Awash Press

Awash Press

Share

ኢትዮጵያ ማንም በቀላሉ እየተዝናና የሚያፈርሳት Candy Crush አይ?

02/06/2026

!
ሀገር ወዳዱ ህዝባችን፣የፀጥታ ኃይሎቻችንና መላው የሀገር ምሶሶዎች በአንድነት በመቆም የማይቻለውን አስችለዋል። ምርጫው በሰላም መጠናቀቁ የሴራ ተንታኞችን አፍ ያዘጋ ሲሆን የኢትዮጵያን የውስጥ ጥንካሬ እና ህዝባዊ አንድነት ለአለም ያሳየ ነበር።ይህ ስኬት ወደፊት ለምንጓዘው የብልፅግና እና የዲሞክራሲ ጎዳና ትልቅ መሰረት ነው።

02/06/2026

!
ምርጫው በሰላም፣በዲሞክራሲያዊ መንገድና በከፍተኛ ስኬት ተጠናቀቀ።ይህ ስኬት ጠላቶቻችንን ያሳፈረ፣ወዳጆቻችንን ያስደሰተ እና የሀገራችንን ሉዓላዊነት በደማቅ ቀለም የፃፈ ታሪካዊ ድል ነው።የሴራው ጉድጓድ በባንዳዎች ላይ ተደፈነ፤ የኢትዮጵያ የነፃነት ሰንደቅ ዓላማ ግን ከፍ ብሎ በሰማይ ስር በክብር ተውለበለበ።

02/06/2026

!
ምርጫው እንዳይካሄድ፣ የሀገር ውስጥ ባንዳዎችና የውጭ ባዕዳን ኃይሎች እጅና ጓንት ሆነው ያልቆፈሩት ጉድጓድ፣ ያልደረደሩት የሴራ እንቅፋት አልነበረም።ኢትዮጵያን በዲፕሎማሲው፣ በኢኮኖሚውና በውስጥ ሰላም መናጋት አውድማ አድርገው ሊያስቀሯት ሉዓላዊነቷንም አደጋ ላይ ለመጣል ሌሊትና ቀን ደከሙ ኢትዮጵያውያን ግን ይህን ሴራ አክሽፈዉ ታሪክ ሰሩ።

02/06/2026

ኢትዮጵያ መርጣለች
በልጆቿ ድምፅ ፀንታለች

ኢትዮጵያ ታሪኳን በጀግንነት በመስዋዕትነትና በአንድነት የጻፈች ታላቅ ሀገር ናት።ከዜጎቿ የምትፈልገውን በፈለገችው ጊዜ ማግኘት የምትችል ሀገር መሆኗ የሚያኮራ እውነታ ነው። ምክንያቱም ዜጎቿ ከሀገራቸው የሚቀርብ ጥያቄ በፈቃደኝነት ምላሽ የሚሰጡ መስዋዕትነትን የማይፈሩ ኩሩና ጀግና ህዝብ ናቸው።ከአድዋ ድል እስከ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክቶች ከወገን ለወገን መረዳዳት እስከ አረንጓዴ አሻራ እንቅስቃሴ የዜጎቿ ተሳትፎ በሁሉም ዘርፍ በግልፅ ታይቷል።ይህም ኢትዮጵያ በህዝቧ ሀይል የምትቆምና የምትገነባ ሀገር መሆኗን ያሳያል።በተጨማሪም በምርጫ ሂደቶች ላይ የተሳተፈው ህዝብ በማስፈራራትና በዛቻ ሳይበገር የሀገሩን የዴሞክራሲ ጉዞ በሀላፊነት ማስቀጠሉ ከተሳትፎና ከአንድነት አንፃር ታላቅ ማሳያ ነው።ኢትዮጵያ በዜጎቿ ተሳትፎ በመስዋዕትነታቸውና በአንድነታቸው የምትገነባና የምትቀጥል ታላቅ ሀገር መሆኗን ትላንት በምርጫ ተሳትፎ ባሳየቸው ተግባር አረጋግጣለች።

02/06/2026

ኢትዮጵያ አሸንፋለች!

በ7ኛው ዙር አጠቃላይ ምርጫ ኢትዮጵያ አሸንፋለች። ባዳ እና ባንዳ ተቀናጅተው በውጭ ሚዲያዎች በመታገዝ ምርጫውን ዋጋ ለማሳጣት ቢረባረቡም፤ የኢትዮጵያ ህዝብ በነቂስ ወጥቶ ከንጋት እስከ እኩለ ሌሊት ተሰልፎ ድምጹን በመስጠት አሸንፏቸዋል። በዚህ ምርጫ ኢትዮጵያ አሸንፋለች!

