Awusa.com

Awusa.com

Teilen

A resource and advocacy center for the art, history, culture, ethnography and current affairs of Afa

10/05/2026

"የሰላሙ ስምምነት የሁለቱም ወገኖች አስገዳጅ ምርጫ ነበር" - ዳንኤል ብርሀነ

ደብረጽዮን በፕሪቶሪያ የክህደት ድርጊት እንደተፈጸመ ሊያሳምነን ይፈልጋል። ጌታቸው በበኩሉ የተኩስ አቁም ስምምነቱ የተፈረመው "ወሳኝ ሽንፈት" ሊያጋጥም ጥቂት ሰዓታት ሲቀሩት እንደነበር ሊያሳምነን ይጥራል።

እውነታው ግን የፕሪቶሪያው ስምምነት የነበረውን እልቂት ያስቆመና ሁለቱም ወገኖች እንዲሁም አስታራቂዎቹ ቁርጠኛ ቢሆኑ ኖሮ ወደ ዘላቂ የሰላም መፍትሔ ሊያመራ የሚችል ዕድል የነበረው መሆኑ ነው።

ነገር ግን ማንኛውም የተኩስ አቁም ስምምነት በቸርነት የሚሰጥ ስጦታ አይደለም። ሁለቱም ወገኖች ስምምነቱን አጥብቀው የሚፈልጉበት አስገዳጅ ሁኔታ ላይ ነበሩ፤ ይህም ለማንኛውም የተኩስ አቁም ስምምነት የመጀመሪያውና መሠረታዊው መመሪያ (ABC) ነው።

ስለዚህ ደብረጽዮን እና ጌታቸው ያለፈውን ታሪክ መከራከሪያ ማድረጋቸውን አቁመው መምራት ላይ ቢያተኩሩ ይሻላል—እርግጥ መምራት የሚችሉ ከሆነ።

Daniel Berhane-

09/05/2026

ሠራተኞች 100 ኪ.ሜ ከሮጡ የደመወዛቸውን 130% ቦነስ የሚሰጥ ድንቅ የቻይና ኩባንያ!
የቻይናው ኩባንያ በሠራተኞች ሩጫ ላይ የተመሠረተ አዲሱ የቦነስ ሥርዓት!

አንድ የወረቀት አምራች ኩባንያ የተለመደውን የሥራ አፈጻጸም ግምገማ ወደ ጎን በመተው፣ የሠራተኞችን ቦነስ ከሩጫ ርቀት ጋር አያይዞታል።

አንድ ሠራተኛ በወር ውስጥ 100 ኪሎ ሜትር መሮጥ ከቻለ፣ የደመወዙን 130% ያህል ተጨማሪ ቦነስ ያገኛል።

ለመሮጥ የማይመች ሁኔታ ካለ፣ የእግር ጉዞና ተራራ መውጣት (Hiking) ለርቀቱ ስሌት ውስጥ ይካተታሉ።

ሠራተኞቹ በወር በአማካይ 90 ኪሎ ሜትር በመሮጥ ላይ ሲሆኑ፣ ይህም የስኳር መጠናቸውን ለመቀነስ፣ ኃይል ለመጨመርና ስሜታቸውን ለማሻሻል እንደረዳቸው ገልጸዋል።

ይህ ኩባንያ ከትርፍ በላይ በሰው ላይ መዋዕለ ንዋይ ማፍሰስን መርጧል። "ጤና ሀብት ነው" የሚለውን መርህ በተግባር እያሳየ ይገኛል።

09/05/2026

📍ህወሓት በአክሱም ሙስሊሞች ላይ በአዲስ መልክ አፈና ጀምሯል!

