵያ የተሰፋላት፥ ኢትዮጵያ በክት ልብሷ ልክ የለበሰችው፥ በሃገሬ ልክ ጥንቅቅ ብለህ የተፈጠርክ ሰንደቅዓላማዋ መሃል ላይ በክብር መቀመጥ የነበረብህ አርማችን ነህ።
ድግሴ ላይ ተገኙልኝ፣ ሙዚቃዬን አድምጡልኝ ብለህ ሳትጠራው ምድረ- አህዛብ በሃይማኖቱ ያላገኘውን ዝና አንተን በማብጠልጠል ሊቀዳጅ ይጋጋጣል😂😂
አክቲቪስትነቱን፥ ዘማሪነቱን፥ጋዜጠኝነቱን፥ ሰባኪነቱን፥ ቄስነቱን፥ ኡስታዝነቱን፥ ፓስተርነቱን አንተ የምታፀድቅለት ይመስል ሁሉም አንተን በመዘርጠጥ አፏን ያሟሻል።
ዘፋኝ ነህ፤ ሃጢያተኛ ነህ የሚሉህ አንተ ግን "የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው" አይነት ዝምታን ተጎናፅፈህ ከሚገባህ በቀር ቃል ሳታባክን ከነ ክብርህ ስዩምህ ላይ ተሰይመሃል።
👉ቴዲዬ ለኔ በሳምንታት መካከል የምወዳትን ቀን ቅዳሜዬን ነህ
👉ከመብል መካከል አጥብቄ የምወደውን ቁርጥ ስጋዬ ነህ
👉ከጀግና መካከል ለኔ አጥብቄ የማደንቀው እምዬ ምኒሊክ በፊታውራሪ ገበየሁ ተፈርሾ ነህ
👉ከአትሌት መካከል እጅግ የምወዳቸው ቀነኒሳ በሃይሌ ለብለብ ነህ
👉ከሃገራት መካከል አብልጬ የምወዳት ኢትዮጵያዬ ነህ
👉 ከአሸናፊነቶች ሁሉ የምወደው የኔ አድዋዬ ነህ
የነበርክበት ላይ ያልነበረ፥ ያሳለፍካቸውን አረር ቀናት ያልቆጠረ፥ የተዋደቅክለትን የ27 እና የ28 ዓመታት የኪነት ዋርካነት በአንዴ ሊገነድስብህ የሚቃጣው፥ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ እያልህ ስትቀኝ ብሄሩ ስር ተወሽቆ የነበረ ሁላ ዛሬ አንተ ላይ ሂሱን ያዘንባል😂😂
አንተን ልጠላህ አይደለም ልገልፅህ ሁላ ቃላት እደኸያለሁ፤ ለግፉዓን ድምፅ መሆን ያልቻሉ፥የህዝብን እሪታና ዋይታ ንቀው ከገዢ ጋር ያ'በሩ፥ ስለተፈናቀሉ ንፁሃን አርምሞን የመረጡ፥ ነገር ግን ሞገስ አልባ የሃይማኖት ካባን የደረቱ ፈሪሳዊያን ተቺዎችህን ሳይ ባይቀኑብህ ነበር የሚገርመኝ ብዬ እገረምብሃለሁ።
የተፈተነ ህይወት፥ የማይደበዝዝ አሻራ፥ ያልተገደበ ድፍረት፥ የማይነጥፍ ጅረት፥ የማይፈታ ኪነት፥ የማይታረም እውነት፥ የማይታበል እምነት፥ ያልታሰረ ህሊና፥ የሚፈቀር ልቦና ይዘህ እነ ማንም ዝም ባሉ ሰዓትም ሆነ እነ ማንም መናገር በጀመሩ ሰዓት ነበርህ።
ከከንቱ የሃይማኖተኝነት ድሪቶ፥ ካልተኖረ የስብከት ጋጋታ፥ ከተደበቀ የዘረኝነት ፍላፃ፥ ከማያንፅ ከንቱ ትችት ይልቅ 18 ሙዚቃዎችህ ትውልድን ያንፃሉ🙏🙏🙏
@ የሽጥላ
05/05/2026
ተቆጡ … በቁጣችሁ ላይ ግን ፀሀይ አይግባ:: ኤፌሶን 4:26
05/05/2026
በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዕውቅናው የተሰረዘው ህወሐት፤ የዛሬ ስድስት ዓመት «ለጦርነት መቀስቀስ ምክንያት» ነበር የተባለለት ምርጫ አካሂዶ የተመረጡ የምክርቤት አባላትን ሰብስቦ ፕሬዝደንትና አፈ ጉባኤ መረጠ።
ምክርቤቱ የቀድሞው የክልሉ ፕሬዝደንት ደብረጽዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር) ን ፕሬዝደንት፤ ወይዘሮ ኪሮስ ሐጎስን አፈ ጉባኤ፤ ወይዘሮ ምሕረት በርሀን ደግሞ ምክትል አፈ ጉባኤ አድርጎ መምረጡን የትግራይ ቴሌቪዥን ዘግቧል።
አሁን በሥልጣን ላይ ያሉት የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝደንት ጀነራል ታደሰ ወረደ ቀደም ሲል በሰጡት መግለጫ ድርጊቱን የፕሪቶሪያውን ውል የሚጥስ መሆኑን ገልጸው ሥልጣናቸውን እንደማያስረክቡ ተናግረዋል።
የህወሐት ድርጊት ሕገመንግሥቱን የጣሰና ለሕገመንግሥታዊ ሥርዓቱ ዕውቅና የነፈገ ተግባር ነው የሚሉት የፖለቲካ ተንታኞች ድርጊቱ ወደ ጦርነት ሊያመራ እንደሚችል እያስጠነቀቁ ይገኛሉ።
DW
04/05/2026
በእስር ላይ የሚገኙ ከአርቲስት ቴዎድሮስ ካሣሁን (ቴዲ አፍሮ) ጋር ቅርበት ያላቸው ሰዎች ቁጥር ሰባት መድረሱ ተሰማ። ዶቼ ቬለ ያነጋገራቸው ከቴዲ አፍሮ ጋር የቅርብ የሥራ ግንኙነት ያላቸው ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁት የመረጃ ምንጭ እንደገለጹት፤ ከአርቲስቱ ቅርብ ጓደኛ አቶ ዩሲፍ ያሲን እና አዲስ የሙዚቃ ሥራዎቹ በዩትዩብ መድረክ ማስታወቂያ እንዲታጀቡ አስፈላጊ ሂደቶችን ለማመቻቸት ጀምራ ከነበረው ወይዘሮ ማኅሌት ሰለሞን(በትክክለኛ ስሟ ሃና ሰለሞን) ሌላ ሁለት የቴዲ አፍሮ ስቱዲዮ ጠባቂዎችም ታስረዋል። በተጨማሪም ከአርቲስቱ ድረገጽ ጋር የተያያዙ ሥራዎችን የሚሠራ አንድ ሰው፤ እንዲሁም ሞምባሳ በተደረገው የሙዚቃ ድግስ (ኮንሰርት) ላይ ተሳትፎ የነበራቸው ሌሎች ሁለት ሰዎችም በዚሁ ሰሞን መያዛቸውን አረጋግጠዋል።
የታሰሩት አዲስ አበባ ሲኤሚሲ በሚባለው አካባቢ የሚገኘው የቴዲ አፍሮ ስቱዲዮ ጠባቂዎች ድርጊቱ በተፈጸመ ዕለት ሚያዝያ 15 ምሽት ሦስት ሰዓት ገደማ ስቱዲዮውን በዘረፉት አካላት ድብደባ እንደደረሰባቸውንም በድጋሚ አስረድተዋል። በዚህ ስፍራ ኤ እና ቢ ያሏቸው ሁለት ስቱዲዮዎች መኖራቸውንም አስረድተዋል። የተጠቀሱት አካላት «በገመድ አምስተኛ ፎቅ ወደሚገኘው የአርቲስቱ ስቱዲዮ ለመግባት ሞክረው ሳይሳካላቸው ሲቀር በበር ለመግባት ሲሉ በመከላከላቸው ደብድበዋቸው ሰብረው በመግባት ከሁለቱም ስቱዲዮዎች ሁለት ላፕ ቶፖች፤ አራት ስፒከሮች፤ እንዲሁም የተለያዩ መሣሪያዎችን ወስደዋል፤ የተሰባበሩ ነገሮችም አሉ በአጠቃላይ ስቱዲዮውን ከጥቅም ውጪ አድርገውት ወጥተዋል» ብለዋል። ሆኖም በማኅበራዊ መገናኛ ብዙኀን የሚዘዋወሩ ፎቶዎች እውነተኛ እንዳልሆኑ ለዶቼ ቬለ ገልጸዋል።
