Singer Tagay W/Mariam
እግዚያብሔር ሁል ጊዜ ልክ ነዉ
06/22/2026
#ዛሬ ማለዳ ስፀልይ ጌታዬ እግዚአብሔር ይህንን ቃል ሰጠኝ::ይሄ ቃል በቤታችሁ ይፈፀም::
👇👇👇👇👇
👉 እንግዲህ በእኛ እንደሚሠራው ኃይል መጠን ከምንለምነው ወይም ከምናስበው ሁሉ ይልቅ እጅግ አብልጦ ሊያደርግ ለሚቻለው፥
ለእርሱ በቤተ ክርስቲያን በክርስቶስ ኢየሱስ እስከ ትውልዶች ሁሉ ከዘላለም እስከ ዘላለም ክብር ይሁን፤ አሜን።ኤፌ 3:20-21
✅እግዚአብሔር አምላኬ እረድቶኝ በአሜሪካን🇺🇸ሃገር በዚህ ዙር የነበረኝን አገልግሎት ትላንት በብዙ የእግዚአብሔር አምላኬ መገኝት አጠናቅቄያለው በህይወቴ የማልረሳውን ጊዜ አሳልፌያለው::በፀሎት በብዙ እቅጣጫ አብራችሁኝ ለቆማችሁ ሁሉ ትልቅ ፍቅር አክብሮት አለኝ ጌታ ዘመናችሁን ይባርክ::ፖርትላንድ ሁሌም
House of God, Cherch ሁሌም የጌታዬን ፍቅር ምጠግብበት ቤቴ ነው ለእኔም ለቤተሰቤም ሁለተኛው ቤታችን ነው ቅዱሳን ነብይ በሻዬ ፓስተር ኤፍሬም እወዳቸዋለሁ::በቅርብ እመለሳለው እንደጌታ ፈቃድ ሰፊ አገልግሎት ይጠብቀኛል::
06/21/2026
#ወንድሜ አሰግድ ደግሞ ሌላ የምስራች ይዞልን ብቅ ብሉዋል ጌታ ቢፈቅድ “ኢየሱስ” የተሰኘው አልበም ሰኔ 20 በማርሲል ቤተክርስቲያን ይመረቃል! ሁላችሁምተጋብዛችዋል እንዳትቀሩ::
Asegid Abebe
06/20/2026
#ሰላም ለሁላችን ይሁን የተወደዳችሁ ቅዱሳን ጌታ ቢፈቅድ እሁድ ማለትም July 21/2026 2pm
🇺🇸በፖርትላንድ House of God international Church ጌታን ለማምለክ እና የእግዚያብሔርን ቃል ለመማር አብረን ለመፀለይ በዚህ አካባቢ ያላችሁ ሁላችሁም ተጋብዛችዋል::ሁላችሁም ወዳጆቻችሁን እየጋበዛችሁ ኑ::ጌታ መልካም ጊዜ ይሰጠናል::ተባረኩልኝ እወዳችዋለሁ::Share ማድረግ አትርሱ::
06/17/2026
Congratulations እንኩዋን ጌታ እረዳህ::
06/16/2026
#ዛሬ ደግሞ በጣም የምወደው የወንድሜ ይዱሻ ልደት ነው::
Happy Birthday 🎂🎉🎁 Yeduyeeee
እግዚያብሔር እረጅም እድሜ ከጤና ጋር ይስጥህ ይዱሻ እወድሃለው::
👉ዴንቨር የፀጋው ወንጌል ቤ/ክ🇺🇸🇺🇸🇺🇸
ድንቅ የአምልኮ ጊዜ እየሰማችሁ ተባረኩበት
#ሊሊሾዬ የእኔ ውድ እህቴ ተባረኪልኝ::
06/14/2026
👉 #ወደ ቤተክርስቲያን ስትሄዱ ሁሌም መፅሐፍ ቅዱሳችሁን መያዝ አትርሱ::
06/12/2026
👉የማለዳ መልዕክታችሁ ነው::
#እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ባይሆን እስራኤል እንዲህ ይበል፡—
እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ባይሆን ሰዎች በእኛ ላይ በተነሡ ጊዜ፥
ቍጣቸውን በላያችን በነደደ ጊዜ፥ በዚያን ጊዜ ያዋን ሳለን በዋጡን ነበር፤
በዚያን ጊዜ ውኃ ባሰጠመን ነበር፥ በነፍሳችንም ላይ ፈሳሽ ባለፈ ነበር፤
በዚያን ጊዜ የጐርፍ ውኃ በነፍሳችን ላይ ባለፈ ነበር።
ለጥርሳቸው ንክሻ ያላደረገን እግዚአብሔር ይባረክ።
ነፍሳችን እንደ ወፍ ከአዳኞች ወጥመድ አመለጠች። ወጥመድ ተሰበረ እኛም አመለጥን።
ረድኤታችን ሰማይንና ምድርን በሠራ በእግዚአብሔር ስም ነው።መዝ 124:1-8
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
#እሁድ ከሰዓት ደግም እግዚአብሔር እንዲህ ያለ መልካም እድል አዘጋጅቶልናል የምትችሉ በዚህ አካባቢ ያላችሁ ሁላችሁም ወዳጆቻችሁን እየጋበዛችሁ ኑ አብረን ጌታን እናምልክ:: ተባረኩልኝ እወዳቸዋለሁ::
06/11/2026
👉✅የማለዳው መልዕክት ነው ይሄ የእናንተ መልዕክት ነው::👇👇👇👇
#ለእናንተ የማስባትን አሳብ እኔ አውቃለሁ፤ ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም።
12 እናንተም ትጠሩኛላችሁ፥ ሄዳችሁም ወደ እኔ ትጸልያላችሁ፥ እኔም እሰማችኋለሁ።ኤር 29:11-12
👇👇👇👇👇👇👇👇
#ደግሞ ሌላ እድል ጌታን ለማምለክ ፀጋ ለመካፈል እግዚአብሔር ቸርነት አድርጎልናል በዚሁ አካባቢ ያላችሁ ኑ አብረን ጌታን እናምልክ::ተባረኩልኝ እወዳቸዋለሁ::
06/09/2026
🇺🇸👉የማለዳው መልዕክት የእናንተ መልዕክት ነው::👇👇👇👇👇👇
#ባሪያዬን ዳዊትን አገኘሁት፥ ቅዱስ ዘይትም ቀባሁት።
እጄም ትረዳዋለች፥ ክንዴም ታጸናዋለች።
ጠላት በእርሱ ላይ አይጠቀምም፥ የዓመፃ ልጅም መከራ አይጨምርበትም።
ጠላቶቹን ከፊቱ አጠፋለሁ፥ የሚጠሉትንም አዋርዳቸዋለሁ።
እውነቴና ምሕረቴም ከእርሱ ጋር ነው፥ በስሜም ቀንዱ ከፍ ከፍ ይላል።መዝ 89:20-24
🇺🇸👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇🇺🇸
#ክብር ሁሉ ለኢየሱስ ይሁን የማይረሳ በጌታ መገኘት የረሰረስንበት ድንቅ ሳምንት እግዚአብሔር ስሙ የተባረከ ይሁን ሃሌሉያ::
Click here to claim your Sponsored Listing.