በትግራይ ክልል የእስልምና እምነት ተከታዮች ከህወሓት ቡድን ከፍተኛ ጫና ይደርስባቸዋል፡፡ በክልሉ ሂጃብ መልበስ ፣ በጋራ መስገድ ወደማይቻልበት ደረጃ ላይ እየደረሰ ነው፡፡ ፅንፈኛው የህወሓት ቡድን በተደጋጋሚ ጊዜ የእስልምና እምነት ተከታዮች ላይ አፈናዎችን ይፈፅማል፡፡ በተለይም የአክሱም ሙስሊሞች የመስገጃ ቦታ የላቸውም፣ ትምህርት ቤቶች ሂጃብ የጠመጠመችን ተማሪ ወደትምህርት ቤት አያስገቧትም፡፡

ይህ ሁኔታ ለረዥም ጊዜ በአክሱም ሰፍኖ የቆየ ሲሆን ሰሞኑን ቡድኑ በአዲስ መልክ በጀመረው አደገኛ እንቅስቃሴ በርካታ የእምነቱን ተከታዮች አፍኗል፡፡ በመንገድ ላይ በሚያገኛቸውን የእምነቱ ተከታዮች ላይ ዛቻ እያደረሰ ነው፡፡ አፈናው በትምህርት ቤቶች ላይም ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

ህወሓት በመላው የትግራይ ህዝብ ላይ ያወጀው ጦርነት እንዳለ ሆኖ ሙስሊሞችን ለይቶ የማጥቃቱ ነገር በግልፅ ተጀምሯል፡፡

እንግዲህ በሙስሊም ጠላትነቱ አለቃው ኢሳያስ አፈወርቂም የሚታወቅ ሲሆን አሽከሩ ህወሓትም ይህኑን በመተግበር ክልሉ ለሙስሊሞች የስቃይ ምድር እንዲሆን እየሰራ ነው፡፡

08/05/2026

:- ሌ/ጀ ታደሰ ወረደ ማስጠንቀቂያ ሰጡ!!

በትግራይ ክልላዊ መንግሥት ውስጥ ያለው የውስጥ የሥልጣን ሽኩቻ ወደ ከረረ ደረጃ መሸጋገሩን ተከትሎ፣ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት ሌተናል ጄነራል ታደሰ ወረደ የተቃውሞ መግለጫ አወጡ።

ዛሬ ሚያዝያ 30 ቀን 2018 ዓ.ም “ተመርጠናል” የሚሉ አካላት በጸጥታ ኃይሎች ታጅበው በጊዜያዊ አስተዳደሩ የካቢኔ አዳራሽ ስብሰባ መጀመራቸውን ገልጸዋል።

ድርጊቱ “የሥልጣን ወረራ” መሆኑን የጠቀሱት ጄነራሉ፣ ለሚከተለው ማንኛውም ዓይነት ቀውስ ተጠያቂው ይህ በጉልበት ሥልጣን ለመያዝ የሚንቀሳቀሰው አካል መሆኑን አስታውቀዋል።

Photos from Awusa.com's post 08/05/2026

በዝናብ የታጀበ ጁምዓ አፋር-አብኣላ!!🌧️
Abqaala roobuy racmata!!🌧️❤️

Tuha Ibn ali

Photos from Awusa.com's post 08/05/2026

ጀግናው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የ 130 ሚሊዮን የህልውና ጉዳይ የሆነውን የባህር በራችንን በህግም ይሁን በጦርነት ለማስመለስ ጫፍ ላይ ደርሷል።

#ጉዞ #ወደ #አሰብ 💪💪🇪🇹🇪🇹
💪💪🇪🇹

07/05/2026

የሕወሓት አንጃ የትግራይን ኢኮኖሚ ከኢትዮጵያ ነጥሎ ከሻዕቢያ ጋር ለማቆላለፍ ወስኗል!

የትግራይን ህዝብ ከሀገሩ የመነጠል ወንጀል! ያረጠው አንጃ የትግራይን ኢኮኖሚ ከኢትዮጵያ ነጥሎ ከሻዕቢያ ጋር ለማቆላለፍ የወሰነው ውሳኔ የሀገር ክህደት ነው።

ህዝብን ለፖለቲካ ቁማር ማስያዝ ይብቃ! የህዝብን ሀብት ለግል ጥቅም ማዋል የትውልድ ወንጀል ነው! ንቃ የትግራይ ህዝብ!


