ZaB

ZaB

Share

Education, entertainment, and other political and political free information are shared via this page

14/06/2026

የ 2019 ዓ.ም ካፒታል በጀት ውስጥ ከፍተኛ በጀት የተመደበላቸው የስራ ዘርፎች



ZaB like and follow for more

13/06/2026

በአሜሪካ፣ ፔንሲልቬኒያ ግዛት ምክር ቤት መጋቢት 2 ቀንን በግዛቱ የቀን መቁጠሪያ ውስጥ ቋሚ "የአድዋ ቀን" አድርጎ በከፍተኛ ድምፅ ማፅደቁን የኮሎራዶ ግዛት የአውሮራ ከተማ ምክር ቤት እና የሪፐብሊካን ፓርቲ አባል የሆኑት ትውልደ ኢትዮጵያዊው አቶ አምሳሉ ፀጋዬ ገልጸዋል።

ውሳኔው በምክር ቤቱ አሠራር ሂደት ረጅም ጊዜ የወሰደ ቢሆንም፣ የኢትዮጵያ አርበኞች እ.አ.አ በ1896 በአፄ ምኒልክና በእቴጌ ጣይቱ መሪነት የጣሊያንን ወራሪ ጦር ድል ያደረጉበትን 130ኛ ዓመት በዓል ለመዘከር የተላለፈ ሲሆን ውሳኔው በግዛቱ ደረጃ እንጂ ወደ ፌደራል የሚሻገር አይደለም።

ይሁን እንጂ ድሉ የኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን የጥቁር ሕዝቦች ሁሉ የነፃነትና የፀረ-ቅኝ ግዛት ምልክት በመሆኑ የአድዋ በዓል በተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች ዕውቅና እያገኘ መምጣቱ ወደፊት ጉዳዩን ወደ ፌደራል ደረጃ ለማድረስ ትልቅ ዕድልና ተስፋ ይፈጥራል።

(ቢቢሲ አማርኛ)

ZaB like this page get more

Photos from ZaB's post 11/06/2026

አዲሱ የተሽከርካሪዎች መለያ ሰሌዳ (ታርጋ) ዋጋ

ዛሬ በአዲስ አበባ ከዚህ ቀደም ለተመዘገቡና ወረፋ እየጠበቁ ላሉ አዲስ መኪና ለገዙ ተገልጋዮች አዲሱ ታርጋ መሰጠት ተጀምሯል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለአዲሱ ታርጋ የተተመነውን ታሪፍ ዶክመንት ተመልክቷል።

የነዳጅ (የፊትና የኋላ ታርጋዎችን ጨምሮ) እንዲሁም የኤሌክትሪክ እና የተፈጥሮ ጋዝ ተሽከርካሪዎች ታሪፍ በየደረጃው በዝርዝር ተቀምጧል።

በዚህም ፥
- የከተማና የሃገር አቋራጭ አውቶቡሶች፣
- የአካል ጉዳተኞች (PD) ተሽከርካሪዎች፣
- የመንግሥት ተሽከርካሪዎች፣
- ባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪዎች (ባጃጅ) የሰሌዳ ዋጋ ለነዳጅ 9,400 ብር ሲሆን፣ ለኤሌክትሪክና ተፈጥሮ ጋዝ ደግሞ 7,100 ብር ሆኖ ታሪፍ ወጥቶለታል።

ለሕዝብ ታክሲ ትራንስፖርት ለነዳጅ 11,700 ብር ለኤሌክትሪክ ደግሞ 9,400 ብር ክፍያ ተቆርጦለታል።

በከፍተኛው የዋጋ ተመን የተመደቡት ፦
- የግል መገልገያ፣
- የንግድ፣
- የዲፕሎማቶች፣
- የዕርዳታ ድርጅቶች፣
- ዓለም አቀፍና አህጉር አቀፍ ድርጅቶች እንዲሁም የልዩ ተንቀሳቃሽ ተሽከርካሪዎች ሰሌዳዎች ሲሆኑ ለእነዚህ ዘርፎች ለነዳጅ ታርጋ ዋጋ 56,000 ብር፣ ለኤሌክትሪክና ተፈጥሮ ጋዝ ታርጋ ዋጋ ደግሞ 44,500 ብር ተቆርጧል።

በተጨማሪም የድንበር ተሻጋሪ የጭነት ትራንስፖርት ተሽከርካሪዎች የነዳጅ ሰሌዳ 28,500 ብር ፣ የኤሌክትሪክ ሰሌዳ 15,200 ብር ታሪፍ ተቆርጦላቸዋል።