02/06/2026

በሰላም ተጀምሮ በሰላም የተጠናቀቀው ታሪካዊው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በኢትዮጵያ ድል አድራጊነት ተጠናቋል።

በ7ኛው ሀገር አቀፍ ጠቅላላ ምርጫ የኢትዮጵያ ህዝብ ለዲሞክራሲ ያለውን ቁርጠኝነት በተግባር አሳይቷል።ከነጋቱ 12 ሰዓት እስከ ምሽቱ 6 ሰዓት ድረስ በፀሐይም ሆነ በብርድ ሳይበገር ደከመኝ ሰለቸኝ ታከተኝ ሳይል በትዕግስት ቆሞ ድምፁን ሰጥቷል።የሚበጀውንና የሚሆነውን በእምነት መርጦ የወደፊቱን አቅጣጫ ለመወሰን ተሳትፏል።ይህ ተግባር የሚያሳየው የኢትዮጵያ ህዝብ መሪዎቹን በሰላማዊና በዲሞክራሲያዊ መንገድ የመምረጥ ባህል እያጠናከረ መሆኑን ነው።ይህ ለአገራችን ዲሞክራሲያዊ እድገት ትልቅ መሰረትና ተስፋ የሚሰጥ እሴት ነው።

02/06/2026

ኢትዮጵያ መርጣለች ኢትዮጵያ አሸንፋለች

7ኛው ሀገር አቀፍ ጠቅላላ ምርጫ በኢትዮጵያ የምርጫ ታሪክ ውስጥ ዜጎች ለረጅም ሰዓታት ተሰልፈው ድምፃቸውን የሰጡበት እና ለመጀመሪያ ጊዜ ከፍተኛ ቁጥር ያለው መራጭ የተመዘገበበት ልዩ ምርጫ ነበር። ከዚህም በተጨማሪ መራጮች እንዳይሳተፉ የተለያዩ ዛቻዎችና ማስፈራሪያዎች ቢኖሩም ህዝባችን እነዚህን ችላ በማለት የእናት ሀገሩን ጥሪ ተቀብሎ በምርጫው ተሳትፏል።የሚፈልገውን ፓርቲ በሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ መንገድ በመምረጥም የዜግነት ኃላፊነቱን ተወጥቷል። በእርግጥም ይህ ህዝብ ቅኔ የሆነ ጥበቡንና ፍላጎቱን በተግባሩ የሚገልፅ ህዝብ ነው።

02/06/2026

ኢትዮጵያ አሸንፋለች ኢትዮጵያ ፀንታለች ወደፊትም በአንድነት በሰላምና በልማት መንገድ ትቀጥላለች።

7ኛው ሀገር አቀፍ ጠቅላላ ምርጫ እንዳይካሄድ ከውጭም ከውስጥም የተለያዩ ጫናዎችና እንቅፋቶች ተደርገው ነበር።ይሁን እንጂ ሀገራቸውን የሚወዱ ኢትዮጵያውያን በአንድነት በመቆምና በፅናት በመሳተፍ ምርጫው በሰላምና በስኬት እንዲጠናቀቅ አድርገዋል።ህዝባችን በሰላማዊ መንገድ ድምፁን በመስጠት የዴሞክራሲ ባህሉን አሳይቷል የኢትዮጵያንም ክብርና ፅናት አረጋግጧል።ይህ ስኬት የአንድ ወገን ብቻ ስኬት ሳይሆን የመላው ኢትዮጵያ ህዝብ ስኬት ነው።በችግሮች መካከል ተስፋ ሳይቆርጥ በፈተናዎች መሃል በፅናት በመቆም ሀገሩን ከሁሉ በላይ ያስቀደመ ህዝብ ያስመዘገበው ድል ነው።

02/06/2026

"ይሄንን ህዝብ ማገልገል መታደል ነውና ተመራጮች ያከበራችሁን አክብራችሁ ለዴሞክራሲ ስርአት ዋጋ የከፈለውን ይሄንን ህዝብ በንፅህና ለማገልገል ያብቃችሁ።"

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ

Photos from Abiy Ahmed Ali's post 02/06/2026
Want your business to be the top-listed Media Company in Dubai?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Website

Address

Dubai