!
#ሕወሓት
#ትግራይ
#ኢትዮጵያ

05/05/2026

ሰበር መረጃ‼️
የህወሓት የጦርነት ጥማት እና መፈንቅለ መንግስት .......!
➖➖➖
ሰላም ጠሉ የህወሓት ሐይል የፕሪቶሪያ ስምምነት ስጥስ ቆይቶ በመጨረሻም ሙሉ ለሙሉ ለሰላም ስምምነቱ እና ለሕገ መንግስቱ የማይገዛ ሽፍታ መሆኑ ይፋ አድርጓል።

ሽፍታው ቡድን በፕሪቶሪያ ስምምነት የተመሰረተውን ጊዜያዊ አስተዳደር በመፈንቀል የራሱን ጎበዝ አለቃ የሾመ ሲሆን የሾመው ደሞ ደብረፅዮን የተባለ ለአንድ ሚልዮን ወጣቶች መቀጠፍ ምክንያት የሆነው በአመራር ድክመቱ የሚታወቅ ሰው ነው።

ደብረፅዮን ፖለቲካዊ ልዩነቶችን በውይይት የማይፈታ፡ በሌለው አቅም ሁሉንም በጦርነት ለመፍታት የሚሞክር፣ ድል የማያውቅ ሽንፈት ሽልማቱ የሆነ ሰው ነው።

04/05/2026

🇪🇹👌

ጀግናው የኢፌድሪ አየር ሃይል የታጠቃቸው አዳዲስ በአምስተኛው ትውልድ ቴክኖሎጂ የዘመኑ፣ እጅግ ዘመናዊ የሆኑ፣ ሁሉንም የአየር ሆኔታ የሚቋቋሙ፣ እንዲሁም ከአየር ወደ አየር የሚደረጉ የመከላከያ ተልዕኮዎችን በብቃት መወጣት የሚችሉት፣ ውጤት ቀያሪወቹ SU-35 Fighter Jet ተዋጊ ጀቶች በዛሬው እለት በአፋር ክልል የተሳካ የበርሃ አየር ሙከራ አድርገዋል።

ከ ሚግ 21 ውጭ ምንም የማያውቁ ቆሞ ቀሮች ያለ አቅማቸው ከኢትዮዽያ ጋር ትካሻ መለካካቱን ቢያቆሙ ይበጃቸዋል!!

04/05/2026

ህወሓት በገዛ ሴራዋ ነበልባል እየተለበለበች ነው!!

የትግራይን ህዝብ ለሦስተኛ ዙር የጦርነት ማገዶ ለማድረግ የቆረጠው ህወሓት፣ ዛሬ በገዛ ወታደራዊ አመራሮቿና በህዝብ ቁጣ ግንብ ስር እየተቀበረች ትገኛለች።

የሰላም ስምምነቱን በመናድ ክልሉን ዳግም ወደ እልቂት ለመውሰድ ያቀደችው ሴራ "ለጦርነት አንሰለፍም" ባሉ የቁርጥ ቀን የጦር መሪዎች አይሆንም ባይነት መክኖ፣ ድርጅቱ በውስጥ ሽኩቻና በመርበድበድ ላይ ይገኛል።

እንደ ብ/ጄነራል ነጋሽ ዳኘው ያሉ ከፍተኛ መኮንኖችን ከሃላፊነት በማንሳትና ለማሰር በማሳደድ የምትፈፅመው የድንባዤ እርምጃ፣ ቡድኑ ከውስጥ እንደ ሰም እየቀለጠ መሆኑንና የህልውናው ጀንበር መጥለቋን የሚያበስር የውርደት አዋጅ ነው።