ዝቅተኛው የዋጋ ተመን የተቆረጠው ለባለ ሁለት እግር (ሞተር ሳይክል) ተሽከርካሪዎች ሲሆን ዋጋውም ለነዳጅ 4,700 ብር እንዲሁም ለኤሌክትሪክ 3,550 ብር መሆኑ ታውቋል።

ZaB Follow and like this page for more

05/06/2026

Like and follow ZaB : Enjoy 😃

04/06/2026

/// " ብዕር ገደል ይግባ!!! " ///

ከእውነት ጎን ቆሞ ግፍን ካልሞገተ፣
በተበዳይ ሚዛን ሰፍሮ ካልዘመተ፣
ጥበብ ገደል ይግባ ብዕር ይሰባበር፤
ከግፈኞች ጋራ በሀሰት ከሚያብር!!!
ከእናት ጎን ቆሞ ግፍን ካልረገጠ!
ለእህት ተከራክሮ ፍትሕ ካላሰጠ!
ለህት እንባ ስቃይ ቀድሞ ካልደረሰ!
የግፈኛን ድልድይ ከአላፈራረሰ!!!
ጥበብ ምን አባቱ ብዕር ገደል ይግባ!
መፍትሔን ካላመጣ ለምስኪኖች እንባ።
/// ስንታየሁ ሀብታሙ ///

Follow and like ZaB
ስንታየሁ ሀብታሙ የጥበብ ጥመኛው

04/06/2026

እንደጻፈችው.....

አንዲት የሥራ ፈጠራ ሃሳብ ይዘው የገንዘብ ሽልማቱን ብቻ ለመውሰድ አሉ የተባሉ ውድድሮች ላይ ሁሉ ይሳተፋሉ። ሃሳቡን አሳድገው ወደ ቢዝነስ የመቀየርም ይሁን ችግር የመፍታት ዕቅድ የላቸውም። ብቻ እዚያም እዚህም የተገኘችውን 'እየቦጨቁ' ጊዜአቸውን ይገፋሉ። እንደነዚህ ያሉ የሥራ ፈጣሪዎች ''Grantpreneurs'' ወይም ''Pitchpreneurs'' እንላቸዋለን።

መንግሥት ሥር ተለጥፈው በመንግሥት ትላልቅ መ/ቤቶች በኩል ከሕዝብ ለመቀፈል ለየት ያለ ፕሮፖዛል ይዘው የሚቀርቡም ሞልተዋል። ''አስካሉ ካን'' የተሰኘው ድርጅት የ 2010ኡን የደ/አፍሪካ የዓለም ዋንጫን አስታክኮ ሕዝቡን ከመግፈፉ በፊት በርካታ ፕሬዘንቴሽኖችን ለተለያዩ የመንግሥት ባለሥልጣናት ሲያቀርብ እንደነበር አስታውሳለሁ። የመንግሥት ባለሥልጣናትን በማታለል (በጥቅም በመደለልም ጭምር) እንዲሁም በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ማስታወቂያ በማስነገር ጭምር የሰራው ሿሿ የሚታወስ ነው። የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ማስታወቂያ ስለመጣ ብቻ አያስተላልፍም። ጥብቅ የውስጥ ሕጎች አሉት። ያንንም በጥሶ ለማለፍ ችሏል። የዚህ ብጤዎቹ ''Govpreneurs'' ብንላቸውስ? መንግሥትን የተደገፉ 'ሿሿ ሥራ ፈጣሪዎች'!

''Govpreneurs'' ባሕሪያቸው ተመሣሣይ ነው። ይህንን ለማየት ከሰሞኑ የአሽከርካሪነት ብቃት ማረጋገጫ/ፈቃድ እንድናወጣ አይናቸውን በጨው አጥበው የመጡ ግለሰቦች/ድርጅቶችን እንመልከት!