ከታሠሩት ውስጥ እስካሁን ፍርድ ቤት የቀረቡት ሁለቱ ማለትም አቶ ያሲን እና ወ/ሮ ማኅሌት (ወ/ሮ ሃና) ብቻ እንደሆኑ የተናገሩት የመረጃ ምንጩ፤ በእነሱ ላይም ፖሊስ የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ እንደጠየቀባቸው ለዶቼ ቬለ አስረድተዋል።
ዶቼ ቬለ ስለታሠሩት እንዲሁም ፍርድ ቤት ቀርበው የ14 ቀን ጊዜ ተጠየቀባቸው ስለተባሉት ሰዎች ከፌደራል ፖሊስ መረጃ ለማጣራት ጥረት አድርጓል። በስልክ ያነጋገርናቸው የፌደራል ፖሊስ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ጀላን አብዲ፤ ለጊዜው በፍርድ ቤት በተያዘ ጉዳይ ላይ መረጃ ለመስጠት እንደማይችሉ ተናግረዋል።
ኢቶሪካ የተሰኘው በቅርቡ የወጣው የክብር ዶክተር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሣሁን ቴዲ አፍሮ የሙዚቃ አልበም በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ዕይታ እያገኘ መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ። እስካሁን «ዳስ ጣል» የተሰኘው ሥራው ብቻ ያገኘው ዕይታ 22 ሚሊየን ደርሷል።
DW
ለንገሩኝ ባይ ኡስታዝ ..... ለምን ይዋሻል?!
መሬማ በሀረብኛ
02/05/2026
ነጃሺ የተባለ ንጉስ ኢትዮጵያ ውስጥ ኖሮ አያውቅም!!! የፈጠራ ታሪክ ደጋግማችሁ ስላወራችሁ እውነት አይሆንም! ንጉስ አርማህ ነበር የነብዩን ቤተሰቦችና ወዳጆች ተቀብሎ በእንክብካቤ አኑሮ የሸኛቸው። ሀገር ያጠፋውን ግራኝ አህመድ ታሪክ ሰንዳ፣ ቁሳቁሶቹን ሁሉ ሳይቀር በቅርስነት ያስቀመጠች ቤተክርስትያን፣ የዮዲት ጉዲትን ታሪኮች ሰብስባ የያዘች ቤተክርስትያን፣ ንጉስ ሲሰልምና ሀገር ሲያስተዳድር አላየሁም ብላ ዝም ልትል አትችልም፣ እሷ ዝም ብትል እንኳ ታሪክ በመዘከር የምትታወቅ ሀገር ንጉስ ሆኖ ጸሀፌ ትዛዛቱ ስለሰውዬው ምንም ነገር ሳይጽፉ ሊያልፉ አይችሉም ፣ ሁሉ ቢቀር በአፍ የተላለፈ ታሪክ ይኖር ነበር። ነጃሺ የፈጠራ ንጉሳችሁ ነው፤ እሱን ይዛችሁ የኢትዮጵያ ጉዳይ ሲነሳ ሀይማኖት በሰማያዊ ተስፋ መሆኑ ቀርቶ በኢትዮጵያ ታሪክ የሚጸና ይመስል ሁሌ ለልቅሶ ነጠላ አቀብሉኝ ማለት ትችላላችሁ! በዚህ ረገድ ድሮም አሁንም ወደፊትም መብታችሁ የተጠበቀ ነው!!
Click here to claim your Sponsored Listing.