የትግራይ ወጣት፣ ኤሊቶችና ሰራዊቱ "ለጥፋት ቡድን ማገዶ አንሆንም" በማለት የጀርባ አጥንቷን ስለሰበሩት፣ ያቀደችው ህገ-ወጥ የሹመት ድራማ ሳይጀመር በውርደት ተስተጓጉሏል።

ይህ ከውስጥ የነደደው የፍትህ ነበልባል ድርጅታዊ መዋቅሯን አመድ እያደረገው ሲሆን፣ ህወሓት ከገዛ ሰራዊቷና ከህዝብ ጋር የተጋጨችበት የዘንድሮው ዓመት የጥፋት ታሪኳ ማጠቃለያ መሆኑ የማይቀረ መራር እውነታ ነው።

ዛሬ ትግራይ ውስጥ እየተሰማ ያለው የለውጥ ነጎድጓድ፣ የጦርነት ነጋሪት ለሚጎስሙ ጁንታዎች የመጨረሻው የመቃብር ጥሪና የጥፋት ሴራቸው ማክተሚያ ነው።

04/05/2026

ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮችን ከስልጣን እያነሳ የሚገኘው ህውሃት ‼️

ቡድኑ ክልሉን ዳግም ወደ ጦርነት ለማስገባት የወሰነውን ውሳኔ የተቃወሙ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮችን ከሃላፊነታቸው እያነሳና በቦታቸው ሌሎችን እየተካ እንደሚገኝ ታወቀ ።

እስካሁን ባለው ሁኔታ ፅንፈኛው ቡድን የፕሪቶሪያውን ስምምነት በማፍረስ ከጦርነቱ በፊት ያቋቋመውን ህገወጥ ምክር ቤት በመመለስ ክልሉን የጦርነት አውድማ ለማድረግ እያደረገ የሚገኘውን እንቅስቃሴ የተቃወመውን የሰው ሀይል አስተዳደር ሃላፊ ብ/ጄነራል ነጋሽ ዳኘው ከሃላፊነት በማንሳት ኮ/ል ገብረ ገ/ጻድቅን (ገብረ አዴት) የሰው ሀይል አስተዳደር ሃላፊ አድርጎ የመደበ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።

ቡድኑ አሁን ላይ ብ/ጄነራል ነጋሽ ዳኘውን ለጊዜው ከወሳኝ ሀላፊነት ቦታ ገለል በማድረግ ሊያቆየው እና በቀጣይ ቀናት በቁጥጥር ስር ሊያውለው መሆኑም ነው የታወቀው ።

ከብ/ጄነራል ነጋሽ ዳኘው በተጨማሪ ሃዱሽ የተባለ የታጣቂ አመራር ከሃላፊነት የተነሳ ሲሆን ፤ በቀጣይ ቀናት ውስጥም በተመሳሳይ የፅንፈኛውን ቡድን የጦርነት ዕቅድ የተቃወመውን የሎጅስቲክስ መምሪያ አዛዥ ጀ/ል ወ/ገብርኤል (ወዲ ባቤ) ከሃላፊነቱ በማንሳት በቁጥጥር ስር ለማዋል እቅድ የተያዘ መሆኑን ከታማኝ ምንጮች ለማረጋገጥ ተችሏል ።

ጽንፈኛ ቡድኑ በሰሞንኛ ፉከራው መሰረት ሚያዝያ 23 ህገወጡን ምክር ቤት መልሶ ጉባኤ በማካሄድ በ24 የፕሬዝዳንት መረጣ በማድረግ ሹመቱን ይፋ ያደርጋል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረው ሁኔታም የተስተጓጎለው በእነዚሁ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች አይሆንም ባይነት እንደሆነ እየተገመተ ይገኛል።

Wollen Sie Ihr Service zum Top-Medienfirma in Vienna machen?
Klicken Sie hier, um Ihren Gesponserten Eintrag zu erhalten.

Telefon

Adresse

Vienna