1ኛ. ''የሕዝብ ችግር እንፈታለን'' ይላሉ። (በመኪና አደጋ ብዙ ሰው እያለቀ ነው፤ የተደራጀ የመረጃ ሥርዓት የለም፤ ፎርጂድ የመንጃ ፈቃዶች ቁጥራቸው የትየለሌ ነው። ''መፍትሔ ይዘን መጥተናል'')

2ኛ. ''በዝቅተኛ ዋጋ አገልግሎቱ ይቀርባል'' ይላሉ። (የምዝገባ፣ የፈተናና የፈቃድ ሕትመት ''በነፃ'' ነው። ስልጠናውን ግን ወደ ድርጅቶቻችን ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻችን ቀርባችሁ ከፍላችሁ ትስተናገዳላችሁ። ''Almost በነፃ በሉት'' 😂)

3ኛ. ''የተመቻቸ የአከፋፈል ሥርዓት አለን፤ አገልግሎቱንም በሚቀርባችሁ ማዕከል ታገኛላችሁ'' ይላሉ። (ብዙ የባንክ ወይም ሌላ አማራጭ ያቀርባሉ፤ ገንዘቡ እስከተገኘ ድረስ እንኳን ለማሽከርከር ስልጠና ማዕከልነት ቀርቶ ለዝንጀሮዎች መዝለያ የማይሆን ኮረብታማ ቦታ ቢሆንም 'ሰልጥን' ልትባል ትችላለህ''

4ኛ. በተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ''ጅንጀና'' አይሉት ፕሮሞሽን እንዲሁም በተገኙት ሚዲያዎች ሁሉ እዚህም እዚያም እንዲቀርብ ያደርጋሉ። ('ዕድሜ' ለፊንቴክ ይቺ ለጥቂት ወራት አትኖርም)

5ኛ. የመንግሥት መ/ቤት ኃላፊዎች ሊቀየሩ የሚችሉባቸውን ጊዜያት ይጠብቃሉ። (ከምርጫ በኋላ መንግሥት ኃላፊዎቹን ወይም የሥር ሹመኞችን እንደሚቀያይር ይጠበቃል። ስለዚህ እነዚህ ሹመኞች ላይ ተጽዕኖ ለማሳደር ሁኔታዎችን ምቹ ያደርጋቸዋል፤ በሙስና ለመጥለፍም ምቹ ነው)

መፍትሔው ምንድነው?

የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ መ/ቤት ''ፊንቴክ'' በተባለ አጭቤ ድርጅት ወጥመድ ውስጥ ወድቆ እንደነበር እናስታውሳለን። እነዚህ በመንጃ ፈቃድ ጉዳይ በደሃው ገንዘብ እንጀራቸውን ሊያበስሉ የመጡ ሰዎች ደረጃ አንድ የሿሿ ተጠርጣሪዎች ናቸው። እናም የእነዚህ govprenuers ዕቅድ እንዳይሳካ የሾፌሮች ማኅበር ወይም ማንም የሚገደው ተቋም ጉዳዩን አደራጅቶ formally ለብሔራዊ መረጃ እና ደኅንነት አገልግሎት መ/ቤት ጉዳዩ እንዲመረመር ገፋ አድርጎም ለጠ/ሚኒስትሩ ጽ/ቤት እንዲደርስ በማድረግ ውሳኔ ማሰጠት መልካም ነው። ከሚኒስቴር መ/ቤት በላይ የጠ/ሚኒስትር ጽ/ቤት ነው ያለው!
ZaB Follow for more
#የሹፌሮችአንደበት

03/06/2026

እረስቸው
የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክ ሚንስትር ድኤታ ክቡር አቶ በርኦ ሀሰን አሽከርካሪውን እንደገና መዝነን ፈትነን የሚል ሰነድ ሰንደው ምዝበራ አቅደው ከመጡት ጋር የተፈራረሙ እውነት ከምዝበራ የዘለለ ጥቅም አለ ብለው አምነው ነው ወይንስ በብላ እንብላ ፖሊሲ ተጠርንፈው ??

በመጀመሪያ በሀገሪቱ በትራፊክ አደጋ እየደረሰ ያለው ውድመት እና ጉዳት ቢያሳስባቸው መስሪያ ቤታቸው ትክክለኛ ጥናትን በማጥናት የችግሩን ምንጭ ለይቶ በማየት አደን ለመቀነስ የሚያስቀር አሰራርን ይዘው ብቅ ይሉ ነበር።

ትናንት የተሰጠን መንጃ ፈቃድ አሰጣጡን ልክ አደለም ብለው አምነው እንመዝን ብለው ከመምጣት በፊት ዛሬም ያ መንጃ ፈቃድ እየተሰጠ ያለበት ሂደትን ለማረም አለመቅረብ በራሱ የፈረሙበት እቅድ ችግርን አደጋን ከማስቀረት ሳይሆን ሀብትን ከማካበት አንፃር የመጣ መላ ምት መሆኑን ያሳያል።

የተከበሩ አቶ በርኦ ሀሰን እርስዎ የሚንስትር ድኤታ ሲሆኑ መቸም እውቀት ይኖራል ታዲያ ይህ ቴዲ የሚሉት ፕሮፖዛሉን ተሸክሞ ልመዝን ሲል ትናንት እርሱ መንጃ ፈቃድ ትምህርት ቤት እያስተማረ ብቁ ናቸው እያለ ያስፈተናቸው ብቁ ሳይሆኑ ነው ብለው ማሰብ እና የልጁን አላማ መረዳት እንዴት ከበደወት ?? ነው ጥቅሙ አወረወት ??

የ Ministry of Transport and Logistics - Ethiopia
ሚንስትር ድኤታ ነወት በምን አግባብ ነው ድርጅቱ ጋር ውል የተፈራረማችሁ ?? ጨረታ አውጣችሁ የነሱ ፕሮጀክት አሸንፎ ነው ?? ወይንስ ፅፈህ ቅረብ እኛ እንፈርማለን ብዙ ሀብትን እናካብታለን ነው ???

ልጠይቀወት እስኪ ትናንት ከተማርንበት ትምህርት ቤት ድጋሜ የምንሄድ ምን የተለየ ትምህርት አለ የመንገድ ዳር ምልክቶች ተቀይረዋል ? የመንገድ ላይ መስመሮች ተሻሽለዋል ???? ስንት ዳገት ቁልቁለት የምንነዳን አውርዳችሁ ቃሊቲ ግቢ ከተማ ላይ ለጥ ባለ መንገድ ንዱ ልትሉን ባልሆነ ???

አቶ በርኦ ሀሰን ብዙ ጊዜ መንግስት ተቋማት ላይ የኮታ ሹመት ይተው ሀላፊወችን ባለሙያወችን በውድድር በብቃት ተመዝነው በፈተና ተፈትነው ትምህርት ዝግጅታቸው ታይቶ ብቃታቸው ተለክቶ ይቀጠሩ ይምሩ ይስሩ የምንል እንዲህ ያሉ ችግሮች ልክ ያልሆኑ ተግባሮች እንደ ተፈራረሙት አይነት ግድፈቶች እንዳይኖሩ በማሰብ ነው።

አቶ በርኦ ሀሰን ዘርፉን አያውቁትም ሾፌሩ እያሳለፈ ያለውን ሂደት አላዩትም ይህ ዘርፍ ሰፊ ሀገራዊ አበርክቶ ያለው ነው አሁን ላይ አሽከርካሪው እያሳለፈ በምን ሁኔታ ውስጥ አልፎ እያገለገለ እንዳለ ግንዛቤ የለወትም።

እስኪ ልጠይቀወት ድንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪ መኪናውን ለማን ሰጦ ነው ወርዶ ሳምንት ተምሮ ፈተና አስቀጥሮ ተፈትኖ 10 ቀን ለሚበልጥ ቀን ሲቆይ ?? የባንክ እዳ ያለበት ባለንብረት መኪና ይህንን ያህል ቀን ሲቆም የሚፈቅድለት ይመስለወታል ??

ሌላው እነዚህ ቀድመን የተማርንባቸው ትምህርት ቤቶች ምን የተለየ ትምህርት ኖሮ ነው ተመልሰን የምንማረው ? በኮምፒዮተር ፁህፍን ሴኪዩሪቲ ካሜራ ባለው ግቢ ነው ተግባር የተፈተን ነን ከ2ቱ ምን የተለየ አፈተታተን መቶ ነው በዘመናዊ ምናምን የምትልን ያዘለች ፕሮፖዛል ይዛችሁ ብቅ ያላችሁ???

የተከበሩ አቶ በርኦ ሀሰን ለዘርፉ ከተጨነቁ ይህንን የምዝበራ ለውጥን የማያመጣ የፍራንክ መሰብሰቢያ የፈረሙትን ሰነድ ቀደው አሽከርካሪ መሰልጠን ካለበት ባለሙያወትን አሰማርተው እንዲ ቢጋዱስ ባሉ ሌሎች ሾፌር በሚበዛባቸው የሙሉ ቀን የግማሽ ቀን ትምህርት ይስጡ የግንዛቤ ማስጨበጥ ፍላጎት ካለ ከዛ ውጭ መከራውን አይቶ በሙቀት ጋይቶ ከአጋች ተርፎ ያመጣትን በከተማ አውደልዳይ ሱፍ ለባሽ ጩሉሌ ለማስነጠቅ አይቅረቡ።
#የሹፌሮችአንደበት

Want your public figure to be the top-listed Public Figure in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Address

Addis Ababa